እስራኤል ማን ናት? አይሁዶችስ  እነማን ናቸዉ?
(WHO IS ISRAEL?)
Original English By Norman Manzon
Translation by Zemen Endale Lashetew


1.
   
ግቢያ

በብዙ ምክንያቶች የምናጠናዉን ርእሰ ጥናት በማብራራት መጀመር አለብን፤እስራኤል ማን ናት? አይሁድስ እነማን ናቸዉ? እብራዉያንስ እነ ማን ናቸዉ?

2.    እስራኤል ማን  ናት?

. ሕዝብ እንዴት ይጠራል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ብዙ ጊዜ ሕዝቦች የሚወሰኑት በተፈጥሮአቸዉ በወንድ የዘር ሐረግ ነዉ፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ በወንድ የዘር ሐረግ ለመጠራቱ ግልጽ ነዉ፤ ለምሳሌ ዘፍ 105 ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ፤  ከዚህ ቁጥር በፊት በኋላም ያለዉን ክፍል ስንመለከት በወንድ የዘር ሐረግ ሲጠራ እናያለን፤ ለምሳሌ .6  የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው።

ኩሽ፡- የዘር ሐረጉ ከኑቢያ እና ኢትዮጰያ ጋር ይገናኛል

ምጽራይም- የታወቀ የእብራዉያን ስም ሲሆን በላይኛዉና በታችኛዉ ግብጽይህም የሚገኘዉ በሰሜን አፍሪካከነዓን እርሱም የከነናዉያን አባት ነበር፤

በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የካም ልጅ ማለት የቀደሙ ሕዝቦች አባቶች ነበሩ ብዙ ጊዜ ‹‹ሕዝብ›› የሚለዉ ቃል ከአገር ጋር የሚያያዝ ሲሆን በዚህ የጥናት መጽሐፍ ግን ሕዝብ  የሚለዉ በመጀመሪያ የሰዉ ዘር በሙሉ ከአንድ የጋራ አባት እንደመጣ እንመለከታለን፤

. የእስራኤል ሕዝብ እንዴት ተመሰረተ?

የእስራኤል ሕዝብ በወንድ የዘር ሐረግ የተወሰነ ነዉ፤ እግዚአብሔር አብርሃምን ጠራዉ እና ከእርሱ ጋር ቃልኪዳን አደረገ በእርሱ ታላቅ ሕዝብ እንደሚፈጠር ተናገረ (ዘፍ 121-2) ከአብርሃም ልጆች በመቀጠል ወደ ይስሀቅ ተሻገረ (ዘፍ 262-5) የይስሀቅ ልጆች ያዕቆብና ኤሳዉ ከዚያም እግዚአብሔር ወደ ይስሀቅ ልጅ ከያዕቆብ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ( ዘፍ 2813-15) በመቀጠልም የያዕቆብ ስም እስራኤል ሆኖ ተለወጠ ( ዘፍ 3228) ከዚያ ጀምሮ እስራኤል በወንድ የዘር ሐረግ ሲጠሩ  በእስራኤል ሲጠራ የነበረዉ ስም ዘሮቹ ደግሞ እስራኤላዉያን ተባሉ፤ይህም አገሪቱ የምትጠራበት ስም ሆነ የእስራኤልም ልጆች ለእህል ሸመታ ከመጡቱ ጋር ገቡ፤ በከነዓን አገር ራብ ነበረና (ዘፍ425 4521465 ዘጸአት2317 1ዜና 21) ከዚያም ሕዝቡ  እርሱ በሕይወት በነበረ ጊዜ ‹‹እስራኤል›› ተባለ፤( ዘፍ 347)

ነገር ግን አንድ ሰዉ እናቱ እስራኤል ሆና አባቱ አሕዛብ ቢሆንስ? በርግጥ ይህ ሰዉ በአባቱ አገር ነዉ የሚጠራዉ አንድ ሰዉየዉ ግን ራሱን ከእስራኤል ጋር ራሱን ማመሳሰል ከፈለገ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል መሆን ይችላል፤ ለምሳሌ ጢሞቲዎስን መመልከት እንችላለን (ሐዋ 161-3)

ጳዉሎስ በነጻነት ጢሞቲዎስን አስገረዘዉ ምክንያቱም እናቱ አይሁድ ነበረችና መገረዝ ደግሞ የግድ ነዉ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር የገባዉ ቃል ኪዳን ስለሆነ ዘፍ (1712-14)

( የሙሴ ኪዳን በመስቀል ላይ አይሰራም ወደዚህ መጥቶ ሊሰራ አይችልም የአብርሃም ኪዳን እስካሁንም ይሰራል) በሚያከራክር መልኩ ጳዉሎስ  ቲቶን ለማስገረዝ እምቢ አለ፣ ምክንያቱም ከአይሁድ የሆነ ቤተሰብ ስለሌለዉ ነዉ፤( ገላ 21-5 .3) አንድ ሰዉ አይሁድ እናት ኖሮት አባቱ ግን አሕዛብ ከሆነ  እርሱ ወይም እርስዋ ወደ እስራኤል ሕዝብ የመቀላቀል እድል አለዉ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል እንደሆነ ነዉ፤ በወንድ ጉዳይ መቀላቀል የሚችለዉ በመገረዝ ነዉ፤እርሱ ወይም እርስዋ እስራኤል መሆን ካልፈለገች በአባትዋ ወንድ የዘር ሐረግ አሕዛብ ሆኖ ይቀራል፤

ሁሉንም ወደ ቤት ለማምጣት አንድ  ሰዉ እስራኤላዊ ለመባል የአብራሃም የይስሀቅና ያዕቆብ ዘር ሆኖ በወንድ የዘር ሀረግ መጠራት አለበት፤ አንድ ሰዉ ግን አይሁዳዊ እናት ኖሮት አባቱ አሕዛብ ከሆነ እና ራሱን ከእስራኤል ጋር ካመሳሰለ ይህ ሰዉ በእግዚአብሔር አይን ሲታይ እስራኤል ነዉ፤ እስራኤላዊ ለመሆን መገረዝ  የግድ ነዉ፤

አይሁዳዊነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከተጠቀሰዉ የሚለየዉ ነገር አለ፤ ማህበራዊም ነዉ፣አይሁዳዊነት ብሔር ነዉ፤አይሁዳዊነት ከብሔር በተጨማሪ ራሱን ከአይሁድ ሕዝብ ጋር ማመሳሰል ያስፈልገዋል፤ ከአይሁድ ሕዝብና ባህል ጋር ራሱን አብሮ ማስኬድ ይኖርበታል፤ ይህ ራስን ማመሳሰል ወደ አይሁድነት የመመለስ አንዱ ምልክት ሊሆን ይችላል፤ከአይሁድ ሕዝብ ጋር በጋብቻ መጣመር፣በማደጎ የአይሁድ ቤተሰብ እንዲሆን በማድረግና የመሳሰሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከሁለቱ አንደኛዉን መንገድ ብቻ የሚከተል ነዉ፤ ማህበራዊዉ ትንታኔ አልተጠቀሰም፤እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የአብርሃም፣ የይስቅና ያዕቆብ ዘር የሆነ ብቻ አይሁዳዊ እንደሆነ ነዉ የሚናገረዉ፤ እንደ ማህበራዊ ጥናት ትርጉም አንድ የአየርላንድ ዜጋ  የሆነ ሰዉ ከአይሁድ ቢያገባና ወደ አይሁድነት ቢለወጥ በተመሳሳይ የአየርላንድን ባህል ሊይዝ ይችላል፤ባህሉና ከአይሁድ የወረሰዉ ነገር ተጋብተዋል እንደገና የተለወጠበት ባህል አለ፤ እርሱ በማህበራዊ ነገር አይሁዳዊ ነዉ ወይስ አየርላንዳዊ ነዉ? እንደጠያቂዉ ሁኔታ ይወሰናል!

ቁልፉ ነጥብ የተነሳዉ በማህበራዊ ትርጉም አይሁዳዊነት ሲተረጎም ነዉ፤ በማህበራዊ ጥናት አይሁዳዊነት የማይጠቅምና ትርጉም አልባ ነዉ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊዉ አይሁድነት ትርጉሙ እንደሚከተለዉ ይቀርባል፤እግዚአብሔር እንዳለዉ በደም አይሁዳዊ መሆን ለሁሉም ሰዉ የሚሆን አይደለም፤ በማህበራዊ ጉዳይ አይሁዳዊ የሆኑ ግን የአብርሃም፣ይስሀቀና ያእቆብ በደም ያልተገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ፤

. በምን ታሪካዊ ቅኝት ነዉ እስራኤል የተፈጠረችዉ?

1.    እስራኤል መቼ ተፈጠረች?

እስራኤል ከተመሰረተች በግምት 2000 / አካባቢ በአብርሃም፣ ይስሀቅ እና ያዕቆብ ነዉ

2.    ይህቺ የተፈጠረች እስራኤል መቼ ነዉ የጠፋችዉ?

ይህ ሁለት ነጥቦችን ያሳየናል፤

1.    አይሁዳዊነት የተገለጸዉ ወደፊት በሺህ አመተ መንግስት ጊዜ የሚሆነዉን ጊዜ ነዉ ለምሳሌ (ዘካርያስ 823) -‹‹በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ››

1.ኢሳ 6520 በሺህ አመቱ ጊዜ የሚወለዱ ልጆች፡-…‹‹ወይም ዕድሜውን ያልፈጸመ ሽማግሌ አይገኝም’’

ከእነዚህ ነጥቦች የተነሳ እስራኤላዉያን እስከ ሺህ አመተ መንግስቱ ጊዜ ድረስ ልጆችን ይወልዳሉ፤

የእስራኤል ሕዝብ የተጀመረዉ 2000/ ሲሆን እስከ ሺህ አመቱ ድረስ ይቀጥላል

3.አይሁዶቸ እነማን ናቸዉ?

 ‹‹አይሁድ››እና ‹‹እስራኤል›› የሚሉትን ቃላት እያቀያየርሁ እጠቀማለሁ፤ ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጠቀሜታ አለዉን?

1.    ‹‹አይሁድ›› ትርጓሜ

ዮሐ 49 ‹‹ለዚህ ሳምራዊቲቱ፦ አንተ የይሁዳ ሰው ስትሆን ሳምራዊት ሴት ከምሆን ከእኔ መጠጥ እንዴት ትለምናለህ? አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር አይተባበሩም ነበርና›› በዚህ ክፍል ዉስጥ አሕዛብ ኢየሱስን የሚያዩት አይሁዳዊ እንደሆነ ነዉ እርሱም አልካደም፤ እስራኤላዊዉ  ዮሐንስም ኢየሱስን ሲገልጸዉ የኢየሱስ ብሔር አይሁድ እንደሆነ ነዉ፤ ዮሐ 1835 ጲላጦስ መልሶ፦ እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል? አለው። እዚህ እንደምናየዉ ኢየሱስ ብሔሩ አይሁድ እንደሆነ ነዉ እርሱም አልካደም፤

ሐዋ 2127-28 ሉቃስ አይሁዶች እስራኤላዉን እንደሆኑ ተናግሯል ሰባቱ ቀንም ይፈጸም ዘንድ ሲቀርብ ከእስያ የመጡ አይሁድ በመቅደስ አይተውት ሕዝብን ሁሉ አወኩና፦ የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ እርዱን ሕዝብን ሕግንም ይህንም ስፍራ ሲቃወም ሰውን ሁሉ በየስፍራው የሚያስተምረው ሰው ይህ ነው፤ ጨምሮም የግሪክን ሰዎች ደግሞ ወደ መቅደስ አግብቶ ይህን የተቀደሰ ስፍራ አርክሶአል ብለው እየጮኹ እጃቸውን ጫኑበት።

በጥላቻ የተሞላዉ ሕዝብ ጳዉሎስም ራሱን እንደ እስራኤል ሰዉ አድርጎ ነበር በመጮህ አይሁዳዊ ነኝ አለ (. 39) እና ፊሊ 35 ላይ ራሱን ሲገልጽ በስምንተኛ ቀን የተገረዝሁ የእስራኤል ወገን

በእነዚህ ክፍሎች ዉስጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ በአሕዛብ አስተሳሰብ፣የማያምኑ አይሁዳዉያን፣የኢየሱስ ደቀመዛሙርት፣ እና ኢየሱስ ራሱ አይሁዳዊ እና እስራኤላዉያን አንድ አይነት መሆናቸዉን ነዉ የሚያዉቁት፤ ጳዉሎስን ከመስቀሉ በኋላ የሆነ አማኝ ማለት ተገቢ አይደለም፤ የአሕዛብ ሐዋርያ ቢሆንም ራሱን አይሁዳዊና እስራኤል አይሁድ አድርጎ ነዉ፤

አይሁድ የእስራኤል አባልና ወገን ነዉ፤ አይሁድ ማለት ሰፋ ባለዉ በመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ከእስራኤል አገር/ወገን/ ጋር ተመሳሳይ ነዉ፤

2.    አይሁድ የአይሁድን ማንነት ሊያጣዉ ይችላልን?

. ከምድራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ አይሁዶች

በበአለ ሃምሳ እለት የተገኙ አይሁዳዉያን ከሮም የመጡ ጎብኚዎች እና ከአሕዛብ ወደ አይሁድነት የተለወጡ ናቸዉ (ሐዋ 210)

ከምድራቸዉ ዉጭ የሚኖሩ አይሁድ አሁንም አይሁዳዉያን እንደሆኑ ይታሰባሉ፤

. ጣኦታትን የሚያመልኩ አይሁዶች

እንዲህም ሆነ ጌዴዎን ከሞተ በኋላ የእስራኤል ልጆች ተመለሱ፥ በኣሊምንም ተከትለው አመነዘሩ፤ በኣልብሪትንም አምላካቸው አደረጉ የእስራኤልም ልጆች በዙሪያቸው ከነበሩት ከጠላቶቻቸው ሁሉ እጅ ያዳናቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን አላሰቡትም፤ መሳፍንት 833-34

በአልን የሚያመልክ እስራኤላዉያን እስራኤላዉያን እንደሆኑ ይታሰባሉ፤ከብዙ  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዉስጥ ይህ አንዱ ነዉ፤በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ዉስጥ አንድ ሰዉ ከእስራኤል ተወልዶ እስራኤላዊ በየትኛዉም ምክንያት ማንነቱን ያጣል የሚል አለ?

3.    ‹‹አይሁዶች›› ይህን ቃል ኢየሱስና ደቀመዛሙር ተጠቅመዋል

. ጥያቄ የሚሆኑ ክፍሎች

እስኪ ለጥቂት ጊዜ በአዲስ ኪዳን በተለይም ዮሐንስ ወንጌልና የሐዋርያት ስራን እንመልከት፤ ‹‹አይሁዶች›› እነዚህን ነገሮች ሲጠቀሙ ጥቂቶችን ወደ መደነቅ ያመጣል በርግጥ ኢየሱስ ዮሐንስና ሌሎች ደቀመዛሙርት ራሳቸዉን ከእስራኤል ወገን በጥቂቱ ራሳቸዉን ያገለሉ ነበሩ፤ አራት የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እንመልከት፤

ዮሐ218 2018 20 ስለዚህ አይሁድ መልሰው፦ ይህን ስለምታደርግ ምን ምልክት ታሳየናለህ? አሉትስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት

ዮሐንስ 5161816 ስለዚህም በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት ነበር ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር….እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር።

ዮሐ 1155 የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር። ብዙ ሰዎችም ራሳቸውን ያነጹ ዘንድ ከፋሲካ በፊት ከአገሩ ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ

ዮሐ 1333 ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድም፦ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አይቻላችሁም እንዳልኋቸው፥ አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ፤

. ገለጻዎች

አይሁድ የሚለዉን ትርጓሜ  እንዳየነዉ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ አይሁድ መሆናቸዉን አልካዱም ከአይሁድ ወንደሞቻቸዉ ራሳቸዉን አላራቁም፤ክፍሉ ግን ገለጻ ይፈልጋል፤

ኢየሱስ አይሁድ ሲል ምን ማለቱ ነዉ በዮሐ 1333  እርሱ ሲናገር ለአይሁድም? ዮሐ 732-34 ለፈሪሳዉያንና ለካህናት አለቆች ተናገረ፣የኋለኛዉ ቡድን ደገሞ ሰዱቃዉያን ናቸዉ፤ፈሪሳዉያንና ሰዱቃዉያን ትልቁ የሐይማኖት ተቋሞችን የመሰረቱና በአይሁድ መካከል የመፍረድ ስልጣን ያላቸዉ ናቸዉ፤ በሌላ ቃላት ኢየሱስ በአይሁዶች ዘንደ በእስራኤል የአይሁድ ባለስልጣን ተደርጎ ይታሰብ ነበር፤ ዮሐንሰ በአይሁድ ምን እነደተባለ ግልጽ ነዉ በዮሐ21820 እና 51618

ዮሐንሰ በአይሁድ ምን ተባለ 1155  ይህቺን ሐረግ ተጠቀመ ‹‹የአይሁድም ፋሲካ ቀርቦ ነበር።››

1.    የአይሁድ ፋሲካ ነበር ምክንያቱም ለአይሁድ ሕዝብ እግዚአብሔር ያዘዘዉ ትዕዛዝ ነበር፤(ዘጸ 12) እና

2.    ከመስቀሉ በፊት ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ራሳቸዉ አይሁዳዉያን መሆናቸዉንና ከሙሴ ሕግ በታች እንደሆኑ ፋሲካንም ማክበር እንዳለባቸዉ  ያዉቁ ነበር፤ ማቴ 2617-18

ዮሐንስ የአይሁድ ሕዝብ እንደሆኑ ብቻ ገለጸ

. ሌሎች ማስረጃዎችና አጠቃቀሞች

በፊሊጵስዮስ 35 ላይ ጳዉሎስ ራሱን እስራኤላዊ እንደሆነ በአራት መንገድ ገለጸ 1) በስምንተኛ ቀን የተገረዝኩ 2)  ዋና እስራኤል 3) ከብንያም ነገድ 4) ከዕብራዉያን ዕብራዊ ( ዕብራይስጥ ተናጋሪ)…..

ገላ211-13 ጳዉሎስ ጴጥሮስን ከአሕዛብ ጋር ሲያነጻጽር ጴጥሮስ አይሁድ እንደሆነ ተናገረ፤ ከሌሎች አይሁድ አማኞች ጋር ይገልጸዋል፤በርናባስም አይሁዳዊ ነዉ፤

የሚቀጥለዉ ጥቅስ ጳዉሎስ ጴጥሮስን በቀጥታ አይሁድ ይለዋል አንተ አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ እንዴት ግድ አልሃቸው?

ዮሐ 1131 ሲያጽናኑአት ከእርስዋ ጋር በቤት የነበሩ አይሁድም ማርያም ፈጥና እንደ ተነሣችና በዚህ ክፍል ዮሐንስ አይሁድን የእስራኤላዉንን ዜግነት መግለጹ ነዉ

. ማጠቃለያ

1.    ኢየሱስ እና የእርሱ አይሁድ ደቀመዛሙርት አይሁድነታቸዉን ተናገሩ እንጂ አልካዱም 

2.    በጊዜዉ የተጠቀሙት ‹‹አይሁድ›› የሚለዉ ቃል  የሚገልጸዉ

) አገሩን በሙሉ

) የአይሁድ ሕዝብ ስልጣን እና

) እያንዳንዱን እስራኤላዉያን

3.    ማንኛዉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ‹‹አይሁድ›› ወይም ‹‹እስራኤል›› የሚለዉ ቃል የሚገልጸዉ የአብርሃም፣ይስሀቅና ያእቆብን ዘሮች ነዉ፤

4.    አሕዛብ ሆነዉ ከአይሁድ ጋር የተባበሩ አይሁድ ተብለዉ ይጠራሉን?

በሩት 116 ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፤ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፤

ሩት ሞአባዊት ናት ነገር ግን ወደ እስራኤል ምድር ሄደች ራስዋን በእስራኤል መንግስት /መስፍን/ ስር አስቀመጠች እስራኤላዊ ወይም አይሁድ ተብላ ተጠርታ አታዉቅም ነበር እርስዋ ሞአባዊት ናት (ሩት 122 2221 45 410)

5.    አሕዛብ ወደ ይሁዲነት ተቀይረዉ አይሁዳዊ ተብለዉ ይጠራሉን?

በሩት መጽሐፍ ዉስጥ ሩት ብቻ አይደለችም ሕዝብሸ ሕዝቤ አምላክሽ አምላኬ ይሆናል ያለችዉ እርስዋ ብቻ አይደለችም ከሞአብ ወደዚያ ምድር ለመኖር የሄደችዉ ራስዋን ከእስራኤል አምላክ ስር አስገዛች ለሙሴ ሕግ ለመገዛት ወሰነች እስካሁንም ግን እስራኤላዊ ወይም አይሁዳዊ ተብላ አልተጠራችም ነገር ግን ሞአባዊት ናት፤

በመጽሐፍ ቅዱስ አሐዛብ ወደ ሙሴ ሕግ፣ፈሪሳዊነት ወይም ወደ አይሁዳዊ ስርአት ሲመጣ  የተለወጠ/ልዉጥ/ ይባላል፤ሩት በትዉልዷ ሞአባዊት ናት ነገር ግን ወደ ሙሴ ሕግ አይሁዳዊነት ተለወጠች፤

ማቴዎስ 2315 እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ አንድ ሰው ልታሳምኑ በባሕርና በደረቅ ስለምትዞሩ፥ በሆነም ጊዜ ከእናንተ ይልቅ ሁለት እጥፍ የባሰ የገሃነም ልጅ ስለምታደርጉት፥ ወዮላችሁ፤ ኢየሱሰ ከአሕዛብ ወደ አይሁድነት ትለዉጣላችሁ አላላቸዉም፤

ሐዋ 1343 እግዚአብሔርን የሚፈሩ አሕዛብ በምኩራብ ዉስጥ የሚሰበሰቡ አይሁዳዉያን ተብለዉ አልተጠሩም፤ ነገር ግን የተለወጡ ይባላሉ፤ ጉባኤውም ከተፈታ በኋላ ከአይሁድና ወደ ይሁዲነት ገብተው ከሚያመልኩ ብዙዎች ጳውሎስንና በርናባስን ተከተሉአቸው፥ እነርሱም ሲነግሩአቸው በእግዚአብሔር ጸጋ ጸንተው እንዲኖሩ አስረዱአቸው፤ እንዴት ነዉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተለወጡትንና አይሁዳዉያንን መለየት የሚቻለዉ?

ሐዋ210 የሙሴን ሕግ የሚከተሉ የተለያዩ ቡድኖች ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ በአለሃምሳን ለማክበር ተሰባስበዉ ነበር፤( ዘጸ 3418-23) የተለያየ ስም ነበራቸዉ ይኸዉም ከሮም የመጡ ጎብኚዎች፣ አይሁዶችና ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተለወጡ ናቸዉ፤

ሐዋ65 በመጀመሪያ ወደ ይሁዲነት የተለወጡ አሕዛብ ክርስቶስን ያመኑ አይሁዶች አይሁዳዉያን ተብለዉ አይጠሩም ነገር ግን የተለወጡ ይባላሉ፤ ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ

6.    አስቴር 817

ለምሳሌ በብዙ በጣም ጥሩ በሚባሉ እትሞች ላይ ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተለወጡ ሰዎች አይሁዳዉያን ተብለዉ ተጠርተዋል፤ ለምሳሌ ኒዉ አሜሪካ ስታንዳርድ መጸሐፍ ቅዱስ፣ ‹‹…አይሁድንም መፍራት ስለ ወደቀባቸው ከምድር አሕዛብ ብዙ ሰዎች አይሁድ ሆኑ›› ( አስቴር 817) የካሊበር ከይል ማብራሪያ መጽሐፍና የደሊች ‹‹አይሁዳዊ ለመሆን አይሁዳዊ ነኝ ብሎ መናገር›› አንዳንድ እትሞች ላይ እንዲህ አይነት ገለጻ ሲጠቀሙ የአይሁድን እምነት መቀበላቸዉን ለመግለጽ ነዉ፤( የቅርቡ እንግሊዝኛ ትርጉም) እና ራሳቸዉን አይሁዳዊ ብለዉ ጠሩ( እንግሊዝኛዉ ስታንዳርድ እትም) አንዳንድ እትሞች እንደ / ቻርለስ ራይሬ ‹‹  የአይሁድን እምነት የተቀበሉ እንደ ተለወጡ›› ( የራይሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እና ከሊልና ደሊች ልክ እንደ ላይኛዎቹ ‹‹ አይሁዳዊ ነኝ በሎ ከተናገረ›› ሲል የአስቴር መጽሐፍ የተጻፈበት ዘመን 465 . ክስተቱ ከተከናወነ በኋላ ነዉ) ‹‹ አይሁድ›› ማለት የእስራኤል ዘሮች ናቸዉ፤ አንድ አይሁዳዊ የቂስ ልጅ የሰሜኢ ልጅ የኢያዕር ልጅ መርዶክዮስ የሚባል ብንያማዊ በሱሳ ግንብ ነበረ።( አስቴር 25)

የትኛዉ ነዉ እጅግ ጥሩዉ ትርጉም? ሁለት ክፍሎች በተቃራኒ አቅጣጫ እየተጓዙ ነዉ፤

1.    ሚቲያሃዲም የሚባለዉ የእብራይስጡ ቃል ዪሂድ እንዲሁም ስርወ ቃሉ ይሁዲ ወይም ይሁዲም የሚለዉ ሲተረጎም ‹‹አይሁድ  እና አይሁዶች›› ተብሏል፤ ይህ በርግጥ ሚቲያሃዲም የሚለዉ ቃል የሚወስደን አይሁዶች ወደ ሚለዉ የቃል ፍቺ ነዉ፤

2.    እንዲሁም ሚቲያሃዲም የሚለዉ ቃል ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተለወጡንም የሚያስብል ዕድል አለ፤

. ክፍሉ በግልጽ ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተመለሱ ስለመሆናቸዉ ከተናገረ

. ይህ ስነ ቃል ትርጓሜ የተሰጠዉ በዶ/ ፍሩችትነባዉም ነዉ

ለሂትሂድ የሚለዉ ግሱ ( በኢንፊኒቲቭ መልክ ሚቲያሃዲም፣ ይህም ፓርቲሲጵል ይሆናል) ይህም ለሂተናተዝር ከሚለዉ ቃል ጋር ተመሳሳይ ትርጓሜ አላቸዉ፤ ቃሉ ትኩረት የሚያደርገዉ  የማንነት ብሔራቸዉን የሚቀይሩ ሳይሆን ሐይማኖታዊ ማንነታቸዉን መቀየራቸዉ ነዉ፤ ለሂተናዘር ማለት ወደ ክርስትና የሚለወጡ ሰዎችን የሚያሳይ ሲሆን ለሂትያሂድ ግን ወደ ይሁዲነት የሚለወጡትን የሚያመለክት ነዉ፤ የበለጠ ትክክል የሚሆነዉ ወደ ይሁዲነት የተቀየሩትን ነዉ፤ ይህ ማለት ግን በብሔር ማንነታቸዉ ወደ ይሁዲነት የተቀየሩትን ማለት ግን አይደለም፤

. በተለይ በአዲስ ኪዳን የአሜሪካዉ ስታንዳርድ  እትም መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ አይሁድ እና አይሁዶች የሚለዉ ቃል 256 ጊዜ የተጻፈ ነዉ፤ አስቴር 817 ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የተመለሱትን ‹‹አይሁዶች›› ብሎ ተርጉሞታል፤( የአዲስ  ኪዳን መጽሐፍ ዉስጥ እንደተገለጸዉ አይነት ግን አይደለም) ይህ ክፍል በተተካዉ ስነመለኮት ስንገመገመዉ ከዚህ በታች ያለዉን ጥናት እንመልከት)

. በዚህ ጥናት ዉስጥ  ኢየሱስ ‹‹አይሁድ›› ብሎ የተጠቀመዉን ቃል የእርሱ ደቀመዛሙርቱ የተረዱት በደም አይሁድ የሆኑትን ነዉ፤

ከላይ ያሉትን ነገሮች ግምት ዉስጥ ከተን ሚዛናዊዉ ትርጉም ሐይማኖት የቀየሩትን ነዉ፤ወደ ‹‹ይሁዲነት መለወጥ›› ማለት ወደ ‹‹ይሁዲነት መምጣት›› ማለት ነዉ ወይም ተመሳሳይ ናቸዉ፤ ከላይ ያሉ ትርጉሞች እንዳሉ ሆነዉ ለሂትያሂድ እና ለሂተናተዝር የሚሉትን ቃላት ማያያዝና የተሸከሙትን ትርጉም መመልከት፤ አይሁድና አይሁዶች የሚሉት ቃላቶች የሚያሳዩት ኢየሱስ የተጠቀመዉ በስጋና ደም ከአብርሃም፣ ይስሀቅና ያዕቆብ ዘር መሆን ነዉ፤

4.ዕብራዉያን እነማን ናቸዉ?

በመጀመሪያ ቃሉ የተገለጸዉ በዘፍ 1413 ላይ ሲሆን አብርሃም ዕብራዊ ነበረ፤በመቀጠል ዕብራዊ የሚለዉ ቃል የተጻፈዉ በግብጻዉያን ለእስራኤል የተሰጠ ስም ነዉ ዘፍ 3914 ዘጸ 116 ወዘተ.)  ዮሴፍ እንዲህ አለ ‹‹እኔን ከዕብራውያን አገር ሰርቀው አምጥተውኛልና፤ ከዚህም ደግሞ በግዞት ያኖሩኝ ዘንድ ምንም አላደረግሁም›› ዘፍ 4015 ዮናስ ራሱን ዕብራዊ ብሎ ጠራ (ዮናስ 19) እግዚአብሔር እስራኤላዉያንን ዕብራዉያን ብሎ ጠራ( ለምሳሌ ዘጸ 212) በሐዋ 61 ሁለት የእስራኤላዉያን ቡድኖች ስሞች በግሪክ ባህል ተጸእኖ ዉስጥ ያሉ አይሁዳዉያን ንጹህ አይሁዳዉያንን ይቃወሙ ነበር፤ 2 ቆሮንቶስ 1122 ጳዉሎስ ሲናገር ዕብራዊ ናቸዉን? እኔም ነኝ፤ እስራኤላዊ ናቸዉን? እኔ ደግሞ ነኝ፤ የአብርሃም ዘር ናቸዉን? እኔ ደግሞ ነኝ፤ በፊሊ 35 ጳዉሎስ ራሱን ከዕብራዊም ዕብራዊ ነኝ አለ፤

5.    እስራኤል፣ አይሁዶች፣ዕብራዉያን፡ ማጠቃለያ እና ዉስብስብ ዉጤት

. መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትርጓሜ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ዉጭ የሆነ ትርጓሜ ዉስጥ መግባት አያስፈልግም ማንኛዉም ወንድና ሴት የአብርሃም፣ የይስሀቅና ያዕቆብ ዘር ሆኖ በወንድ የዘር ሐረግ ላይ የሚሄድ ከሆነ እስራኤላዊ፣አይሁዳዊ ወይም ዕብራዊ ይባላል፤አባቱ ወይም እናቱ አሕዛብ ከሆነ ሰዉ እስራኤላዊ የመሆን ምርጫ አለዉ፤ ወንድ ከሆነ በመገረዝ ማረጋገጥ አለበት ከዚያ በኋላ እስራኤላዊ ይባላል፤ይህን ያላደረገ ግን አይሁዳዊ፣ዕብራዊ ወይም እስራኤላዊ ሊባል አይችልም፤ከተገረዘ (ትክክለኛ አይሁድ ይባላል) ወይም ከመሲሁ አይሁዳዊነት ጋር ይጣበቃል፤ የአይሁድ ሕዝብ የተጀመረዉ በተፈጥሮ የአብርሃም፣ይስሀቅና ያእቆብ ትዉልድ ሲሆን እስከ ሺህ አመተ መንግስቱ ዘመን ድረስ ይቀጥላል፤

. ‹‹አይሁድ ሆኜ ተወልጄ አይሁድ ሆኜ እሞታለሁ!››

 ‹‹አይሁድ ሆኜ ተወልጄ አይሁድ ሆኜ እሞታለሁ!›› የሚለዉ ንግግር ወንጌሉ ሲሰበክላቸዉ ከብዙ አይሁዳዉያን የሚነገር ንግግር ነዉ፤ ከአብርሃም፣ይስሀቅና ያዕቆብ ዘር ተወልዶ አይሁዳዊነትን ማጣት አይቻልም፤ ክርስቶሳዊ አይሁዳዊነት የሚከሰሱበት ምክንያት አይሁዳዊነትን ስላልተቀበሉ ነዉ፤ ወይም ደግሞ በቅጽበት አይሁዳዊ ወደ አለመሆን ሲለወጡ የእስራኤል ሰዎች ግን እንዲህ ይላሉ ‹‹ አይሁዳዊ ሆኜ ተወልጃለሁ አይሁዳዊ ሆኜ እሞታለሁ!›› ይላሉ፤ በርግጥ በዚህ መረዳት አይሞቱም ምክንያቱም እነርሱ በሕይወት እያሉ ንጥቀት ይፈጠራል፤ በተጨማሪ እስራኤላዉያን በአልን ሲያመልኩ አይሁዳዊ ማንነታቸዉ ይቀጥላል፤አይሁዳዊ የክርስቶስ አማኞች የአይሁድ ንጉስ እንዲሁ ይቀጥላል፤ሌሎች እንደሚሉት አይሁዳዊነቱን ይጠፋል ሲሆን እግዚአብሔር ግን አያደርግም፤

4.    የክርስቶስ አካል ምንድን ነዉ?

) መግቢያ

የእኛ ንግግር ሲነበብ ‹‹ እስራኤል ከክርስቶስ አካል ትለያለች የሚል ነዉ››

ብዙዎች እንደሚያምኑት ቤተክርስቲያን፣ የክርስቶስ አካል እስራኤል ትሆናለች ወይም ከእስራኤል ጋር ትተባበራለች ወይም እስራኤልን ትተካለች፤ ወይም  በተምሳሌታዊ ንግግር መንፈሳዊ እስራኤል ናት፤ ስለዚህ ዋናዉን ነገር ስንገመግም እና ስንለካዉ ዛሬ እስራኤል እንዳለች ነዉ፤ ይህ እንዴት እንደሆነ እናያለን፤

) የክርሰቶስ አካል ሲገለጽ

1.    ‹‹የክርስቶስ አካል››

መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስ አካል ቤተክርስቲያን እንደሆነች ይናገራል፤ ቆላስያስ 118 እርሱ የአካሉ ራስ ነዉ

2.    የክርስቶስ አካል ከአጥቢያ ጉባኤ ይለያል

ከቁጥር በላይ የሆኑ ጉባኤዎች ወይም ቤተክርስቲያናት ለምዕተ አመታት ነበሩ፤ እነዚህም አማኞች እንደሆኑ ነዉ፣የማያምኑ ሰዎችም ወይም ሁለቱንም ያቀፈ ሊሆን ይችላል፤ የክርስቶስ አካል ግን ይለያል፤አንድ አካል ብቻ ነዉ ያለዉ እርሱም የአማኞች ስብስብ ነዉ፤ ከበአለ ሃምሳ ጀምሮ አስከ ንጥቀት ድረስ ያሉ የአማኞች ስብስብ ናቸዉ፤(ሮሜ 741ቆሮ1016 1ቆሮ1227፣ኤፌ 44-612) የክርስቶስ አካል የሚገለጸዉ ከአለም አቀፋዊ ቤተክርስቲያን ጋር ነዉ፤ ይህቺም ቤተክርስቲያን የማትታይ አጠቃላይ እዉነተኛ አባላት ያሉበት ነዉ፤ ለእግዚአብሔር የሚታይ ለሰዉ የማይታይ  ነዉ፤

3.    አካሉ የሚይዘዉ

1ቆሮ1213አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል፤

አካሉ አይሁዶችንና አሕዛብን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የያዘ ነዉ፤

4.    አካሉ ‹‹አዲስ ሰዉ›› ነዉ

ኤፌሶን 211-15 እንደ ክፍሉ አማኝ አይሁዶች እና አማኝ አሕዛብ በክርስቶስ ወደ አንድነት መጡ አንድ አዲስን ሰዉ ፈጠሩ፤

5.    አካል እስራኤልም አሕዛብም አይደሉም

በክርስቶስ ደም የአይሁድና አሕዛብ አንድ መሆን ወደ አዲስ ሰዉነት አመጣቸዉ፤ እነዚህ ሰዎች አዲስን ልደት ያገኙት በዳግም ልደት ነዉ፤ ይህ አዲሱ ሰዉ በጥራትም ሆነ በብዛት ከአህዛብ ወይም ከእስራኤል ይለያል፤ሙሉ በሙሉ አዲስ ህልዉና ያለዉ ነዉ፤ 1ቆሮ 1032 እኔ ደግሞ ብዙዎቹ ይድኑ ዘንድ ለጥቅማቸው እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ እንደማሰኝ፥ ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ።

6.    እንዴት ከጋራ የእስራኤል ብልጽግና የራቁ አሕዛብ አሁን ቀረቡ?

በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁአሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።( ኤፌ 212-13) ይህ ማለት ምን ማለት ነዉ?

ዋናዉ ሐሳብ አሕዛብ ከጋራ ብልጽግና ተገለሉ የሚለዉ ሳይሆን አምላክ ለዉ እስራኤል ሲሆን እነዚያ ግን ከክርስቶስ መለየታቸዉ ነዉ፤

በሁሉም ዘመናት ድነት በእምነት ብቻ ነዉ፤ይህ ደግሞ በሕጉ ዉስጥ እዉነት ነዉ፤ በሕግ ስር ሆኖ ዕንባቆም ሲጽፍ ‹‹ ጻዲቅ በእምነቱ በሕይወት ይኖራል›› ይላል፤( 24) እግዚአብሔር እንድንከተለዉ ሕግን አስቀምጦአል፤ይህም የሙሴ ሕግ ነዉ አሕዛብ እዉነተኛ የሆነ እምነት በእስራኤል አምላክ ላይ ቢኖራቸዉ ኖሮ እና ወደ ሙሴ ሕግ ቢመጡና ቢለወጡ እንደገናም ሕጉን ተቀብለዉ ቢያደርጉት ኖሮ ከእስራኤል የጋራ ብልጽግና ተጋሪ ይሆኑ ነበር፤ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ለፋሲካ ሄዶ ያመልክ ነበር፣ በበአለ ሃምሳና በመገናኛዉ ድንኳኑ ወደ ቤተመቅደሱም መስዋዕት ያቀርባሉ ወዘተ፤ ያለእምነት ሕጉን መቀበል አያድንም፤( እስራኤላዊ ቢሆንም እንዲሁ አይድንም) እዉነተኛ እምነት ያለዉ ሕጉን የሚፈጽመዉ ነዉ፤ በክርስቲያን ሕይወት አዉድ  ያዕቆብ ሲናገር ‹‹ነገር ግን አንድ ሰው፦ አንተ እምነት አለህ እኔም ሥራ አለኝ፤ እምነትህን ከሥራህ ለይተህ አሳየኝ፥ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ ይላል›› ( ያዕ 218) ሕጉ በሚሰጥበትም ዘመን እንዲሁ ተመሳሳይ ድንጋጌ ነበር፤አሕዛብ እዉነተኛ የሆነ እምነት በእስራኤል አምላክ ካላቸዉ ነገር ግን መስቀሉ የሙሴን ሕግ የእስራኤል የጋራ ብልጽግና ማሰብ የሞተ ነገር ነዉ ምክንያቱም የሙሴ ሕግ የጥላቻን ግድግዳ ገንብቶ ነበር፤ አሁን ግን በመስቀሉ ስራ ተሻረ፤ ይህ ዘር ኢየሱስ ለሰማርያዊትዋ ሴት ሲናገር ዮሐ 42123  አንቺ ሴት፥ እመኚኝ፥ በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ለአብ የማትሰግዱበት ጊዜ ይመጣልነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ ለአብ በመንፈስና በእውነት የሚሰግዱበት ጊዜ ይመጣል አሁንም ሆኖአል፤ አብ ሊሰግዱለት እንደ እነዚህ ያሉትን ይሻልና፤

ጳዉሎስ ምን አለ ከመስቀሉ ስራ ጀምሮ አሕዛብ ወደ ድነቱ በረከት ቀርበዋል፤ ወደ እስራኤል የጋራ ብልጽግና አይደለም፤ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ እና በአካሉ በዳግም ልደት አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።( 1ቆሮ1213)

ማጠቃለያ

1.    አዲሱ ሰዉ እስራኤል ወይም አሕዛብ አይደለም

2.    አሕዛብ አማኞች ወደ ድነቱ በረከትና ወደ እስራኤል የጋራ ብልጽግና አልቀረቡም ነበር፤ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ሰዉ ሆኑ፣የክርስቶስ አካል አለም አቀፋዊ ወይም የማይታይ ቤተክርስቲያን ተባሉ፤ 

7.በአካል ዉስጥ ያሉ አባላት ብሔራቸዉና ማንነታቸዉ

ከላይ ያየናቸዉ አይሁድ በደንብ አድርገን ልናብራራቸዉ ያስፈልጋል፤አዲሱ ሰዉ ከእስራኤልና ከአህዛብ የሚለይ ነዉ የአዲሱ ሰዉ አባላት ናቸዉ፤ የአህዛብን ወይም የአይሁድን ማንነት የሚያጠፋ አይደለም የአህዛብም ሆነ የእስራኤል አባል የምትሆነዉ በተፈጥሮ ማንትህ ነዉ፤ የአዲሱ ሰዉ አባል መሆን ግን በዳግም ልደት ነዉ ይህም በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ነዉ፤ በሁለቱ አባላት መካከል ምንም ግጭት የለም፤ ወይም አንደኛዉ አንደኛዉን አያገልም፤ ሐዋርያዉ ጳዉሎስ ራሱን የእስራኤል ወገን አድርጎ ሲሆን ያዉም የብንያም ወገን፣ከዕብራዊም ዕብራዊ (ፊሊ 35) እና በሮም የአሕዛብ አማኞችን ለመድረስ ነዉ (ሮም 1113)

እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በአዉዱ መሰረት ሊታይ ይገባል፤ ስለዚህም እርስ በርሱ አይጋጭም ለምሳሌ ገላ 328 እንዲህ ይላል ‹‹አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና። የዚህን ጽሑፍ አዉድ መረዳት ያስፈልገናል፤›› ክፍሉን ስናይ በአይነት ከአንድ በላይ ናቸዉ በአንድነት ግን ይኖራሉ፤

የክርስቶስ ካል ማለት አንድ አዲስን ሰዉ የያዘ ሲሆን ይህም አሕዛብንና አይሁድን ያቀፈ ነዉ፤ እነዚህ አሕዛብና አይሁዳዉያን ለዘላለም የሚኖሩ ናቸዉ (ራዕይ 212426) በታላቅ ክብር ያረገዉ ኢየሱስ መንፈሳዊና ሰማያዊ አካል አለዉ ( 1ቆሮንቶስ 15 434448) የሚጠራዉም የይሁዳ አንበሳ ተብሎ ነዉ (ራእ 55)

7.    በምን ታሪካዊ ጊዜ ዉስጥ አካሉ የሚሰራዉ?

. መቼ ነዉ መሰራት የሚጀምረዉ?

የክርስቶስ አካል የጀመረዉ በበአለ ሃምሳ ዕለት ነዉ(ሐዋ 2) በዚህ ጊዜ የተገለጠዉ

1.    በመጀመሪያ በኢየሱስ ሞት፣ትንሳኤና እርገት ነዉ አርሱ እንደተናገረዉ ቤተክርስቲያን ወደፊት የምትቀጥል ናት ‹‹እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።›› ( ማቴ 1618)

እንደ / ፍሩችትንባዉም አረፍተ ነገሩ የተመሰረተዉ ግሱ የሚፈታዉ በነበረችዉ ቤተክርስቲያን ላይ ተነስቶ አይደለም፤

2.    1ቆሮንቶስ 1213 አካሉ የተሰራዉ አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቁ በኋላ ነዉ ‹‹አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል››

ከላይ ያለዉን በመጨመር የመንፈስ ጥምቀትን እንመለከታለን፤እርሱም ለአካሉ መፈጠር ምክንያት ነበር ኢየሱስ ከመሞቱ፣ከትንሳኤዉና እርገቱ  በፊት  ተናግሮ ነበር

3.    ከኢየሱስ እርገት በኋላ ደቀመዛሙርት እንዲህ አላቸዉ በመንፈስ ቅዱስ እስክተጠመቁ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ፤ (ሐዋ 11-5)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ኢየሱስ እስኪያርግ ድረስ አልተከናወነም ነበር የአካሉ መፈጠር ወደፊት የሚሆን ነበር፤

ድረስ ይህ ስራ ይቀጥላል፤(ሮሜ 1125) እግዚአብሔር አስቀድሞ የተወሰኑ አይሁድንና አሕዛብን በመጥራት በአንድ አካል ዉስጥ የማጥመቁን ስራ ይቀጥላል፤ የመጨረሻዉ አሕዛብ ከተጨመሩ በኋላ የክርስቶሰ አካል በሙላት ትሰራለች፤

አካሉ መሰራት የጀመረችዉ በበ

ዮሐ 738-39 ኢየሱስ ካረገ በኋላ ስለሚሆነዉ የመንፈስ ጥምቀት መናገሩ ነዉ፤ስለመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በግልጽ አልተገለጸም፤ ይህ ግልጽ የሆነዉ ወደፊት  እርሱ ስለሚሰጠዉ መንፈስ መናገሩ ነዉ፤

4.    አማኞች በበአለ ሃምሳ እለት በመንፈስ ተሞሉ (ሐዋ 21-4) አማኞች በመንፈሰ ቅዱስ የተሞሉት ኢየሱስ ካረገ በኋላ ነበር፤ በመንፈስ ተጠምቀዉ ነበርን? ቃሉ ተመሳሳይ አይደለም እስኪ በጥልቀት እንመልት፡-

5.    ከበአለሃምሳዉ ዕለት 12 አመት በኋላ ቆርኖሌዎስና ቤተሰቡ በመንፈስ ቅዱስ ተጠመቁ፤

በሐዋ 10 ጴጥሮስ በቆርኖሊዎስ አሕዛብ ቤት በመገኘት ቃሉን በሰሙት ሁሉ ላይ መንፈስ ወረደባቸዉ ( .44) በሐዋ 1115-16 ጴጥሮስ በኢየሩሳሌም ጉባኤ ላይ ‹‹ለመናገርም በጀመርሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለእኛ ደግሞ በመጀመሪያ እንደ ወረደ ለእነርሱ ወረደላቸው ዮሐንስ በውኃ አጠመቀ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ ያለውም የጌታ ቃል ትዝ አለኝ።›› ጴጥሮስ የተናገረዉ በቆርኖሌዎስ ቤተ ስለነበረዉ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት ልምምድ ነዉ፤

6.    ጴጥሮስ እየተናገረ ያለዉ የቆርኖሌዎሰ ቤት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በበአለ ሃምሳዉ እለት ኢየሱስ ካረገ በኋላ ጊዜ ከሆነዉ ጋር በማመሳሰል ነዉ፤ በእነርሱ ሕይወት ምን እንደሆነ ተረከላቸዉ፤ በመጀመሪያ በአይሁድ ላይ የሆነዉ ነገር ሁሉ አሁን ደግሞ በአሕዛቡ ላይ ሆነ፤ ይህም በመጀመሪያ በቃሉ በተነገረዉ መሰረት መሆኑ ነዉ ( ሐዋ 15) ዮሐንስ ሲናገር እኔ በዉሃ አጠምቃቸኋለሁ እናንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ፤

(ሐዋ 1 ለሐዋ 2) ዝግጅት ነዉ ስለዚህ ስናጠቃልል  (የሐዋ 2) የክስተቱ መጀመሪያ ነዉ፤ በቆርኖሌዎስ ቤት በመንፈስ ቅዱስ ሲጠመቁ ምን ተከሰተ? ኢየሱስ ካረገ በኋላ በመንፈስ ቅዱስን ሐይል አይሁዶች ሲጠመቁ  ምን ሆነ?

የክርስቶስ አካል፣ የማይታየዉ አለም አቀፋዊ ቤተክርስቲያን ከኢየሱስ እርገት በኋላ ተፈጠረች፤ ስለዚህም አማኞች በመጀመሪያ በመንፈስ ቅዱስ  ይጠመቃሉ፤

. የተፈጠረችዉ አካል መች ታቆማለች?

ከአሕዛብ ወደ ይሁዲነት የገቡ አሕዛብ በመጀመሪያ በበአለሃምሳ እለት ተጠመቁ፤( ሐዋ 2) እግዚአብሔር አሕዛብን ከአለም በመጥራት በኢየሱስ አካል ዉስጥ ያጠምቃል፤(ሐዋ 1514) የአሕዛብ ሙላት እስኪያበቃ

አለሃምሳ ዕለት ነዉ፤ አካሉ የምታበቃዉ የአህዛብ ሙላት ሲያበቃ ነዉ፤

. አካሉ በምድር እስካለች ድረስ

አንዴ የክርስቶስ አካል በሙላት ተፈጥራለች፤ እግዚአብሔር የሞቱ ቅዱሳንን ስጋ ትንሳኤ ይሰጣል፤ የሞቱ ቅዱሳን ሲነሱ በሕይወት ያሉ ደግሞ ይነጠቃሉ(1ቆሮ 1512-57 1ተሰሎንቄ 413-18) ከዚያ በኋላ ሁሉም ከጌታ ጋር ይሆናል( 1ተሰ 417) በክርስቶስ የሆኑ ብቻ ይጨመራሉ፤(1ቆሮ 15181922 1ተሰ416) ‹‹ በክርስቶስ›› የሆኑ ቅዱሳን ሁሉ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ይጨመራሉ፤ በብሉይ ኪዳን ያሉ ቅዱሳን ( ኢሳ 2619 ዳን 122)   በታላቁ መከራ ዉስጥ ያልፋሉ፤ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን (ኢሳ 2619 ዳን 122) በታላቁ መከራ ዉስጥ ያልፋሉ( ራዕይ 204) ወዲያዉኑ በትንሳኤ ይነሳሉ ወይም ወዲዉኑ ከመከራዉ በኋላ የሚሆን ነዉ፤

7.    እስራኤል ከክርስቶስ አካል ትለያለች

የክርስቶስ አካል ዝግጁ ናት፣ አለም አቀፍ ቤተክርስቲያን ይህም ከእስራኤል ትለያለች

·         ከአብርሃም ይስሀቅና ያእቆብ ጀምሮ እስከ ሺኅ አመት መንግስት ጀምሮ እስራኤል በቁጥር እየጨመረች ናት፤ በማነጻጸር የክርስቶስ አካል የጀመረችዉ በበአለ ሃምሳ ሲሆን እስከ ንጥቀት ቀን ድረስ በቁጥር ይጨምራሉ ይህም ከሺ አመተ መንግቱ በፊት ነዉ፤(ሺህ አመተ መንግስት የለም ለሚሉ ሰዎች ወይም ንጥቀት የሚሆነዉ  በመቀጠል ነዉ ለሚሉ እስራኤል የሚጀምረዉ የዚያን ጊዜ ነዉ፤ ቤተክርስቲያን ግን 2000 አመታት ተለይታለች፤

·         አካል የሚለዉ ከእስራኤል ጋር ተመሳሳይ አይደለም ከአሕዛብ ጋር ተመሳሳይ ከሚለዉ በላይ ነዉ፤በብዛትም ቢሆን በጥራት አዲሱ አካል በተምሳሌታዊ ንግግር አዲሱ ሰዉ ተብሏል፤

·         እስራኤል በተፈጥሮ የተገኘ ዜግነት ነዉ አዲሱ ሰዉ መሆን ግን በዳግም ልደት የሚገኝ ነዉ፤ ይህም የሚሆነዉ በመንፈስ ቅዱስ ነዉ፤

·         ከእስራኤል ጋር የተባበሩ አሕዛብ እስራኤላዊ ተብለዉ ግን አልተጠሩም፤ በክርስቶስ ያመኑ አሕዛብ ሆነ አይሁድ መጠሪያ ስሞቻቸዉ አማኞች፣ክርስቲያኖች፣ቅዱሳንና ወዘተነዉ

·         ከበአለ ሃምሳ በፊት ክርስቶስን ያመኑ እስራኤላዉን እነርሱ በታላቁ መከራና በሺህ አመቱ ጊዜ አዲሱ እስራኤላዉያን አማኞች ይባላሉ፤እነርሱ የክርስቶስን መንግስት (ሺህ አመቱን) በረከት ይለማመዳሉ ከዚያም ወደ ዘላለማዊ መንግስት ይገባሉ፤ በቤተክርስቲያን ዘመን ግን ሊሆን አይችልም የቤተክርስቲያን አካል ተብሎም መታሰብ የለበትም፤

·         እስራኤል የተመሰለችዉ በሚስት፣ ከዚያም የፈታች ሚስትና እንደገና የእግዚአብሔር ሚስት የሆነች ናት፤( ኤር3120 ሕዝ 1615) የክርስቶስ አካል ግን  የተመሰለችዉ ለማግባት እንደተዘጋጀች እጮኛ ናት፤ የኢየሱስ ሙሽራ ናት፤ ሁለቱን ተምሳሌቶች በምንም ሁኔታ አንድ ሊሆኑ አይችሉም፤

·         ከሕጉ በታች የሆኑ ጥቂት እስራኤላዉያን መንፈስ ቅዱስ ከእነርሱ ጋር አለ( ከጥቂቶች ጋር ለተወሰነ አላማ ነበር፤ ሁሉም አማኞች ግን ከበአለሃምሳ ጀምሮ እስከ ንጥቀት ጊዜ ድረስ መንፈስ ቅዱሰ አብሮአቸዉ አለ፤ በተጨማሪ መንፈስ ቅዱስ በጥቂት እስራኤል ላይ በዘላቂነት አይኖርም፤(ለምሳሌ 1ሳሙ 1614 መዝ 5111) መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ላሉ ለዘላለም ይኖራል፤ ንጽጽሩ ሶስት ሲሆን ጥቂት፣ሁሉ፣ጋር ዉስጥ፣ በጊዜያዊነት-ዘላለማዊ (ዮሐ 737-3914 16-17 ዘኁ 1117-252718 2ነገ 29-12 1ሳሙ 1614 መዝ 5111)

·          70 እና 135 . የእስራኤል የጋራ ብልጽግና በሮማዉያን ተደመሰሰ፤ የአሁኑዋ እስራኤል 1948. የተመሰረተች ናት የእስራኤል የፖለቲካ ክፍተት 1800 አመታት በላይ የቆየ ነበር፤ ከበአለ ሃምሳ 29 . ጀምሮ  እስካሁን ድረስ አልተሰበረም፤

·         የጥንቱ የጋራ ብልጽግና ከሙሴ ሕግ በታች መሆንን ይጠይቃል የአሁኑዋ እስራኤል ግን በሙሴ ሕግ የምትተዳደር አይደለችም፤ በክርስቶስ ሕግ ነዉ( ገላትያ 62) ወይም ለአማኞች ሌላ ሕግ አለ፤ ቤተክርስቲያን ከጋራ ብልጽግና እስራኤል የተለየች ስትሆን ከሙሴ ሕግ በታች አይደለችም፤ ከዘመናዊዉ እስራኤልም ትለያለች ምክንያቱም ከክርስቶስ ሕግ በታች በመሆኗ ነዉ፤  የክርስቶስ አካል  ቤተክርስቲያን ከጥንትዋም ከአሁኑዋም እስራኤል ትለያለች፤

·         በአካል ዉስጥ ያለች በንጥቀት ጊዜ ትንሳኤን ታገኛለች፤ ይህም ከታላቁ መከራ በፊት የሚሆን ነዉ፤( 1ተሰሎንቄ 52-9 2ተሰሎንቄ 28-13 ወዘተ) ሌሎች ቅዱሳን ግን ከታላቁ መከራ በኋላ ትንሳኤን ይቀበላሉ፤( ኢሳ 2619 እና ዳን 122)

·         በታላቁ መከራ ጊዜ ሁሉም የክርስቶስ አካል በሰማይ ይሆናሉ( 1ቆሮ 1551-52) ነገር ግን በታላቁ መከራ ጊዜ እስራኤላዉያን የሚድኑት ከበአለ ሃምሳ እና በንጥቀት በሰማይ የሚሆኑት ነዉ፤

·         የክርስቶስ አካል ሁሉም በጌታ ፊት ዘላለማዊ በረከትን ያጣጥማሉ ነገር ግን የእስራኤል ቅሬታ የሚድኑ ይሆናሉ ( ኢሳ 19 1022 ሮሜ 927)

. ‹‹በምድረ በዳ  የነበረች ቤተክርስቲያን››

ሐዋ 738 የሚያሳየዉ ከሙሴ በታች የነበሩትን እስራኤል ሲሆን ልክ እንደ በምድረ በዳ ያለች ቤተክርስቲያን 1ቆሮንቶስ 102 ‹‹ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባሕር ተጠመቁ፤›› እስራኤል ከቤተክርስቲያን የምትለይ ከሆነ ለምን ታዲያ እዚህ ቤተክርስቲያን ተባሉ?››

እንደ ስሚዝ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ ‹‹ ኤክሊሽያ ለቤተክርስቲያን የተሰጠ የግሪክ ቃል ነዉ ትርጉሙም ሕጋዊ ስልጣን ከተሰጠዉ አካል ተጠርተዉ የወጡ ሰዎች ጉባኤ›› ማለት ነዉ፤

የግሪኩ ቃል ቤተክርስቲያን ማለት ጉባኤ ማለት ነዉ፤ ሕጋዊ ስልጣን ያለዉ አካል እስራኤልን ከሕዝብ ሁሉ ዉስጥ ጠራ የአማኞች አካል ደግሞ ከአለም ሲስተም ዉስጥ በተመሳሳይ መልኩ ተጠርተዉ ወጡ፤ እስራኤላዉያን በምደረበዳ በነበሩ ጊዜ ጉባኤ ነበሩ ይህም በተፈጥሮና በአካል  ያገኙት ሥፍራ  ነዉ፤ የክርስቶስ አካል /ጉባኤ/ ግን በመንፈስ ቅዱስ ጥሪና ድርጅት የሆነ ነዉ፤ ጉባዔ የሚለዉን ቃል ለጂሆቫ ዊትነስ የሚሰጥ አይደለም የአይሁድ መከላከያ ሊግ ተመሳሳይ ቡድን የሚጠቀም ሲሆን ምክንያቱም እያንዳንዳቸዉ ቡድኖች ስለሆኑ ነዉ፤ በተጨማሪ ከጥምቀት በኋላ ያለዉ ሐሳብ መለየት ነዉ፤አንድ እስራኤላዊ ከሙሴ ወይም ከእስራኤል ጋር ለመመሳሰል አይጠመቁም፤ እነርሱ በትዉልድ እስራኤላዉያን ናቸዉ፤ ከሙሴ አመራርም የተለዩ ናቸዉ ከግብጽ ወጥተዉ ቀይባህርን ሲሻገሩ ነጽተዉ ነበር፤ በቀይ ባህር ዉስጥ አልተጠመቁም፤(ዘጸ 1416-29) የደመናዉ አምድ ሲያዩ እሰራኤላዉያን እየተመሩ እና እየተጠበቁ መሆናቸዉን የሚረዱበት ነዉ፤ ይህ ድንቅ ምሳሌ ነዉ ደመናዉ እስራኤልን ወደ ቀይ ባህሩ ይመራቸዉ ወደፊት ይሄድና በዙሪያቸዉ  ከፈረኦን ሰራዊት ይጋርዳቸዉ ነበር፤( ዘጸ 1321-221419)

እስራኤልና የክርስቶስ አካል ሁለቱም በእግዚአብሔር እቅድ ዉስጥ በተለያየ ጎዳና ላይ ብዙ ልዩነት ያላቸዉ ናቸዉ፤ አንድና ተመሳሳይ አይደሉም፤የሚገናኙበት ጊዜ አለ፤ የአይሁድ አማኞች ከበአለ ሃምሳ እለት ጀምሮ እስከ ንጥቀት እለት ከክርስቶስ አካል ጋር የእስራኤል አባላት ናቸዉ 

. እስራኤልና  አካሉ ሲጠቃለል

1.    የክርስቶሰ አካል፣ ቤተክርስቲያን እስራኤል አይደለችም  ወደ እስራኤልም አትደመርም ትለያለች፤

2.    በአካል ዉስጥ አባል መሆን ማለት ዜግነትን ማጥፋት ማለት አይደለም፤ አይሁድ አይሁዳዉያን ይሆናሉ አሕዛብም አሕዛብ ሆኖ ይቀጥላል፤                                               

እንደ እስራኤል ቤተክርስቲያንም የተመረጠች ናት የተመረጠ ሕዝብ የእግዚአብሔር ሕዝብ ነዉ፤ በእግዚአብሔር እቅድ ሲታይ ግን ሁለቱም በተለያየ መንገድ ላይ ያሉ ናቸዉ፤ሁለቱ የተለያዩ ማንነቶች በሁለት መንገዶች ላይ አሉ ይህን የእዉነት ቃል መከፋፈል አንችልም በግራ መጋባት ላይ ግራ መጋባት ሊያደርስ ይችላል፤

8.    የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ከእስራኤል ትለያለችን?

ከላይ ያየነዉ የማትታየዋ ቤተክርሰቲያን ከእስራኤል እንደምትለይ ነዉ

. የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ምንድን ናት?

የምትታየዋ ቤተክርሰቲያን የማትታየዋን የምትቃረን ናት፤የማትታየዋ ቤተክርስቲን አማኞችን ብቻ የያዘች ስትሆን የምትታየዉ ግን አማኞችንና አላማኞችን የያዘች ናት፤ የማትታየዋ ቤተክርስቲያን አባል የሆኑ እዉነተኛ አማኞች ሲሆኑ ልብን ሁሉ የሚመረምረዉ አምላክ ብቻዉን የሚያዉቃት ነዉ፤ያላመኑ ሰዎች ቤተክርስቲያን ሊገቡና አማኝ ነን ብለዉ ሊናገሩ ይችላሉ፤ የማትታየዋም የምትታየዋም ቤተከርስቲያን የጀመሩት በበአለ ሃምሳ እለት ነዉ፤

የእስራኤልና የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ልዩነት

የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ከእስራኤል ትለያለች የምትመሳሰልበት ጊዜም አለ በዚህም የማትታየዋ ቤተክርስቲያን፡

·         እስራኤል የተጀመረዉ በአብርሃም፣ይስሀቅና ያዕቆብ ነዉ፤ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ግን 2000 አመታት በኋላ በበአለ ሃምሳ ዕለት ነዉ፤

·         እስራኤል የተሰራችዉ በእስራኤላዉያን ነዉ የማትታየዋ ቤተክርስቲያን ግን አሕዘብንና አይሁድን የያዘች ናት፤

·         አሕዛብ ሆነዉ ወደ እስራኤል ምድር የገቡ እስራኤላዉያን ተብለዉ አልተጠሩም ምክንቱም ስላልሆኑ ነዉ፤በተመሳሳይ መልኩ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን አሕዛብን አቅፋ የያዘችዉም ብትሆን እስራኤል ወይም የእስራኤል አካል ተብለዉ አይጠሩም፤

·         18 አመታት በፊት በእስራኤል ፖለቲካ ታሪክ ዉስጥ ክፍተት ነበረ፤ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን  ከበአለ ሃምሳ እለት ጀምሮ 29. ያልተቋረጠ ገንኙነት አለ፤

·         የጥንትዋ እስራኤል በሙሴ ሕግ ስር የምትተዳደር ሲሆን ዘመናዊዋ እስራኤል ግን እንዲህ ያለ ሕግ የላትም፤ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ደግሞ ከሁለቱም ትለያለች የምትተዳደረዉም በክርስቶስ ሕግ ሥር ሆና ነዉ፤

. ማጠቃለያ

መፅሐፍ ቅዱስ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን ከእስራኤል ጋር ተመሳሳይ ናት አይልም፤ ወይም ከእስራኤል ጋር ተዋህዳለች አይልም፤ የተሰጠዉም ምክንያት ሊሆን አይችልም፤ የማትታየዋ ቤተክርስቲያን እና እስራኤል የተለዩ አካላት ናቸዉ፤ በተጨማሪም የምትታየዋ ቤተክርስቲያን እና እስራኤል እንዲሁ የተለያዩ አካላት ናቸዉ፤

ወደፊት በሚደረገዉ ጥናት ቤተክርስቲያን እንዴት እስራኤልን እንደተካች እናያለን፤ እስራኤል ስንል መንፈሳዊዉን ወይም ተምሳሌታዊ ንግግር ነዉ፤ አይሁድና የአካሉ አባላት በአንድ ጊዜ እንዴት ነዉ ልዩ የሚሆኑት፤

የእስራኤል መመረጥ

1.    መግቢያ

በመጀመሪያዉ ክፍል እንዳየነዉ እስራኤልንና ቤተክርስቲያነ በአንድ ጊዜ አንድ ሊሆኑ እንደማይችሉ ነዉ፤ በምንም ምክንያት አሕዛብም ሆነ አይሁድ ዜግነነታቸዉን ሊያጡ አይችሉም፤ ኢየሱስ እንዳለዉም አይሁድ ግን አይሁድነታቸዉን በደምና ስጋ እንደሚያገኙ ብዙ ምስክሮች አሉን፤ ደቀመዛሙርቱና በዚያ ዘመን የሚኖሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የሚረዱት እንዲህ ነዉ፤

ስለቤተክርስቲያን ጠቃሚ የሆኑ ነጥቦች ይነሳሉ የተለያዩ ጥያቄዎች እንደሚከተለዉ ይቀርባል፤አሕዛብ ማለት ከጠፉ ከአስሩ ነገዶች ጋር ተደምረዉ እስራኤላዉያን መባል አይችሉምን? ቤተክርስቲያን እስራኤልን ተክታለችን? ወይም መንፈሳዊ እስራኤል መባል ትችላለችን? አዲሱ እስራኤል መባል የሚያስችላት ሁኔታ አለን? በተምሳሌታዊ ንግግር እስራኤል ያስብላታልን? ያመኑ አሕዛብ መንፈሳዊ አይሁዳዉያን ያስብላቸዋልን? በሚቀጥሉት ክፍሎች ዉስጥ እነዚህን እንመረምራለን፤ ከማድረጋችን በፊት ስለ እስራኤል መመረጥ የሚናገሩ ልናደርግ የሚገባን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እናያለን፤ ይህም የእግዚአብሔርን ሐሳብ እናያለን፤ይህንን የምናየዉ የቤተክርስቲያንን መመረጥ ለማግለል ወይም ለማቅለል አይደለም፤ የእስራኤልን የመመረጥ ዓላማ ለመገምገምና እና ሁለቱ እንዴት አንድ ላይ እንደሆኑ ለማወቅ ነዉ፤

አብዛኛዉ የምናነሳዉ ነጥብ የምንደርሰዉ ዋናዉን ጉዳይ ወይም ከዋናዉ ሀሳብ ቀጥሎ ያሉትን ጉዳዮች እናያለን፤

2.    የኤኤምሲ ጽሑፍ በእስራኤል ላይ

እስራኤል የእግዚአብሔር ልዩ ሕዝብ እንደሆነ እናምናለን፤ ከክርስቶስ አካል ግን ይለያል፤ በእርሱ የተመረጡ ቅዱስ ሕዝብ እና የንጉስ ካህናት  ናቸዉ፤ በክርስቶስ ያመኑ አይሁዳዉያን ሁለት ልዩ ማንነት አላቸዉ፤ እነዚህ መንፈሳዊ ቅሬታ ያላቸዉ እስራኤል በተመሳሳይ የክርስቶስ አካል ናቸዉ፤ የአብርሃም ኪዳን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እግዚአብሔር ከአይሁድ ጋር ያደረገዉ ኪዳን ነዉ፤ ይህ ኪዳን ለእስራኤል ምድር 29-10 1ጴጥ 29-10 እንመለከታለን፤ በተለያዩ እትሞች ላይ የተመረጠ የሚለዉ ቃል በልዑል እግዚአብሔር የተመረጠ መለኮታዊ አላማና በረከት ያለዉ ነዉ፤

5.    የእግዚአብሔር አላማ ለእስራኤል መመረጥ

ተስፋዉም ለዘራቸዉ (ለመሲሁ) ነዉ፤እርሱ እስራኤልን ይቤዣል ከዚያም አለምን ሁሉ ይባርካል፤ የአብርሃም መንፈሳዊ በረከት ለሁሉም ሕዝቦች የሚደርስ ነዉ፤ እግዚአብሔርም በመጨረሻ የክርስቶስን ሺህ አመተ መንግስት ጊዜ ኪዳን በስጋም በመንፈስም ይፈጽማል፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባዉ ዘላለማዊ የስርየት ኪዳን ማለት እንዳንዱ እሰራኤል ለመዳኑ ዋስትና አይሰጥም፤ ስለዚህ አማኞች መልካሙን ዜና ለእንዳንዱ አይሁድ ማድረስ አለባቸዉ( ዘፍ 121-3 151-21171-21 ሮሜ 111-29 ገላት 314-17)

3.    ወርቃማዉ ሕግ እና ትርጉሙ

አንዱ አስፈላጊዉ የመጽሐፍ ቀዱስ ትርጉም መታሰብ ያለበት ወርቃማዉን ሕግ መተረጎም ነዉ፤

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የጋራ ሐሳብ ቢኖረዉም ሌላ ሀሳብ የለዉም፤ስለዚህ የተጻፈበትን ቃል ትርጉም፣ ሁልጊዜ፣ እና አዉዱን የተጻፈበትን ምክንያት ከላይና ከታች ያለዉን ጽሑፍ ካልተረዳን ወደ ተክክለኛዉ ትርጉም ልንደርስ አንችልም፤

መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የጋራ ሐሳብ ቢኖረዉም ሌላ ሀሳብ አትፈልግ፤ ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱሰ እንዲህ ይላል‹‹እስራኤል›› ይህ ማለት ብሔራዊ እስራኤልን ነዉ ካልሆነ ግን መልካም እና ምክንያታዊ የሆነ ትርጉም ያስፈልጋል፤

4.    የእስራኤል የመመረጥ እዉነት

በዘዳግም 76 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ፤

ልዩ ሕዝብ የምትለዉን ሐረግ እናያለን ‹‹ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት›› የእብራይስጡ ቃል ‹‹ሲጉላህ›› የሚል ሲሆን ጠንካራዉ ትርጓሜ ልዩ የሚል ነዉ፤

ሌሎቹ ስለምርጫ የሚናገረዉ ክፍል ዘዳ 142 1ዜና 1613 መዝ 3312 1056431065 1354 ኢሳ 418-9431020441-2454 አሞጽ 32 1

መመረጥ አላማ ያለዉ ነዉ ከላይ ባሉ ክፍሎችና ሌሎች ክፍሎች ዉስጥ እንዳየነዉ እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠበት ምክንያት እንደሚከተለዉ ጠቅለል ተደርጎ ይቀርባል፤

·         ለእርሱ ቅዱስ ህዝብ እንዲሆኑ ዘጸ 196 142 ወዘተ መቀደስ የሚለዉ ቃል መለየትን፣መሰጠትን፣ንጹህ መሆንን የሚያሳይ ነዉ፤ ዘጸ196 ‹‹እናንተም የካህናት መንግሥት የተቀደሰም ሕዝብ ትሆኑልኛላችሁ። ለእስራኤል ልጆች የምትነግራቸው ቃል ይህ ነው››

·         የእርሱ ርስት፣ልዩ ሀብት ዘጸ195 ዘዳ42076 142 መዝ 1354 ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ(መዝ 241) ከብዙ ሕዝብ መካከል እስራኤል በእግዚአብሔር ተመረጠች የእርሱ ልዩ ሐብት (ዘጸ 195)

·         የእርሱ ባሪያ እንዲሆኑ ኢሳ 4189441221 65915 ኤር 3010462728

·         የእርሱ ርስት  እንዲሆኑ ዘዳግም 926329 መዝ 3312742786271 9461065 ኤር 1279

ርስት ማለት በእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ያለዉ ትርጉም አንድ ዋጋዉ ዉድ ሆነ ርስት ለተወሰነ ሰዉ ወይም ቡድን መስጠት ማለት ነዉ፤( ኢያሱ 141-15 በተለይ 13) ሌለኛዉ ትርጉም ባለቤቱ ርስቱን ትቶ ሲሞት የቅርብ የሚባለዉ ሰዉ የሚወርሰዉ ነዉ፤( ዘኁ 277) እንደመጀመሪያዉ ትርጉም እስራኤል የእግዚአብሔር ርስት ናት ኢየሱስን አሁን ቢገድሉትም ወደፊት ሁሉም እስራኤል ይድናል (ሮሜ 1126)

ይህ ማጠቃለያ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚደግት ነዉ 1ጴጥ 29 ብዙ ማስረጃዎች እንደሚሉት ጴጥሮስ የጻፈዉ ለአይሁድ አማኞች እንደሆነ ነዉ የተመረጡ ሕዝቦች፤ ቃሉ የመጣዉ ከዘጸ196፣ዘዳ 761015 ኢሳ 4216 4320 እና 616 ሌሎቹን ነጥቦች በግርጌ ማስታወሻ ይመልቱ፤

6.    ለተመረጠችዉ እስራኤል አቅርቦት

ስለ ተመረጠችዉና ስለተመሰረተችዉ እስራኤል እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ስላደረገዉ አምስት ኪዳኖች እናያለን፤ አንዳንዶች እንደሚምኑት ይህ ኪዳን ለቤተክርስቲያን ነዉ ይላሉ፤ከዚህ በታች ሉትን ነገሮች በግልጽ እንመልከት፤

1.    1ቆሮንቶስ 1032 እንደሚያሳየዉ እስራኤል፣ አሕዛብና ቤተክርስቲያን ሶስቱ የተለያዩ ቡድኖች መሆናቸዉን ነዉ፤ ‹‹ለአይሁድም ለግሪክም ሰዎች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንም ማሰናከያ አትሁኑ››

2.    ጳዉሎስ ስለኪዳኑ በአዎንታዊና በአሉታዊ መንገድ ሲያረጋግጥ እናያለን፤ በሮሜ 93-4 ይህ ኪዳን በቀጥታ ከብሔራዊ እስራኤል ጋር እንደሆነ ሲናገር ‹‹በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርና።እነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና››  አሉታዊ የሆነ ንግግሩ ደግሞ አሕዛብን በተመለከተ ‹‹ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ››  (ኤፌ 211-12) ትኩረት የሚያደርገዉ በተረሱት አሕዛብ ላይ ሲሆን ለተስፋዉ ኪዳን እንግዶች የሆኑ ናቸዉ፤

የኪዳኑን ቅደም ተከተል ስነመለከት ከአብርሃም ጋር( 1900 //) የሙሴ ኪዳን (1450 .) ከምድር ጋር (1400.) ከዳዊት ጋር(1000.) እና አዲሱ ኪዳን (600.) ኪዳኖቹ ሁለት ዓይነት ናቸዉ፤ በሁኔታ ላይ የተመሰረቱ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረቱ ናቸዉ፤ የሙሴ ሕግ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ሲሆን በእስራኤል ታማኝነት እና ለእግዚአብሔር መታዘዝ ላይ ያተኮረ ነዉ፤

ሁለቱ አይነት ኪዳኖች በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ዉስጥ የተለያዩ ናቸዉ በሮሜ 94 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተዉ ኪዳን ኪዳናት መካከል የሚታይ ሲሆን በሁኔታ ላይ የተመሰረተዉ ኪዳን የሙሴ ሕግ ሆኖ በተሰጠዉ ሕግ ላይ የተመሰረተ ነዉ፤ በኤፌ 211-16 በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተዉ ኪዳን የተስፋዉ ኪዳን/ቃል) ሲባል (.12) የሙሴ ኪዳን ግን የጥልን ግድግዳ የሰራ ነዉ የትዕዛዛት ሕግ የያዙት በመመሪ ነዉ( .14-15)

የአብርሃም ኪዳን የመጀመሪያዉ ኪዳን ሲሆን እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የመሰረተዉ ለሌሎቹ አራቱ መሰረት ነዉ፤

7.    የኤኤምሲ ጽሁፍ በአብርሃም ኪዳን ላይ

የአብርሃም ኪዳን የማይለወጥ፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እግዚአብሔር ከአይሁድ ጋር የገባዉ ኪዳን  እንደሆነ እናምናለን፤ኪዳኑም ለአይሁድ ሕዝብ ተስፋንና ለዘሮቻቸዉ( መሲሁ) ሲሆን እርሱም ወደፊት የሚመጣዉ  እስራኤልንና መላዉን አለም የሚቤዥ እንደሆነ ነዉ፤

8.    የአብርሃም ኪዳን

እግዚአብሔር ከአብርሃም ጋር ኪዳን አደረገ (ዘፍጥረት 121-371314-17151-21171-212215-18) ይህም ወደ አብርሃም ልጅ ይስሀቅ አለፈ( ዘፍ 262-524) ከዚያም ወደ ይስሀቅ ልጅ ያዕቆብ ( ዘፍ 2813-15) ስሙ እስራኤል ተባለ( ዘፍ 3228) የተስፋዉ ኪዳን በጽኑ መሰረት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሁሉም ኪዳናት በመጀመሪዉ ገጽ ላይ አለ ዘፍጥረት 121-3)

እነዚህ ቁልፍ የሆኑ የእግዚአብሔር አቅርቦቶች ናቸዉ፤

·         አብርሃምን ታላቅ ሕዝብ ማድረግ ( ዘፍ 1221316 155 171-27 2217)

·         የከነዓንን ምድር ለእርሱና ለዘሮቹ መስጠት ይህም በይስሀቅና ያዕቆብ፣ ከአካባቢዉ ተባረዉ ወጡ( ዘፍ 12171314-171517-211718)

·         የአብርሃም ዘሮች በግብጽ ባሪያ ሆኑ 400 ዓመታት በኋላ ነጻ ወጡ( ዘፍ 113-14)

·         የምድር ነገዶች ሁሉ በአብርሃም ይባረካሉ(ዘፍ 1232218)

·         አብርሃምን የሚባርኩ ይባረካሉ የሚረግሙት ይረገማሉ (ዘፍ 123)

የመጨረሻዉ የተስፋቃል አንዳንዶችን በአብርሃም ላይ ወይም በሁሉም ሕዝብ ላይ ሲተገበር ሊያስደንቅ ይችላል፣ ለአብርሃም ብቻ የሚሆን ቃል ሳይሆን ( ዘፍ 1210-17201-318) ነገር ግን በተመረጡት ሁሉ ላይ ነዉ፤ እግዚአብሔርም ኪዳኑን ወደ ይስሀቅ፣ያዕቆብ እና ለሁሉም እስራኤል አስተላለፈዉ፤ዓላማዉም አለምን ሁሉ በእርሱ በኩል መባረክ ነዉ፤ይህ ደግሞ በሚባርኩትና በሚረግሙት መካከል ታይቷል ለምሳሌ ጲጥፋራ ዮሴፍን ሲባርክ (ዘፍ 391-5) ሐማ መርዶክዮስን ረገመ (አስቴር 925) በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንደ አገር (ዘካርያስ 28 ማቴዎስ 2531-46 በተለይ 4045 እና በድህረ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ

·         ግርዘት የኪዳኑ ምልክት ነዉ (ዘፍ 179-14)

. በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተዉ የአብርሃም ኪዳን

እግዚአብሔር ምንም ሁኔታን አላስቀመጠም ወይም እንደ አገር ኪዳኑ እንዲፈጸም ቅድመ ሁኔታን አላስቀመጠም ያለ ቅድመ ሁኔታ ኪዳኑን ሰጠ አጸናለትም (ዘፍ 15)

እንደ አገሩ ልማድ ኪዳን ሲፈጸም እንስሳ ይታረድና ለሁለት ይከፈላል ደሙ በመፍሰሱ በሁለቱ ሰዎች ወይም ፓርቲዎች መካከል ጽኑ የሆነ ኪዳን መደረጉን የሚያመለክት ነዉ፤ እግዚአብሔር ለአብርሃም ኪዳኑን ሲያጸና በአንድ አካል በኩል ብቻ የጸና ነዉ እግዚአብሔር ብቻዉን ታየ፤ 17 ‹‹…የምድጃ ጢስና የእሳት ነበልባል በዚያ በተከፈለው መካከል አለፈ።›› ይህ የሚያሳየዉ የኪዳኑ ፈጻሚ በራሱ ታማኝነት እና መለኮታዊ ባህርዩ  ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማመልከት ነዉ፤

. ለሌሎቹ ኪዳኖች መሰረት ነዉ፤

የአብርሃም ኪዳን ለሌሎቹ ሶስቱ  በሁኔታ ላይ ላልተመሰረቱ ኪዳኖች መሰረት ነዉ፤ የሙሴ ሕግ የአብርሃምን ኪዳን በልዩ ሁኔታ ያገለግላል፤ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረቱት ኪዳናት የአብርሃምን ኪዳን በማብራራት እና የሙሴ ኪዳን ደግሞ እስራኤል ከአለም ሕዝብ ለእግዚአብሔር የተለየች ለመሆንዋ ራስዋን ከክፉ ዉጫዊ ተጸዕኖ እንድትጠብቅ የተሰጣት ኪዳን ነዉ፤በመጀመሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተዉን ኪዳን እንገመግምና በመቀጠል የሙሴን እናያለን፤

9.    የምድር ኪዳን

የምድር ኪዳን ያለዉ (በዘዳ 291-3020) ነዉ፤ ይህ ብዙ ጊዜ የፍልስጥኤማዉን ኪዳን ይባላል ምክንያቱም እስራኤል ነጻነትዋን እስካወጀችበት እስከ 1948 . ማለት ነዉ፤ (ምድሩ የፍልስጥኤም ግዛት ነዉ) እንዲህ ተብሎ የተጠራበትም ምክንያት የሮሙ ንጉስ ሐርዲያን የባርኮባንን አመጽ 135. ካሸነፈ በኋላ ነበር፤ በመጽሐፈ ቅዱስ ዉስጥ የፍልስጥኤማዉን ምድር ተብሎ አልተጠራም፤በቅርብ ጊዜ ሰዎች አይሁድን ከመለኮታዊ የተሰፋ ምድራቸዉ  ለማዉጣት ሲፈልጉ የሚናገሩት ነዉ፤ስለዚህ የተሳሳተ መረዳት እንዳይኖር የዶ/ ፍሩችባሁምን ንግግር ‹‹የቃል ኪዳን ምድር›› የሚለዉን እንወስዳለን፤

ስለ ቃልኪዳንዋ ምድር አቅርቦት ከዚህ የሚከተሉትን እናያለን

·         እስራኤል የሙሴን ባይታዘዙ ይበተናሉ ዘዳ 292-301 በተለይ 292028301

·         እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ሲመለሱ ዘዳ 303

·         መሲሁ ይመለስላቸዋል (ዘዳ307) እና

·         ከምድር ሁሉ ይሰበስባቸዋል ከዚም ይባርካቸዋል ዘዳ 303-58-9

የምድር ኪዳን አንዱ እነርሱ ወደ ጌታ ሲመለሱ  እስራኤል እንደ አገር ትሰበሰባለች፤ይህ የሚያብራራዉ እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባዉ የምድር ተስፋ እንደገና ሲያጸና ነዉ፤ ሲያምጹ ይበተናሉ ሲመለሱ ይሰበሰባሉ፤ ይህ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ኪዳን ነዉ እግዚአብሔር ያመጣቸዋል፤

10 የዳዊት ኪዳን

የዳዊት ኪዳን ቃላቶቹን ስናይ በነብዩ ናታን በኩል ለንጉስ ዳዊት ሲናገር 2ሳሙኤል 711-16 እና 1ዜና 1710-14

ቁልፍ የኪዳኑ አቅርቦት እንደሚከተለዉ እናያለን እግዚአብሔር ለንጉሱ የገባዉ፤

·         ዘላለማዊ መንግስት( 2ሳሙ 71116 1ዜና 1710-14) የዳዊት ቤት የንጉሱ የዘር ሐረግ አያቆምም

·         የዳዊት ዙፋን ዘላለማዊ ነዉ ( 2ሳሙ71316)

·         መሲሁ የተወለደዉ በዳዊት የዘር ሐረግ ዉስጥ ነዉ(1ዜና 1711) እና

·         የመሲሁ ቤት….መንግስት….ዙፋኑ ዘላለማዊ ነዉ (1ዜና 1714)

በሌላ ቃላት እግዚአብሔር ለዳዊት የገባዉ ኪዳን ዘላለማዊ መንግስት፣ዙፋን፣ ዘር እና መንግስት ናቸዉ

በተዘዋዋሪ እግዚአብሔር ለአብርሃም ኪዳን ሲገባ በአንተ የምድር ነገዶች ሁሉ ይባረካሉ፤ ( ዘፍ 123) የመሲሁ መምጣት በአብርሃም የዘር ሀረግ ላይ ነዉ አብርሃም ለእግዚአብሔር እንዲህ አለ ‹‹ልጅ የለኝም›› ( ዘፍ153) እግዚአብሔር ዘር በይስሀቅ በኩል እንደሚሰጠዉ ቃል ገባ፤ ይስሀቅ ብቸኛ ልጅ ሲሆን እስራኤል ግን 12 ልጆች ነበሩት፤እነርሱም 12 ነገዶች ሆኑ፤ በዘፍ 4910 የመሲሁ የዘር ሐረግ ጠበብ ካለዉ ከይሁዳ ነገድ ሆነ፤ ከሺህ አመት በኋላ በዳዊት ኪዳን ኢየሱስ ከይሁዳ ነገድ መጣ ስለዚህ የዳዊት ኪዳን የሚያብራራዉ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጠዉን ኪዳን ለማጽናት ነዉ፤መሲሁ የመጣዉ ከዳዊት የአብርሃም ዘር ነዉ፤

የአብርሃም ኪዳን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዳዊት ኪዳን ደግሞ የአብርሃምን ለማጽናትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆኑን ለማረጋገጥ ነዉ፤

10. አዲሱ ኪዳን

የአዲሱ ኪዳን ማዕከል ኤርምያስ 3131-34 ላይ ነዉ

ይህን አስታዉሱ፡-

1.    እንደግለሰብም ሆነ አገር ምንም ቅድመ ሁኔታ የለም፤ያለቅድመ ሁኔታ በሁሉም አቅጣጫ ይፈጸማል

2.    እየሆነ ያለ ነዉ ዘላለማዊ ኪዳን ነዉ ተስፋዉ ሊፈጸም የሚችል ነዉ .34

3.    አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ( .31) ወደፊት የሚሆን ነዉ ኪዳኑ ሲነገር አቅርቦት እንዳለዉ እናያለን፤ በዚህ ግን አልሆነም፤ ይህ በመስቀል ላይ በእግዚአብሔር በራሱ በልጁ  የተፈረመ ነዉ፤ኢየሱስ እንዳለዉ ‹‹ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን አዲስ ኪዳን ነው።››( ሉቃስ 2220) እና ዕብ 81-1018 በተለይ 914-16)

4.    የኪዳኑ ተመርቆ መከፈት ከሃምሳ ቀን በኋላ ለቤተክርስቲያን መፈጠር ምክንያት ሆኗል፤ ከቤተክርስቲያን ጋር የተደረገ አይደለም፤ ከእስራኤል ቤት ከይሁዳ ቤት ጋር የተደረገ ነዉ( .31) ይህም ከመላዉ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ነዉ፤

የትንቢተ ኤርምያስ 31 መልእክት ማረጋገጫነቱ በኢሳይስ 533 5921618-96622፣ኤር3240 ሕዝ16603425-31 3726-28 እና ሮሜ 1126-27

 የአዲሱን ኪዳን ቁልፍ አቅርቦት በተመለከተ፤

·         ዋናዉ አቅርቦት ለድነት ዋስትናን መስጠት ነዉ፤ ጳዉሎስ በሮሜ 1126 ላይ እንዳለዉ ‹‹እስራኤል ሁሉ ይድናል›› ይህ ማለት በታላቁ መከራ መጨረሻ ላይ በሕይወት ያሉ እያንዳንዱ አይሁድ ሁሉ ይድናሉ (ኢሳ591-21 ሕዝ 2038 ዘካ129-10 1318-9)

·         የሙሴ ሕግ እንሰሳትን በእምነት መስዋእት ሲያቀርቡ የሕዝቡን ሐጢአት የሚሸፍን ከሆነ ይህ አዲስ ኪዳን ደግሞ የሐጢአትን ይቅርታ የሚያስገኝ ነዉ(.34)

·         እግዚአብሔር በእያንዳንዱ እስራኤል ልብ ዉስጥ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚያድር ኪዳን ገብቷል(.33)  የሙሴ ሕግ ያላዘጋጀዉን የእግዚአበሔርን ፈቃድ እንዲያደርጉ ነገራቸዉ( ሮሜ 18-4)

·         እስራኤል በብዙ ቁሳቁስ በረከት ትባረካለች ኢሳ 618 ኤር 3241 ሕዝ 3425-27

·         የሙሴ ኪዳን ለአማኞቹ ስለ ባህርይ እንደደነገገ እንዲሁ አዲሱ ኪዳንም ደንግጓል፤ እርሱም እንዲህ ተብሎ ይጠራል ‹‹በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና›› ሮሜ82  የክርስቶስ ሕግ (ገላ62) የሙሴን ሕግ አስርቱን ትዕዛዛት ተክቷል፤ ሞራላዊ የሆኑ ጉዳዮችን ሁሉ፣ስነምግባርን እና በቤተክርስቲያን ዘመን ያለዉን ልምምዶች ያካተተ ነዉ፤

የእስራኤልን ድነት በተመለከተ እግዚአብሔር ለአብርሃም የገባዉ ኪዳን ነዉ፤ ‹‹የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ›› (ዘፍ 123) በመጨረሻም ይፈጸማል( ኢሳ 616 ዘካ 820-23 ሮሜ 1115) ፍጻሜዉ ተጀምሯል( ማቴ 2819)፤የተሰቀለዉና ከሞት የተነሳዉ ክርስቶስ ብዙዎችን በምድር የሚኖሩትን ቤተሰብ ሕይወት የነካ ሲሆን እስካሁን ግን ሁሉም ግን አልተነኩም፤ ይህ በሚጻፍበት ጊዜ በአሜሪካ የሚሲዮናዊ ተልእኮ ያለዉ የጆሽዋ ፕሮጄክት 6760 በወንጌል ያልተደረሱ ነገዶች እንዳሉና በዓለም ላይ 16467 ነገዶች በወንጌል ያልተደረሱ መሆናቸዉን አሳይቷል ይህም  ወደ 41% መሆኑ ነዉ፤

ሁሉም አስተማሪዎችና ማብራሪያ የሚሰጡ ሰዎች አዲሱ ኪዳን የሚጀምረዉ ከቁ.31 እስከ 34 ድረስ መሆኑን ይናገራሉ፤ እንደዛ አልረዳም፤እኔ እንደምረዳዉ እስከ ቁጥር 37 ድረስ ይደርሳል፤

.35-37

ሕዝቡ ምንም ይሁን ምን እግዚአብሔር ከእስራኤል ፊቱን አልመለሰም፤ ከዚህ በፊት በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ኪዳን ስለነበረዉ እንደ አገር ልትኖር ችላለች ምክንያቱም የተመረጠች ናት፤ተስፋዉም የሚባርኩህን እባርካለሁ የሚረግሙህ እረግማለሁ የሚለዉ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደ አገር እና ሕዝብ የሚመለከት ነዉ፤ ለምሳሌ ዘፍ 121-17 እግዚአብሔር ፈርዖንን ረገመ ዘፍ 121-2 የአብርሃምን ሚስት አቤሚልክ በወሰደ ጊዜ እግዚአብሔር ረገመዉ፤  ይህን ተስፋ ሲገባ የአብርሃም ልጅ ይስሀቅ አልነበረም የእስራኤል ሕዝብም አልነበረም አልተወለደምም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እስራኤል በሌሉበት ስፍራ ባረካቸዉ፤ እስራኤል ግን ተቆረጠች፤

ኢሳይያስ ስለ ሕዝቡ መቀጠል ሲናገር ‹‹እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፡›› (ኢሳ 6622)

11 የሙሴ ኪዳን

አራቱን በሁኔታ ላይ ልተመሰረተ ኪዳን ስንመለከት የሙሴን ኪዳን እናያለን፤

. የሙሴ ኪዳን ባህርይ

የሙሴ ኪዳን በዘጸ 201 እና በዘዳ 2868፤መካከል ላይ የሚገኝ ነዉ፤ ስድስት መቶ አስራ ሶስት ትዕዛዛት  የያዘ ሲሆን አስሩን እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠዉ በሲና ተራራ ሲሆን ሰድሰት  መቶ ሶስቱ ግን ሕዝቡ በምድረበዳ በመንከራተት ላይ ሳሉ ነዉ፤ከሕግ አንዱ ቢያሰናክል በሁሉ እንደተሰናከለ ነዉ ( ያዕ210) የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ሁኔታዊ ኪዳን ነዉ በእስራኤል መታዘዝ ላይ ትዕዛዛቱን ሲጠብቁ እንደሚባረኩና ካልታዘዙ ደግሞ እንደሚፈረድባቸዉ ነዉ ( ዘጸ1526193-6)

. ኪዳኑን ማፍረስ እና ዉጤቶቹ

እስራኤል የሙሴን ኪዳን አፈረሱ (ኤር 3132) የእብራይስጡ ቃል ማፍረስ የሚለዉ ሄፌሩ ማለት ነዉ፤ ይህም ፓራር ከሚለዉ ግስ የመጣ ነዉ፤ መስበር ማለት በጥንቱ ትርጉም( በተምሳሌታዊ ንግግር ማመጽ ወይም መፍራት ማለት ነዉ) መስበር፣ማስወገድ፣ለማቆም ምክንያት መሆን፣ንጹህ፣መሸነፍ፣ተስፋ መቁረጥ፣መሟሟት፣መክፈል፣ ዉጤት የሌለዉ፣መዉደቅ፣መፍረክረክ፣መወገድ፣ወደ ከንቱነት መምጣት፣በፍጹም፣ማስወገድ፣ በሌላ ቃላት እስራኤል ኪዳኑን ላለማድረግ ስታምጽ መኖርዋ ያቆማል፣ትሟሟለች፣ትወገዳለች፤ ትዕዛዛቱን ከሰበረች ጊዜ ጀምሮ ዉጤታማ አትሆንም፤

አራት ነገሮች ትኩረት መደረግ አለባቸዉ፡

1.    የሙሴ ሕግ ሊሰራ ያልቻለዉ በመስቀል ላይ ነዉ ( ሮሜ 104 ኤፌ 215፣ቆላ 213-14፣ዕብ 718፣ዕብ 1019) አስርቱን ትዕዛዛት ጨምሮ(2ቆሮ 32-11) ይህ ማለት ግን ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ መታዘዝ አለባቸዉ ማለት አይደለም፤ አንዳንዱ ትዕዛዛት በሌላ መልክ ሆኑ እስካሁን ድረስ እየሰራ ይገኛል፤ እንደ ኪዳን ሁሉ ሊታዘዙት የሚገባ ሲሆን እንደ ሙሴ ኪዳን ግን አይደለም፤ የአይሁዶች መገረዝ እንደ ጥሩ ምሳሌ ማየት ይቻላል፤ይህም የአብርሃም እና የሙሴ ኪዳናትን ማየት ይቻላል፤ የዛሬዎቹ አይሁድ ግን ይህን ለማድረግ አይችሉም ምክንያቱም የሙሴ ሕግ ስለሆነ ነዉ፤ ለአብርሃም የተሰጠዉ ኪዳን ግን እስካሁንም ይሰራል፤ ዘጠኙ ትዕዛዛት(የሰንበትን ቀን አክብረዉ) ከሚለዉ ዉጭ በአዲሱ ኪዳን ዉስጥ እናገኛቸዋለን፤ እንደ አዲሱ ኪዳን ትዕዛዝ አድርገን ልንታዘዘዉ ይገባል፤

ብዙሃኑ የሙሴ ትዕዛዛት ግን አሁን ልንታዘዛቸዉ አይገባም፤

2.    እግዚአብሔር የሙሴን ሕግ በአዲሱ ኪዳን ተክቶታል፤ እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔርከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፡( ኤር 3131-32)

አዲስ በማለቱ ፊተኛውን አስረጅቶአል፤ አሮጌና ውራጅ የሆነውስ ሊጠፋ ቀርቦአል።(ዕብ 813) ይህ የመተካካት ስነመለኮት ይባላል ብዙዎቹ ያደርጉታል፤

3.    ዘዳግም 28-29  ላይ ጠብቁ ሲል እስራኤል ባይጠብቅ እና ኪዳኑን ቢያፈርስ ወደ አለም ሁሉ እንደሚበተኑ ይህም ደግሞ 1900 ዓመታት ያህል የተለማመደችዉ ነዉ ዲስፖራ ሆነዉ ቆይተዉ ወደ ምድራቸዉ ተመለሱ፤

4.    ያለቅድመ ሁኔታ የተገባዉ ኪዳን በሙሴ ኪዳን በኩል የተሰጠዉ እስካሁንም ድረስ ሙሉ በሙሉ የተፈጸመ አይደለም፤ ኪዳናቱም አሁን አይሰሩም፤

. ወሳኝ የሆኑ ትእዛዛት መሰበር

ያለጥርጥር ዋና ዋና የሙሴ ሕግጋት እስራኤል የሰበረችዉ በዘዳ 1815 ላይ ያለዉ ሲሆን ሙሴም ለሕዝቡ አለ ‹‹…አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ።››

በሙሴና በኢየሱስ መካከል የሚነጻጸር ነገር አለ ኢየሱስን ብቸኛ ነብይ ያደረገዉ ነገር ምንድን ነዉ፣ ትህትናዉ ነዉን፣ኢየሱስና ሙሴ ብቻ ናቸዉ ስለእግዚአብሔር ፊት የተናገሩት (ሙሴ በዘጸ 3310-11 ዘዳ 3410 ኢየሱስ ማቴ 1127 ዮሐ 118፣ዮሐ 5196468381015 30 1410) በምድሪቱ አራት ማዕዘን የተበተነዉ ሕዝብ ኢየሱስ በይሁዳ በነበረበትና ተቀባይነትን ባላገኘበት ጊዜ እንኳ ሙሉ በሙሉ አልተሰበሰቡም፤ በኋላም ፈሪሳዉያንና ጻፎች የእስራኤል መሪዎች እየሰሙ ነገራቸዉ፤

ማቴዎስ 2337-39

ቁጥር 39 የተጠቀሰዉ ከመዝሙር 11826 ነዉ፤

እነርሱን ከተበተኑበት ስፍራ ከመሰብሰብ ይልቅ ቤተመቅደሳቸዉ ቅዱስ ቤታቸዉ ሮማዉያን 70 . ላይ ደመሰሱት፤ የመጀመሪዉ የአይሁድ አመጽ ተሰበረ፣ከዚያም ታረዱ፣ በአገሮች ሁሉ በመበተን ከምድራቸዉ ለቀቀዉ ተሰደዱ እና ባሪያዎች ሆኑ፤ ሁለተኛዉ ብተና የሆነዉ 135. ላይ ሁለተኛ አይሁድ አመጽ ጀምረዉ በመፍረሱ ምክንያት ነዉ፤

ለምንድነዉ አስፈላጊ ትዕዛዝ የሆነዉ? የሕጉ ዋና አላማ እስራኤላዉያንን ወደ ክርስቶስ መምራት ነዉ(ሮሜ 81-4 ገላ 324-25) እሰራኤል መሲሁን አንቀበልም ሲሉ የሕጉን ዋና አላማ ሰበሩ ማለት ነዉ፤

. እግዚአብሔር ለምን ኪዳንን መሰረተ?

እግዚአብሔር በቅድመ እዉቀቱ ኪዳኑ እንደማይሰራ ያዉቃል፤ ታዲያ ለምን መሰረተ?

ምክንያቶቹ ጠቅለል  ሲደረጉ፡-

·         ለግለሰብና ለሕዝብ ባህርይን እንዲመሩበት ነዉ

·         በእሰራኤልና በሌሎች ሕዝቦች መካከል ያለዉን ልዩነት ለማሳየትና ለማገልገል (ኤፌ 214-15)

·         እስራኤልን ከሌሎች ሕዝቦች ለመለየት( ዘሌ1144-45 ዘዳ 76 141-2)

·         አለምን እንዲገለግሉ መሾም በእግዚአብሔር ስራ ለሌሎች ሕዝቦች እንዲተነብዩ (ዮናስ ለነነዌ) የዕብራይስጡን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲጽፉና ክርስቶስ እንዲመጣ

·         ቅድስናዉን ለመግለጽ

·         በቅድስና ለማሰልጠን

·         ለጋራ አምልኮ ጊዜን ለማመቻቸት

·         እስራኤላዉያንን ወደ ድነት ማለት ወደ ክርስቶስ ለማምጣት( ሮሜ 81-4፣ገላ324-25)

እግዚአብሔር አስሩን ትዕዛዛት ለሙሴ ሲሰጥ ቅድስናዉ ተገልጦ ነበር ይኸዉም በብዙ ድንቅና ምልክት ነዉ፤ በተራራዉ ግርጌ እስራኤላዉን ጣኦቶች ሰርተዉ ባመለኩ ጊዜ፣ ሌዋዉያን ለሐጢአት መሰዋዕት ባቀረቡ ጊዜ፣ምስጋናንና አምልኮን በሰጡ ጊዜ፣ እርሱ በመገናኛዉ ድንኳን ሙሴን ባናገረ ጊዜ፣በምድረበዳ ለእስራኤል የሚያስፈልጋቸዉን ባዘጋጀ ጊዜ፣ባለማመናቸዉና ባመጹ ጊዜ  በምድረ በዳ እስራኤልን በቀጣ ጊዜ፣ከእርሱ ፊታቸዉን ሲመለሱ ለከናዓናዉን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ፣ወደ እርሱ በተመለሱ ጊዜ ከመካከላቸዉ ሰዉ አስነስቶ ነጻ ሲያወጣቸዉ፣ በሰለሞን ጊዜ ክብሩ ቤተመቅደሱን በሞላ ጊዜ፣ቃል ስጋ በሆነ ጊዜና በመካከላቸዉ ባደረ ጊዜ እና ሌሎችም፤

. የጥል ግድግዳ

ይህ ከፋይ የሆነ ግድግዳ ለምክንያት የሚያገለግል ነዉ፤ እስራኤል ከሌላዉ ሕዝብ የምትለየዉ በሕጉ ብቻ ሳይሆን አሕዛብ ይህን ግድግዳ መዉጣትና ከእስራኤል መንፈሳዊ በረከት መካፈል ስለሚፈልጉ ጭምር ነዉ፤

በእስራኤል ዙሪያ ያሉ አገሮች ጣኦት አምላኪና ልጃቸዉን ለጣኦት የሚሰዉ፣በቤተመቅደሳቸዉ ዉስጥ ዝሙት መስራትና አስጸያፊ ነገር ማድረግ የተለመዱ ተግባሮች ናቸዉ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠበት ምክንያት ቅዱስ ሕዝብ እንዲሆኑለትና በልባቸዉም በተግባራቸዉም እንዲለዩ ከዚያም ለአለም ሕዝብ የበረከት ማስተላለፊያ መሳሪያ እንዲሆኑ ነዉ፤ቅዱስ አገር ለመፍጠር እግዚአብሔር ግድግዳ መፍጠር ነበረበት( ኤፌ 214-15) ይህን በማድረግ የአሕዛብን ጣኦታት መቀነስ ነዉ፤

አጠቃላይ ሕጉ ስለ ግድግዳዉ የሚናገር ነዉ አሕዛብ ያለጥሩ ምክንያት ይህ ሸክም በላያቸዉ ላይ መዉደቁ ነዉ፤ የሰንበት ሕግ፣ መስዋዕትና መስጠት፣ የምግብ ሕጎች፣የጺምን ዳር ዳር መቁረጥ፣የተደባለቀ ሱፍ ልብስ መልበስ፣ተመሳሳይ የጥጥ ልበስ መልበስ፣ጸጉርን በልብስ የመሸፈን አስፈላጊነት፣የእንስሳትና አትክልት አይነቶች፣ እና የመሳሰሉት ሕጎች ወዘተጠቅላላዉ 613 ሕጎች ናቸዉ፤ አሕዛብ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ከሆነ ሕጎቹን ሁሉ የመጠበቅ ግዴታ አለባቸዉ፤( ያዕ218) የጣዖታትን ሕይወት ያወግዛል፣ ተገረዙ እና ሕጉን መጣስ ቅጣትን ያመጣል፤ በዚህ ልማድ የጥል ግድግዳ የጣኦታቸዉን መንገድ እንዲተዉ እና የሚያስጠላዉን ልምምዳቸዉ የሚለይ ግድግዳ ነዉ፤

ግድግዳዉ በጨለማ ዘመን ካለዉ የገዳም ግድግዳ ጋር ተመሳሳይ ነዉ፤መነኩሴዎች ተለይተዉ ይጸልያሉ፣መጽሐፍ ቅዱስን በመገልበጥና በማጥናት ለመልካም ስራ እና ለወንጌል ስርጭት መነሳሳትን ያካትታል፤ልክ የዘመናዊዉ የስደተኞች ሕግ፣ለአገር ደህንነት ሲባል በዉስን ቦታ ሆኖ ቃለ መሐላን መፈጸም እና ከዚያ አጥርን፣ግድግዳን ይገነባሉ፤ በጦርነት ባሸነፉበትም ስፍራ ወታደራዊ ማዕከል በመገንባት የጦር ልምምድ ያደርጋሉ፤

1500 አመታት እግዚአብሔር የጥልን ግድግዳ እስራኤልን ለመቀደስ ሲል ተጠቅሞበታል ነገር ግን ልባቸዉን ለመቀደስና ለማንጻት ሐይል የለዉም፤ ስለዚህም የተስፋዉን ቃል በሕጉ በኩል እንደ አገር ለመለወጥ አልቻለም፤(ሮሜ83) በግደግዳዉ ምክንያት እስራኤል ወደ ጌታ የምትመለስበት ጊዜ አለ ነገር ግን ሁሉንም እስራኤልን ተጠቅሞ የአለምን ሕዝብ አይባርክም፤ ሁሉም ቤተሰብ ወደ መጽሐፍ ቅዱሱ ክርስቶስ አይመጡም፤ በማይሰራዉ ኪዳን ይህ ሊፈጸም አይችልም ነገር ግን በአራቱ ያለቅድመ ሁኔታ በሆነዉ ኪዳን እስከመጨረሻዉ ዘመን ድረስ ይቆያሉ፤በተመሳሳይ መልኩ የእስራኤል መመረጥ፣በሙሴ ኪዳን ሊታይና ሊቆም አይችልም ነገር ግን ጠንካራ በሆነዉ በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተዉ ኪዳን ላይ የሚቆም ነዉ፤

13. ያለ ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተዉ ኪዳን የማይችለዉ

የአብርሃም፣የምድሩ፣የዳዊት እና የአዲሱ ኪዳን በሁኔታ ላይ ያልተመሰረቱ ኪዳናት ናቸዉ፤ስለዚህም የማይቀሩ ናቸዉ፤ ጳዉሎስ በአዉዱ ሲናገር ለእስራኤል ሕዝብ ነዉ ‹‹እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።( ሮሜ 1129) እግዚአብሔር ሕዝቡን በሐይል ከግብጽ ባርነት ነጻ እንደሚያወጣ ተስፋ ገባ(ዘፍ 1513-14) ከአባቶቻቸዉ ጋር የገባዉን ኪዳን ‹‹እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው።›› ዘጸ 36151645) እስስራኤልን ነጻ በማዉጣት ቃልኪዳኑን ፈጸመ ለአብርሃም፣ይስሃቅና ያዕቆብ የገባዉ ኪዳን ለዘሮቹም ጭምር ነዉ ‹‹እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል ሁሉ አዎን ማለት በእርሱ ነውና›› (2ቆሮ120)

14. የእስራኤል መመረጥ የማይቀር ጉዳይ ነዉ፤

በሥጋ ዘመዶቼ ስለ ሆኑ ስለ ወንድሞቼ ከክርስቶስ ተለይቼ እኔ ራሴ የተረገምሁ እንድሆን እጸልይ ነበርናእነርሱ እስራኤላውያን ናቸውና፥ ልጅነትና ክብር ኪዳንም የሕግም መሰጠት የመቅደስም ሥርዓት የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና (ሮሜ 93-4)

እስራኤል አሁንም የማደጎ ልጆች ናቸዉ፤ እግዚአብሔር ራሱን የሚያየዉ የእስራኤል አባት አድርጎ ነዉ፤(ኤር 319) እስራኤልን ልጆቼ ይላል፤(ዘዳ141) የእርሱ ልጅ (ዘጸ 422 ሆሴዕ 111) የበኩር ልጅ (ዘጸ 422፣ኤር 319)

ጳዉሎስም አለ በሮሜ 11127-29

እስራኤል የተመረጠ ሕዝብ ናት፤ዛሬም ባለማመናቸዉ ምክንያት ቢቀሩም እንኳ የተመረጡ ናቸዉ፤በመጽሐፈ መሳፍንት ዘመን በጣዖት ሐጢአት በወደቁ ጊዜ ከእነርሱ ጋር እንደገና ከእነርሱ ጋር በመነጋገር ይመልሳቸዉ ነበር ዛሬም በእነረሱ የጀመረዉ አላማ ይፈጽመዋል፤ጳዉሎስ ለቤተክርስቲኑ ሲናገር በፊሊ16 ላይ ‹‹በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና›› ሮሜ 33-4

እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባዉ ኪዳን በምንም ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ነዉ፤ በማያምኑም እንኳ ኪዳኑን ይጠብቃል እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸዉን? አልጣለም፤የእስራኤል መመረጥ የማይቀር ነዉ፤

15. ኪዳኑ እስካሁንም የእስራኤል ነዉ

ሮሜ93-4

ጳዉሎስ ሲናገር ‹‹የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና፤…›› ይህ ቃል ለእስራኤል ያለፈ ኪዳን ሳይሆን የእነርሱ የአሁንም ነዉ፤ የሙሴ ኪዳን የሚያሳየዉ አራት በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ መሆኑ ነዉ፤

ሮሜ1127‹‹ ይህ የሚለዉ የአሁኑን ዘመን ነዉ ከእነርሱ ጋር ያለኝ ኪዳን ሐጢአታቸዉን አስወገዳለሁ ይህ ጠቅለል ሲደረግ ኢሳ 5921 ኤር 3134 ይህ ዘላለማዊ የሆነ የአዲስ ኪዳን ነዉ፤ የሮሜ መጽሐፍ አዉዱን ስንመለከት እግዚአብሔር ለእስራኤል የሚገባዉን አዲሱን ኪዳን የሚያሳይ ነዉ፤እስካሁንም ለእስራኤል ልዩ ነዉ፤

አምስቱንም ኪዳን ስንመለከት ከእስራኤል ዉጭ ወደ ሌላ አገር የተላለፈ አይደለም አስካሁንም ለእርስዋ ነዉ፤

 16. በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተዉ ኪዳን ለአህዛብና ለቤተክርስቲያንም የሚተገበር ነዉ

ጸሑፋችን እንዲህ ይነበባል ‹‹ ለአብርሃም የተገባዉ መንፈሳዊ በረከት ለምድር ሕዝቦች ሁሉ የሚሆን ነዉ፤ እግዚአብሔር ሕዝቦችን አሕዛብና እስራኤል ብሎ ከመከፋፈሉ በፊት( ዘፍ121-3) የአማኞች ድነት በዚህ ጊዜ ዋስትና የሚሰጠዉ በአዳምና ሔዋን ዘመን እግዚአብሔር የተስፋን ቃለ ሲገባ ከሴትዋ (ከማርያም) የሚወለደዉ ዘር ወይም ዘሮች(ኢየሱስ (ዘፍ 315) እርሱም እስራኤል ነዉ፤እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያለዉ ኪዳን የድነት ሲሆን ይህም ለእስራኤልና አሕዛብ ነዉ፤ ጳዉሎስ እንዲህ ከተረዳ እናም እንደዚህ መረዳት ያስፈልጋል፤

ለአይሁድ የተገባዉ ኪዳን አሁን በቤተክርስቲያን ዘመን ለአሕዛብ  ይተገበራል ይህም አራት ነገሮችን ይዟል

1.          ኤፌ 36 ይህም፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም መስበክ በክርስቶስ ኢየሱስ በሆነ የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ፥ ኤፌ 213-15 ገላ 313-14

አሁን የጥል ግድግዳዉ ፈርሷል፤አሁን አሕዛብ እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባዉን የድነት ተስፋ ተካፋይ ሆነዋል፤(ሐዋ 151-19፣ገላ 51-6) ይህ በክርስቶስ በእምነት በኩል የሚሆን ነዉ፤ በተጨማሪም እግዚአብሔር ለእስራኤል በገባዉ ተስፋ መሰረት መንፈስ ቅዱስ በልባቸዉ ያድራል፤( ኤር 3133) አሁን በቤተክርስቲያን ዘመን የዳኑ አሕዛብ ከዳኑት አይሁድ ጋር በእኩልነት መንፈስ ቅዱስ በልባቸዉ ያድራል፤ በክርስቶስ ደም አይሁድና አሕዛብ በወንል በኩል የሚገኘዉን ተስፋ በእኩልነት ይካፈላሉ፤ የክርስቶስ አካል ናቸዉ በጋራ ወራሾች ናቸዉ፤

2.          እግዚአብሔር ኪዳኑን ለአሕዛብ ከፈተ፣ የድነታቸዉ ዉጤት በዚህም እያንዳንዱ አማኝ ይድናል፤የተስፋ ቃሉ እስራኤል ሁሉ እንዲድኑ ነዉ፤

ሮሜ1111 እንግዲህ፦ የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን? እላለሁ። አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ።

ከእስራኤል ሞገስን ለማግኘት ብሎ በርግጥ እግዚአብሔር ድነትን ለአሕዛብ አላመጣም፤ ድነትን ያመጣዉ ስለሚወዳቸዉ ነዉ (ዮሐ 316) እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ (ሐዋ 154) እግዚአብሄር ለአሕዛብ ድነትን አመጣ ምክንያቱም እስራኤልን ለማስቀናት ነዉ፤የዳኑ አሕዛብ በኑሮአቸዉ ሁሉ ለአይሁድ ምሳሌ በመሆን መኖር እንዳለባቸዉ ጥቅሱ ይነግረናል፤ በተግባር መባረክ አለባቸዉ ወንጌሉነ በፍቅር ሊያካፍሉአቸዉ ይገባል፤ ትለቅ ደግነት ያደረጉ አሕዛብ በመጨረሻ ምን ተባሉ ማቴ 2531-40 በታላቁ መከራ ጊዜ በመከራ ዉስጥ ለሚያልፉ እስራኤላዉያን (ወንድሞቼ .40) ልባቸዉ ክርስቶስን እንዲቀበሉ ያዘጋጃቸዋል፤ እንደ ሮሜ1111 እንዲህ ብዬ ላጠቃልል

3.          ወንድሞች ሆይ፥ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው..እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል ሮሜ 1125-26

እግዚአብሔር አስቀድሞ በወሰነዉ መሰረት የአሕዛብ ሙላት አስከ ንጥቀት ጊዜ ድረስ ወደ ክርስቶስ እንዲገባና በታላቁ መከራ ጊዜ ለእስራኤል የድነትን ጊዜ ለማምጣት አስቦ ነዉ፤

4.          እግዚአብሔር በመስጠቱ ጸጋ እንደማይፀፀት ለማሳየት የቤተክርስቲያን የተስፋ ቃል ይፈጸማል ይህም የሚሆነዉ ያለ ቅድመ ሁኔታ ላይ በተመሰረተዉ ኪዳን ሲሆን አሕዛብም የዚህ ድነት በረከት ተካፋዮች ናቸዉ፤( ሮሜ 1129) ጳዉሎስም ስለእስራኤል የተናገረዉ ነገር ትከክል ነዉ፤ መመሪዉም በቤተክርስቲያን ላይ የሚፈጸም ነዉ፤ ሮሜ9-11 ትኩረት ያደረገዉ ነጥብ መታየት ያለበት በሮሜ 8 አና 12 ላይ ባለዉ ምክረ ሀሳብ ነዉ፤ እግዚአብሔር ለማይታዘዙት ሕዝቦች ያለ ቅደመ ሁኔታ በተመሰረተዉ ኪዳን መሰረት ያስባቸዋል (ሮሜ9-11) ሙሉ በረከት እና ተስፋዉ ሀጢአተኛ ለሆነችዉ ቤተክርስቲያን ጭምር ነዉ ሮሜ 8

17. የእስራኤል መመረጥ በቤተክርስቲያን ዘመን

በቤተክርስቲያን ዘመን አስራኤልን መመረጥ እንደሚከተለዉ እናያለን።

.አይሁዳዉዉያን ተመስርተዋል፣ታዘዋል፣እና ቤተክርስቲያንን መርተዋል

ጴጥሮስ አይሁዳዊ ነዉ የመንግስተ ሰማይ መክፈቻ ቁልፍ ተሰጥቶታል፤(ማቴ1618-19) ለአለም የቤተክርስቲያንን በር ከፈተ የአለም ሕዝብ በሶስት የሐይማኖት ቡድን የተከፈለ ነዉ፤

1.          አይሁድና ከአሕዛብ ወደ ሁዲነት የተመለሱ መጽሐፍ ቅዱስ አላቸዉ (ሐዋ 2)

2.          ሳምራዉያን አሕዛብና አይሁድ ቅልቅል የሆኑ የሕጉን መጽሐፍ አስተካክለዉ በሙሴ አሕዛብ አስተሳሰብ ዉስጥ ናቸዉ፤የሚያመልኩትም ባልታዘዙበት ስፍራ በገሪዛም ተራራ ነዉ(ሐዋ 814-17) እና

3.          አሕዛብ በአጠቃላይ የእብራዉያን አይነት መጽሐፍ የሌላቸዉ ናቸዉ( ሐዋ 10)

አይሁዶች ከገዛ ምድራቸዉ ከመዉጣታቸዉ ወይም ከመበተናቸዉ በፊት ቤተክርስቲያንን ሲመሩና ሲስተዳድሩ ነበር( ሐዋ151-31 ሮሜ 322 ኤፌ 222)

. ወንጌሉ በመጀመሪያ ለአይሁድ ነዉ

ጌታ ወንጌሉን ለአለም ከመላኩ በፊት አስቀድሞ የሰጠዉ ለአይሁድ ነዉ (ማቴ106 15242819) አሁን ባለንበት ዘመን ወንጌሉ ከመድረሱ በፊት አሰቀድሞ የተሰጠዉ ለአይሁድ ነበር( ሮሜ116) ጳዉሎስ ለአሕዛብ ሐዋርያ ሆነ (ሮሜ 1113) በሄደበት ስፍራ ሁሉ ይዞ ሄደ እንደገና ተመለሰ፣ተልዕኮዉን እናም የምንከተለዉ ነዉ ምክንያቱም አስፈላጊ ስለሆነ ነዉ (ሐዋ 1346)

18. የአስራኤል መመረት በታላቁ መከራ ጊዜ

አብርሃም ኪዳን ያለቅድመ ሁኔታ የሆነ ኪዳን ነዉ ሁሉም ኪዳኖች ስለምድሩ የገባዉ፣ የዳዊትና የአዲስ ኪዳን ሁሉም ሙሉ በሙሉ የተፈጸመ አይደለም፤

ጠቅለል አደርገን ስንመለከት

1.         

. እስራኤል አለምን ትባርካለች

በታላቁ መከራ ጊዜ ከመንግስቱ በፊት፣ እስራኤል የአለምን ማህበረሰብ ሁሉ ትባርካለች፤ 14400 አስረኤላዉያን የወንጌል ስርጭትን ስራ ይሰራሉ ከሕዝብ ፣ከወገን፣ ከነገድ፣ ከቋንቋ( ራዕይ 71-9 በተለይ .9)

. እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርካል፤

ታላቁ መከራ ሲቃረብ አገዚአብሔር ለአበርሃም እንደተናገረ እባርክሃለሁ እስራኤል ሁሉ ይድናል በሚለዉ ቃል ይፈጸማል( ዘካ 131፣ሮሜ 1126)

የእስራኤል ድነት ማለት የታላቁ መከራ ጫፍ ላይ የሚሆን ነዉ(ዘካ 131) ይህም ወደ ኢየሱስ ዳግም መምታት ይመራል፤(ሆሴዕ 515፣ማቴ 2339፣ራዕይ 19)ሰይጣን ሲታሰር(ራዕይ 202) የሺህ አመተ መንግስት ሲመሰረት (መዝ 26-8 ኢሳ 96-7 ሉቃ 130-33 ራዕ 204)

19. በመጨረሻ እግዚአብሔርም ሁሉንም ኪዳናት በስጋም በመንፈሳዊም የገባዉን ሁሉ ይፈጽማል፤

ኢየሱስ/መሲሁ/ በምድር ሁሉ ላይ ይገዛል (መዝ 2611-12 ኢሰ 22-4) እና ቤተክርስቲያን ኢየሱስ በከበረ አካሉ ይመለሳል፣ በታላቁ መከራ ጊዜ ያሉ ቅዱሳን በምድራዊ አካላቸዉ ሆነዉ ትንሳኤን ካገኙ ቅዱሳን ጋር ከእርሱ ጋር አብረዉ ይገዛሉ፤( ራእ16 510 204-6) በትንሳኤ የተነሳዉ ንጉስ ዳዊት እስራኤልን ይገዛል( ኤር 309 ሕዝ 3423-24) 12 ሐዋርያት በዳዊት ስር ሆነዉ በአስራ ሁለቱ ነገዶች ላይ ይነግሳሉ፤( ማቴ 1928፣ሉቃ 2228-30)

2.          በምድር ያለዉ መንግስት ምድሪቱን ይለዉጣታል(ኢሳ 24116-96517-25)

3.          እስራኤል እስካሁንም በአለም ካሉ ሕዝቦች በእግዚአብሔር የተመረጠች ናት( ዘዳ 15628113 ኢሳ 141-2)

4.          በመንፈሳዊ በረከት በሺህ አመቱ ጊዜ በሕይወት ያሉ እስራኤላዉያን ሁሉ በስጋ አካላቸዉ እንዳሉ የሚድኑ ናቸዉ፤ የእስራኤል ሕዝቦች ሁሉ ይድናሉ በብሉይ ኪዳን ያሉ ቅዱሳን ደግሞ በትንሳኤ አካል ይሆናሉ (ኢሳ 2619 ዳን 122) ከአሕዛብ ወደ በግነት የመጡ ማቴዎስ 2531-40 ድነትን ለመቀበል ዕድል ያገኛሉ(ኢሳ 496) በሺህ አመቱ ቤተመቅደስ ዉስጥ በአንድነት ያመልካሉ፤( ኢሳ 6618-24)

5.          በልዩ መንፈሳዊ አገልግሎት ንጉሱ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም ያገለግላል፤(መዝ 26 ኢሳ 11-12 እስራኤል የመንግስቱ ካህናት ናት (ዘጸ 196) የንጉስ ካህናት( 1ጴጥ 29) የእግዚአብሔር ካህናትየአምላካችን አገልጋዮች (ኢሳ 616) ክርስቶስ ዓለምን የሚያገለግልበት ጊዜ ነዉ (ዘካ 8 20-23)

6.          የቤተክርስቲያን ቅዱሳን በከበረ አካል ይሆኑና በስጋ አካላቸዉ ያለዉ ሁሉ ወደ ልዩ የሥጋዊ በረከት ዉስጥ ይገባሉ፤

7.          ሁሉም አግዚአብሔር ለእስራኤል የገባቸዉን የተስፋ ቃል ይፈጽማል፤ኢየሱስ ጠላቶቹን ያጠፋል (ዘካ 122-9) ሺህ አመቱ ሲጀምር እስራኤል ከአራቱም አቅጣጫ ይሰበሰባሉ ወደ ተስፋዋ ምድር ይገባሉ፤(ኢሳ 1111-12 435-7 ኤር 317-10 ሕዝ 1114-183715-23 ማር 1327) ፍጹም ሰላም እና ደስታ ይሆናል፣ ሀዘን ይጠፋል፤(ዘዳ 305፣ኢሳ2712 3023-26 351-2 6521-24 ወዘተ…) በአዲስ ሕግ በቅድስቲትዋ ከተማ አዲስ ቤተመቅደስ ይገነባል አምልኮ ይጀመራል፤ የመንግስቱ ሕግ ( ሕዝ 401-4327 441-4624)

19. የእስራኤልን መመረጥ የሚያሳየዉ እንደገና ስፍራቸዉን መያዝ ነዉ

ይህን ጠቅለል ስናደርግ እግዚአብሔር እስራኤልን መረጠ

·         ቅድስናዉን ለማሳየት እና ለሕዝብ ክብር መሆን

·         ከአብርሃም ጀምሮ የመጀመሪዉ የእግዚአብሔር ቃል ተቀባዮች ናቸዉ

·         ለሌሎች አገሮች ይተነብያሉ

·         መጽሐፍ ቅዱስን ያመጣሉ

·         ክርስቶስን ያመጣሉ

·         የጥንትዋን ቤተክርስቲያን መስርተዋል፣ገንብተዋል

·         ለአለም ወንጌልን ማሰራጨት የሚለዉን ለመፈጸም

·         በታሪከ ድነትን ለአለም ያመጣች ብቸኛ አገር ናት

·         ከአብርሃም  ጀምሮ ክርስቶስ በአለም ላይ ያገለግላሉ

20. የመጨረሻዉ ዘመን

ብዙ ትንቢቶች በመቶዎችና በሺዎ﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽﷽ የሚቆጠሩ ተፈጽመዋል፤ በጥልቀት ደግሞ ወደፊት የሚፈጸሙ ናቸዉ፤ አስረኤል ከግብጽ ባርነት ጀምሮ ( ትንቢት ተነግሮ ነበር በዘፍ 1513-14) የመጀመሪዉ እስራኤል ከየስፈራዉ ተሰባስበዉ 1948 ወደ ምድራቸዉ መጡ( ሕዝ 2033-383622-24) 1967 የቤተመቅደሱን ተራራ ያዙ( ይህም ለሌላ ታላቅ መከራ መሆን ምልክት ነዉ) ከዚያ በኋላ ኢየሱስ እንዲመጣ 30 ትንቢቶች መፈጸም አለባቸዉ

በዚህ ፍጻሜ ሁሉም ትንቢቶችና የተስፋ ኪዳናት እስካሁንም ገና አልተፈጸሙም፤ በምን ምክንት ትንቢቶቹን ተምሳሌዊ ወይም ግጥም ነዉ ብለን ቸል የምንለዉ አይደለም፤ እስራኤል እስራኤል ናት አሕዛብም አሕዛብ ናቸዉ፤ ቤተክርስቲያንም ቤተክርስቲያን ናት የተስፋዋ ምድርም የምትታየዋ የእስራኤል ምድር ነዉ እና ወዘተ

ወርቃማዉን ሕግ እናስታዉስ፡

መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ያለዉ ስሜት እንዲሰጥ የጋራ የሆነዉን ስሜት መያዝ አለብን፣ሌላ ነገር አትፈልግ፣ ማንኛዉን ቃላት በመጀመሪያ እንዳለ እንዉሰደዉ፣ሁልጊዜ እንዳለ እንዉሰድ አዉዱን ከላይና ከታች ካለዉ ክፍል ጋር አያይዘን ማንበብ አለብን ከዚያም እዉነቱን እናገኘዋለን፤

አሜን 

በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. * 

ኖርማን ማንዞን 2016

መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ

የማራባትና መገልበጥ መመሪያዎች 

 


 

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines