የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትበኖርማን ማንዞን

(A Handbook of Bible Doctrine)
Original English By Norman Manzon
Translation By Zemen Endale Lashetew

 


መግቢያ

ኢትዮጵያ ለምትገኙ ለተወደዳችሁ ወንድምችና እህቶች፡-

በተወደደው ወንድሜ ዘመን እነዳለ በኩል ይህችን አነስ ያለች መጽሁፍ ለእናንተ በመስጠቴ
ትልቅ ክብር ይሠማኛል፡፡ በዚህች መፅሀፍ ውስጥ የተቀመጡት ጠቃሚ ርእሶች የተወሰዱት በመቶ ገፆች
ከመቆጠሩ በድህረ ገጽ www.BibleStudyProject.org. ላይ ከሚገኙ መርጃ ሰነዶች የተውሰዱ
ናቸው፡፡ በዚህ መርጃ ሠነድ ውስጥ የተዘረዘሩት ነጥቦች ለክርስትና አስተምህሮ መሠረት በመሆን ሥለ
መጽሐፍ ቅዱስ ሰፋ ያለ እውቀት ይሠጡሃል፡፡ ጌታ ቢፈቅድ፤ ለዚህ የመመሪያ መጽሐፍ አጋዥ
የሚሆኑ በጋብቻ፤ በፀሎት፤ በመንፈሳዊ ሥጦታዎች እና ተአምራዊ ፈውስ ዙሪያ ጠቃሚ ርእሶች
አየተዘጋጁ ነው፡፡

ጥናቶቹ የተቀመጡት በቅደም ተከተል ነው፡፡ በቅድሚያ ተወዳዳሪ በማይገኝለት መጽሐፍ ቅዱስ
ከእግዚአብሔር ባገኘነው ከተፈጠሯዊውም ዓለም በማይገኘው መገለጥ እንጀምራለን፡፡ ከዚያም በመጽሐፍ
ቅዱስ እውነቶች፤በመጀመሪያ በዘላለማዊ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስን በሰዎች እጅ ስላዘጋጀው ስለ
እግዚአብሔር ባህሪያት በመግለጥ እንጀምራለን፡፡ ከዚያም በመቀጠል ስለ መጀመሪያ ፍጥረቶቹ ስለ
መላእክት እና በእርሱ ላይ ሰላመፁት ስለ ሠይጣንና አጋንንት እንመለከታለን፡፡ ከዚያም በኋላ ስለ ሠው
ባህሪይ፤ በኃጢአት ስለመውደቅ እና ስለ ድነት እንቀጥላለን፡፡ በመቀጠልም እግዚአብሔር ቃሉን እና
መሲሁን ለዓለም ለመስጠት የመረጣትን አስራኤልን እና ቤተ ክርስቲያንን በመመልከት በመጨረሻም
የወደፊቱን ፍጥረት እቅድ፤ ስለ መላእክት እና ሠብአዊነት እንመለከታለን፡፡ ጥናቱ አንዱ ለሌላው
መሠረት በመሆኑ በቅደም ተከተል እንዲነበብ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የመጨረሻው የታመነ ምስክር- አስተማሪ ያልሆነ- በመሆኑ ለእያንዳንዱ ነጥብ
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጣቀሻዎች ሰጥቼያለሁ፡፡ ፀሎቴ እነዚህን የጳውሉስንና የሥላስን መመሪያዎች
በማዳመጥና በየቀኑ መጽሐፍትን በመመርመር የታወቁ የተከበሩ የቤሪያ አይሁዶችን ተምሣሌት(የሐዋሪያት
ሥር 17፤10-11) እንድትከተሉ ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝ በተለይ ስለ ወደፊቱ መገለጥ
የማስጠነቅቃችሁ ጥቂቶቹ ምዕራፎች ጥልቀት በሌለው ትምህርት ግልፅ ላይሆኑ ይችላሉ፡፡ ክፋቱ በዚች
አጭር ፅሁፌ ውስጥ ይህንን ጉዳይ የማስረዳት አቅሜ መወሰኑ ነው፡፡ ቢሆንም ከእነዚህ ምንባቦች
ላልኩት የማስረዳት ውስንነቴ ሌላ ማመሳከሪያ ሳትፈልጉ ያልኩት ከብዙ ጥናት በኋላ የደረስኩበት
መደምደሚያ መሆኑን በመገንዘብ እንድትማሩ እመክራለሁ

፡፡
አብዛኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በዚች አጭር ፅሁፍ ውስጥ ለማስተላለፍ አይቻልም፡፡
በመሆኑም እንደነዚህ በጣም ጠቃሚ እንደሆኑት ፅሁፎች መጽሐፍ ቅዱስን በተለይም አዲስ ኪዳንን
ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ማንበብን ቸል ማለት የለብንም፡፡ በመጨረሻም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
በራሱ ማለቂያ ስሌለው አላማውም እኛን ስለ እግዚአብሔር እና ስለ መንገዶቹ በማስተማር በቅድስናና
በቅናት ጠለቅ ወዳለው አምልኮው እንድንገባ ነው፡፡ በቀረው ህይወታችንም የእግዚአብሔርን ቃል
በመማር፥ እርሱን በማምለክና ራሳችንን በመቀደስ በልጁ እኛን ሐጢአተኞችን ኃጢአት በሌለበት በራሱ
ደም ለገዛው እንለይ፡፡

የእግዚአብሔርን ቃል ስታሰላስሉና ስትኖሩበት በረከት ይሁንላችሁ፡፡
በጌታ አገልጋያችሁና ባልደረባችሁ ኖርማን ማንዞን

I. የመጽሐፍ ቅዱስ ባህርያት

መጽሐፍ ቅዱስን የተፃፈው በሶስት ቋንቋዎች ሲሆን ለመፃፍም ከ1600 ዓመታት በላይ
ፈጅቷል፡፡ የተፃፈውም 40 በሚደርሱ ቢያንስ በ11 የሥራ መስኮች ላይ በተሠማሩ (ከንጉስ እስከ ግብርና
ባለሙያዎች) ቢያንስ በ3 አህጉሮች በሚገኙ 11 አገሮች ውስጥ ባሉ ሠዎች ነው፡፡ በዓለም ላይ ያሉ
መጽሐፍት የተለያዩ ጥራዞች ሲኖራቸው መጽሐፍ ቅዱስ ግን ጥራዝ የሌለው ብቸኛው መጽሐፍ ነው፡፡
መፅሐፉ 66 ሙሉ በሙሉ የተቀናጁ እና የማይጣረሱ ምእራፎች አሉት፡፡ መጽሐፉን የፃፉት ሠዎች
ቢሆኑም የተፃፈው ግን በመገለጥ፤ በሚያበረታታውና በሚመራው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው፡፡

በ2ኛው ጢሞቴዎስ 3፤16 እነደተነገረው ቅዱሣት መጽሐፍት ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ ባለበት
ሰው የተጻፉ ናቸው፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባት የሚለውን የግሪኩ ቃል እስትንፋስ ሲለው ይህም
የእግዚአብሔር ትንፋሽን ያመለክታል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር መጽሐፍ ቅዱስን በሠው ፀሐፊዎች
አማካይነት እስትንፋሱን ያሳቀመጠበት መጽሐፍ ነው፡፡

እኒዚህ ከሶስትና ከአራት ጥቅሶች በፊት በመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በራእይ መጽሐፍ
ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የዚህን መጽሐፍ የትንቢት ቃል የሚሠማውን ሁል አስጠነቅቃለሁ፤ ማንም በዚህች
የትንቢት ቃል ላይ አንዳች ቢጨምር፤ እግዚአበሔር በዚህ መጽሐፍ ውስጥ የተፃፉትን መቅሰፍቶች
ይጨምርበታል፤ ማንም በዚህች የትንቢት መጽሐፍ ከተፃፈው ቃል እንዳች ቢያጎድል፤ እግዚአብሔር
በዚህ መጽሐፍ ከተፃፉት ከህይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እድሉን ያጎድልበታል (ራእይ 22፤18-
19)፡፡

ዮሐንስ በመፅሐፉ ውሰጥ ስለ እግዚአብሔር ቃል የጠቀሰው እና በመቶዎች የሚቆጠሩ የብሉይ
ኪዳን ነብያት እንዲሁም የአዲስ ኪዳን መሰረታዊ አስተምህሮቶች እና ነቢያት ያስጠነቀቁት መጽሐፍ
ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ነው፡፡ ስለዚህ የዮሐንስ ማስጠንቀቂያ የሚያሳየው የነገስታት ንጉስ
የጌቶችም ጌታ ዳግም ምፅአት ድረስ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የተገለጠበት 66 የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሎች መኖራቸውን ነው፡፡

ብዙ ውጊያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተነስተዋል፡፡ ነገር ግን ብዙ ህግ አስከባሪ ነን ባዮች ስህተት
ለመፈለግ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበውት አማኞች ሆነው ቀርተዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክን
በሚያወሳባቸው ጉዳዮች የታሪክ ባለሙያዎች እና አረኪኦሎጂስቶች በሚያስገርም ሁኔታ ትክክል እንደሆነ
መስክረውለታል፡፡ ሣይንስን በተመለከተም በሚያነሳቸው ጉዳዮች ትክክል እንደሆነ ተምኖበታል (ስለ
ዓለም አፈጣጠር እና ስለ ሰው ልጆች አመጣጥ እንኳን ሣይቀር)፡፡ እሰኪ ይህ ሣይንቲሰት ከብዙ ድካም
በኋላ የመሰከረውን እንመልከት፡፡

 

በአርኪኦሎጂ ቁፋሮ ወቅት በተመሳሳይ የጊዜ ክፍተት ውስጥ በአበባነት ጊዜያቸው በተለያየዩ ቦታዎች
የሞቱትን የእፅዋት ቅሪተ አካል ተመሳሳይነት በድንገት አገኘን፡፡ በእነርሱ ላይ ልዩነት በፍጹም
አይታይም፡፡ ይህ ሁሉ ከዘገምተኛው የህይወት ለውጥ አስተሳሰብ የሚቃረን ድንቁርና ….. ሁሉም
ምርምሮቼ ወደ ሚያስገርም ተቃራኒ ውጤት…..በዚህ ምክንያት የዘገምተኛ ለውጥ አስተሳሰብ ሙሉ
በሙሉ ውድቅ ሆነ…. ለሥነ ህይወት ትምህርት ምርምር አስቸጋሪው እንቅፋት፡፡ በዚህ ምክንያት
የዘገምተኛ ትምህርት አስተሳሰብን በቤተ ሙከራ ለማሳየት የታሰበ የ40 ዓመታት ልፋቴ ሙሉ በሙሉ
ከንቱ ቀረ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የታመነ ነው፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሠማይንና ምድርን ፈጠረ (ዘፍጥረት
1፤1)፡፡ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ሠውን ከምድር አፈር ሰርቶት እስትንፋሱን እፍ አለበት
(ዘፍጥረት2፤7)፡፡

የትኛውም መጽሐፍ ፍቅርን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አይገልፅም፡፡ መፅሐፉም ባልንጀራህን
እንደራስህ ውደድ (ዘሌዋውያን 19፤18፤ ማቴዎስ 22፤39) እንዲሁም ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤
ለሚሳድዷችሁም ፀልዩ (ማቴዎስ 5፤44) ይላል፡፡ ይህ ፍቅር የጋብቻን ውበትና በረከት ያሳያል፤
ይህንንም የተከበረውን አስገራሚ የሰዎች ግንኙነት የሚያሠጋን ማንኛውንም ነገር ይኮንናል፡፡ ይህ ፍቅር
ዓለምን እንደ ሱናሚ ማዕበል እያጥለቀለቀ ለሴቶች፤ ለወላጆች፤ ለአዛውንቶች፤ ለህፃናት፤ ዳግም
በክረስቶስ ላልተወለዱ፤ ለድሆች፤ ለአካል ጉዳተኞች እና ለመፃተኞች ክብርን ያጎናፅፋል፡፡ በእርግጥ ይህ
የቃሉ ፍቅር የሰው ልጆችን ከሚወደው ፍላጎቱም እነርሱን ማዳንና በማናኛውም በኩል መባረክ ከሆነው
ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፡፡

II. የእግዚአብሔር ባህሪያት

እግዚአብሔር በራሱ የሚኖር ነው፡፡ የእርሱ መኖር በማንም መኖር ምክንያት አይደለም (ዘፍ
1፤1)፡፡ እግዚአብሔር እውነተኛ ሰው ነው፡፡ እንደ እናንተና እነደ እኔ ሥጋ የሌለው ነገር ግን የመንፈስ
ሰው (ዮሀ 4፤24) ነው፡፡ እርሱ ኃይል ባይሆንም ኃይልን ይጠቀማል፤ ሁሉን ነገር ባይሆንም የሁሉ ነገር
ፈጣሪ ነው፡፡ ለሰዎች መኖር ባህሪያቶቸን በሙሉም እርሱ አለው፡፡

1.የማሰብ ችሎታ አለው፡፡ የማሰብ፤ ምክንያት የመሥጠት እና የማቀድ (ኢሳያስ 1፤18)፡፡

2.ስሜት አለው፡፡ ስሜቱ ይነካል (ዘፀአት 4፤14፤ ኤፌሶን 4፤30)፡፡

3.ፍቃድ አለው-ድርጊትን የመምረጥ ችሎታ አለው (ዘፍጥረት 1፤3)፡፡

እግዚአብሔር ሥላሴ ነው፡፡ እርሱ አንድ አምላክ ሆኖ በሶስት እራሳቸውን በቻሉ መለኮታዊ
ሰዎች- አባት፤ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ መልክ ይገኛል (ማቴዎሰ 28፤19)፡፡ እግዚአብሔርን ምንም
አይዘውም፡፡ ከወሰንም ውጪ ሊወጣ አይችልም፤ ህልውናው በድንበር በሚታይ ነገር፤ በሚታወቅ
ኃይል፤ በነፍስ፤ በመንፈስ፤ በአስተሳሰብ፤ በስሜት፤ በቦታ ወይም በማንኛውም ነገር ወይም ክስተት
ወይም ከሰዎች ባህርይ ውጪ የሆነ ወይም የተፈጥሮ አለም ሊገድበው አይችልም (1ኛ ነገስት 8፤27)፡፡

እግዚአብሔር ዘላለማዊ ነው፡፡ እርሱ የመኖሪያ ዘመኑ ሳይቋረጥ ወይም ያለፈው፤ የአሁኑና
ወደፊቱ ዘላለማዊነት ሳይገደብ ይኖራል (ዘፀአት 3፤14፤ ዘዳግም 33፤27፤ መዝሙር 90፤2)፡፡

 

እግዚአብሔር የትም ቦታ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር በሁሉም ቦታና ጊዜ በሙሉ ማንነቱ በመገኘቱ
ምክንያት እግዚአብሔር አይወሰንም ፤ ሁሉ ቦታም ይገኛል (መዝ 139፤7-10)፡፡

እግዚአብሔር ኃያል ነው፡፡ እርሱ የማይለካ ኃይል ያለውና ሁሉንም ነገሮች በራሱ የኃያልነት
ባህርይ የሚሰራ ሲሆን ይህ ግን ከባሕሪው የሚቃረኑ ነገሮችን አያጠቃልልም፡፡ ለምሣሌ እግዚአብሔር
እግዚአብሔር መሆኑን ማቋረጥ አይችልም (መዝሙር 90፤2)፤ ኃጢአትም አይፈትነውም (ያዕቆብ
1፤13)፤ ቃሉን አያጥፍም (ዘኁልቁ 23፤19፤ 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፤13)፤ አይዋሽም (ዘኁልቁ 23፤
ዕብራውያን 6፤18፤ ቲቶ 1፤2)፡፡ እግዚአብሔር አዋቂ ነው፤ እርሱ የሁሉን ነገር እውነተኛ እውቀት
ያለውና ገና ያልተበጀውንና ወሰን የሌለውን ግዛት ሁሉ ሁሌ የሚያውቅ ነው (መዝሙር 139፤16 ፥

ሐዋሪያት ሥራ 15፤18 ፥ ዕብ 4፤13)፡፡ እግዚአብሔር ትክክል፤ ሙሉእ እና ስህተት የሌለበት ነው
(ማቴዎስ 5፤48)፡፡

እግዚአብሔር ፍቅር ነው (1ኛ ዮሐንስ 4፤8፥16)፡፡ የእግዚአብሔር ባህሪ መሠረቱ ፍቅር ነው፡፡

ስለዚህ የእርሱ ዘላለማዊ ፍላጎት ሰውን መባረክ ነው(ዮሐንስ 3፤16፥ 15፤13፥ 1ኛ ዮሐንስ 4፤10)፡፡

እግዚአብሔር ብርሃን ነው (1ኛ ዮሐንስ 1፤5)፤ በባሕርይውም እግዚአብሔር የመንፈሳዊ ብርሃን ሁሉ
ምንጭ ነው፡፡ እግዚአብሔር አይለወጥም፤ ዘላለማዊ ባህርይው የማይለዋወጥ እና ፅኑ የሆነው መንፈሱ፤
ባህርይው፤ድንጋጌው፤ ቃል ኪዳኑ ሁሉ የእርሱን ባህርይ ያመለክታሉ (ሚልክያስ 3፤6 ፥ ያዕቆብ
1፤17)፡፡ እግዚአብሔር የሁሉ ነገር ፈጣሪ ነው፡፡ ፈጣሪ የሚለው አንዱ የእግዚአብሔር መለያው
ብቻ ሳይሆን ከማዕረጎቹ ውሰጥ አንዱ ነው፡፡ ሁሉን ነገር የፈጠረው በዚህ ከፍጠረት በተለየው ባህርይው
ነው፡፡ በፍጥረት ህግ ፈጣሪና የተፈጠረ ሲኖር እግዚአብሔር ግን የሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱ ከሁሉም
ፍጥረታት በፊት ነበረ፤ ሁሉንም ፈጠረ (ዘፍጥረት 1፤1፥ ቆላስይስ 1፤16)፡፡ የእግዚአብሔር የፍጥረት
ዝርዝር በፍፁም ተገልፆ አያልቅም፡፡ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ አንተ ያደረከው ድንቅ ነገር ብዙ ነው፤
ለእኛ ያደረከውን ሊዘረዝርልህ የሚችል ማንም የለም፤ ላውራው ልናገረው ብል፥ ስፍር ቁጥር
አይኖረውም (መዝ 40፤5)፡፡

ሀ. የእግዚአብሔር አባትነት
የእግዚአብሔር አባትነት የመጀመሪያው ማንነቱ ነው፡፡ በገላትያ 1፤3 ላይ ከአባታችን
ከእግዚአብሔር ከተቀባው ጌታ ከእየሱስ ክርሰቶስም ፀጋና ሠላም ለእናንተ ይሁን በማለት የእግዚአብሔርን
አባት መሆን ይገልፃል፡፡ እግዚአብሔር ሙሉ ፈጣሪ ነው፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 8፤6 እንደተጠቀሰው ለእኛ
ግን ሁሉም ነገር ከእርሱ የሆነ፤ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ አምላክ አብ አለን፤ ደግሞም ሁሉም ነገር
በእርሱ አማካይነት የሆነ፤ እኛም በእርሱ አማካይነት የሆን አንድ ጌታ እየሱሰ ክርስቶስ ደግሞ አለን፡፡

በያዕቆብ 1፤17 ላይ እነደተጠቀሰውም በጎ ሰጦታና ፍፁም በረከት ሁሉ ከላይ ከሠማይ ብርሃናት አባት
ይወርዳሉ፤ በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ ከመዞር የተነሳ የሚያርፍ ጥላም የለም፡፡

አባት ሰው ነው፡፡ ያስባል፤ ስሜትና ፍቃድ አለው፡፡ በዮሐንስ 3፤16 እንደተጠቀሰው በእርሱ
የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ
መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዷልና፡፡ የሰው ልጆችን ለማዳንና በተመሳሳይም ፍትህን ለማስፈን
የተለየ ችሎታን ይጠይቃል፡፡ እርሱ ለዓለም ካለው ፍቅር የተነሳ እግዚአብሔር ስሜት እንዳለው መረዳት

እንችላለን፡፡ ሐጢአተኞችን ለማዳን አንድያ ልጁን መስዋዕት ማድረጉ መንፈሰ-ጠንካራነት ፍቃድ
እንዳለው ያሳያል፡፡ መጽሐፍት የእግዚአብሔርን አባትነት በስድስት መልኩ ይገልፀዋል፡፡

እግዚአብሔር የጌታ እየሱስ ክርስቶስ አባት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ህግ አውጃለሁ፤ እርሱም
እንዲህ አለኝ፤ ‘‘አንተ ልጄ ነህ፤ እኔ ዛሬ ወለድሁህ’’ (መዝሙር 2፤7)፡፡ ዮሐንስ 5፤26 እና
መዝሙር 2፤7 ላይ የተፃፈውን ሲያብራራው አብ በራሱ ሕይወት እነዳለው ሁሉ፤ ወልድም በራሱ
ሕይወት እንዲኖረው ሠጥቷልና ይላል፡፡ ዶ/ር ሉዊስ ቻፈር ይህንን እውነት እንዲህ በማለት ይገለፀዋል፤
ይህ መጀመሪያ ያለውን የምድራዊ ሰዎችን ህይወት አይወክልም፡፡ ነገር ግን ይህ ህይወት እግዚአብሔር
የሰጠውን ዘላለማዊ ህይወትን ይወክላል እንጂ፡፡ ይህንን ዘላለማዊ ህይወት እግዚአብሔር ለልጁ ሰጠ፡፡

የወለድኩት ልጄ የሚለው እግዚአብሔር ወልድን ባለፈው ዘላለማዊ ጊዜ ውስጥ እንደፈጠረው እና
የእየሱስ ክርስቶስን ሰው ሆኖ ከሰው መፈጠር አያመለክትም፡፡

የስነ መለኮት ምሁራን ይህንን የእየሱስ
ክርስቶስን አፈጣጠር የተለየ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ይህም ወልድ ከሰማይ አባቱ ጋር ያለው ግንኙነት የተለየ
እንደሆነ ያሳያል፡፡ አንዳንድ የስነ መለኮት ምሁራን እግዚአብሔር አባት ወልድን በዘላለም ጊዜ ውስጥ
ፈጠረው ብለው ያምናሉ፡፡ ምንም ይሁን ምን ወልድ ከመለኮታዊ አባቱ ጋር የተለየ እና በፍፁም
የተቀደሰ ግንኙነት አለው፡፡ በዮሐንስ 1፤18፥ 3፤16ና በ1ኛ 4፤9 ውስጥ የሚገኘው የወለድኩት ልጄ
የሚለው ፅንሰ ሃሳብ ይህንን ይገልፃል፡፡

2. አግዚአብሔር በ1ኛ ቆሮንቶስ 8፤6 እና በያዕቆብ 1፤17 ላይ እንደተገለፀው የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ
ነው፡፡ በመሆኑም እርሱ ራሱ የበላይ ሆኖ የሚያስተዳድር ነው፡፡ በኢዮብ 9፤5-7 እንደተገለፀው “እርሱ
ሳያውቁት ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤ በቁጣው ይገለብጣቸዋል፡፡ ምድርን ከስፍረዋ ያናውጣታል፤
ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል፡፡ ፀሓይን ያዛታል፤ አትወጣምም፤ ክዋክብትንም በማህተም ያሽጋል”
ይላል፡፡

3. እግዚአብሔር መላእክትን ስለፈጠራቸው አባታቸው ነው (ቆላሳይስ 1፤16)፡፡ እነርሱም
የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉ (ዘፍጥረት 6፤2 እና ኢዮብ 1፤6፥ 2፤1 እና 38፤7)፡፡

4. እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረ (ዘፍ 2፤7፥ ሐዋ ሥራ 17፤9፥ 26-29፤ ኤፌ 3፤14-15፥ ዕብ 12፤9)፡፡

5. እግዚአብሔር እስራኤልን መረጦ ወደ ተለየ ከፍታ ስላሻገራት አባቷ ነው (ዘፀአት 4፤22፥ ዘዳግም

6. እግዚአብሔር በልጁ ለሚያምኑ ሁሉ አባት ነው (ማቴዎስ 5፤45፥ 6፤6-15፥ ዮሐንስ 1፤12፥ ሮሜ

7፤6፥ 32፤6፥ ኢሳይያስ 64፤8፥ ሆሴዕ 11፤1፥ ሚልኪያስ 1፤6)፡፡

8፤14-16፥ 1ኛ ዮሐንስ 3፤1)፡፡

ከሶስቱ ስላሴዎች መካከል የእግዚአብሔር ባህርያት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1. እርሱ በዘላለማዊነቱ ዘላለማዊ ወልድን ፈጥሯል (ዮሐንስ 5፤26)፡፡

2. እርሱ ልጁን መባረክ ይባርካል (መዝሙር 2፤7-8)፡፡

3. እርሱ ወልድ ምን መስራት እንዳለበት እና ወልድ ለሰራቸውም ይሁን ለሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ
እውቅና ይሰጣቸዋል (ዮሐንስ 5፤19-20፥ 22፤36)፡፡

4. እርሱ ወደፊት ተከስተው እንዲያልፉ የሚፈቅደውን ድንጋጌዎችን ያወጣል (መዝ 2፤5-7)፡፡

5. እርሱ የሰዎችን ፍቃድ ሳይጋፋ በመሲሁ አምነው የሚድኑትን ይመርጣል (ኤፌ 1፤3-6)፡፡

6. ለሰው ልጆች አባት በመሆኑ የሰዎችን መንፈሳዊ ፍላጎት ልጁን ለሐጢአተኞች መስዋዕት በማድረግ

የድነትን ስጦታዎች ይሰጣል (ዮሐንስ 3፤16፥ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፤19-20፥ 2ኛ ጴጥሮስ 3፤9)፤ ለኑሮ
የሚያስፈልጋቸውንም ይሰጣል (የሐዋርያት ሥራ 14፤7) ምንም እንኳን መቼ እርሱን ወደ ማወቅ
መምጣት እንዳለባቸው ቢያስተምራቸውም (ህዝቅኤል 38፤16)፡፡

7. በልጁ በማመን አባት ለሆነላቸው ለስጋቸው የሚስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል (ማቴዎስ 6፤25-33) ፤
በመንፈሳዊ ህይወታቸውም በሁሉ አቅጣጫ ሣያቋርጡ እንዲያድጉ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ ይሰጣቸዋል
(ዕብራውያን 12፤6-7፥ ፊልጵስዩስ 1፤6)፡፡

ለ. እግዚአብሔር ወልድ
የእግዚአብሔርነት ሁለተኛው አካል ወልድ ነው፡፡ ወልድ እግዚአብሔር ነው (ዮሐንስ
1፤3)፤ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሯል፤ ከተፈጠረውም ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ ምንም የለም፡፡

በቆላስይስ 1፤16 ላይ እንደተገለፀው ገና ማሪያም ሳትወልደው በወልድ ባሕርይ ውስጥ የማሰብ ችሎታና
ፍቃድ ነበረ፡፡ ሌለኛው ባህርይውን የተላበሰው ግን በመዝሙር 40፤8 ላይ አምላኬ ሆይ ፍቃድህን
ላደርግ እሻለሁ፤ ህግህ በልቤ ውስጥ አለ ብሎ የእግዚአብሔርን ፍቃድ ሲፈፀም በዮሐንስ 11፤35 ላይ
ልቡ በሀዘን ተመትቶ ሲያለቅስ ወልድ ሥሜት እንዳለው ያሳያል፡፡

ሁለተኛው የስላሴ አካል ባለፈው ዘላለማዊ ውስጥ በመዝሙር 40፤8፥ በዮሐንስ 3፤13 እና
ሌሎች መላእክቶች ላይ የተገለፀው ወልድ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ለማሪያም ልጅ (ኢሳይያስ
7፤14) ለእየሱስ ክርስቶስ ስጋዊ አባቱ አይደለም፡፡ ቅዱስ መንፈስ በማሪያም ማህጸን ውስጥ ያለ ሥጋ
ፍቃድ የተፈጠረውን ፍሬ በማሳደግ (ሉቃስ 1፤31፥ 34-35) ዘላለማዊው ሰው ወልድ ከሰው ሥጋ
ተወለደ (ኢሳይያስ 9፤6)፡፡ ሥጋ በለበስ ጊዜ ወልድ መለኮታዊ ክብር በመጎናፀፉ ፍፁም መንፈስና
ፍፁም ስጋ ለባሽ በመሆን ለጥቂት ጊዜ በአካሉ ፍፁም መለኮትነት አልሆነም (ቆላስይስ 2፤9)፡፡

ነገር ግን 
ከስላሴዎች ከአብ እና መንፈስ ቅዱስ ጋር እኩል ዘላለማዊ፥ የትም ቦታ የሚገኝ፥ ሁሉን አዋቂ እና
ሁሉን ቻይ ሳይሆን አልቀረም፡፡ ሠው የሆነው እየሱስ ሐጢአተኛ እንደሆኑት ሠዎች ሁሉ ሳይሆን ምንም
የኃጢአት ባህርይ ያልተገኘበት (ሉቃስ 1፤35)፤ በሃሳቡም፥ በቃሉና በድርጊቱም ኃጢአት የሌለበት ነው
(ዮሐንስ 8፤46)፡፡ ስለ ሐጢአታችን በሥጋው የሞተው (ዮሐንስ 19፤1-31)፤ ከሞት የተነሳውና በክብር
ያረገው ክርስቶስ ነው፡፡

የተለያዩ የወልድ ባህርያት እንደሚከተለው ተጠቃለው ቀርበቃል፡፡

1. እርሱ ለመለኮታዊ አባቱ አግልጋይ ነው (ኢሳይያስ 42፤1፥ 53፤11)፡፡

2. እርሱ የመንፈስ ቅዱስን አገልግሎት ወደ ደቀ መዛሙርት ይመራል( ዮሐንስ 16፤13-15)፡፡

3. አምላክ የሆነና ስጋ የለበሰ እርሱ ወልድ ብቻ ነው (ሉቃስ 1፤35)፡፡

4. ሰዎችን ከኃጢአት በደሙ የሚያነፃ እርሱ ብቻ ነው (ገላትያ 3፤13፥ 1ኛ ጴጥ 1፤18-19)፡፡

5. እርሱ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው (ኤፌሶን 5፤23)፡፡

6. እርሱ በእግዚአብሔር ዙፋነ ፊት ለቅዱሳን ሁሉ ይማልዳል (ዕብራውያን 7፤24-25)፡፡

6. እርሱ በሺ ዓመት ዘመን ምድርን ሁሉ ይገዛል (መዝሙር 2፤1-6)፡፡

7. እርሱ መለኮታዊ ዳኛ ሆኖ (ራእይ 5፤22) ቅዱሳን ዙፋኑ ላይ በመፍረድ (2ኛ ቆሮነጦስ 5፤20)
የፍየልና የበግ ተምሳሌት ህዝቦችን በመጨረሻው የታላቁ መከራ ዘመን (ማቶዎስ 25፤31-46) ያላመኑ
ሙታኖችም በነጭ ዙፋኑ ላይ በመሆን ይፈርዳል (ራእይ 20፤10-15)፡፡

 

ሐ. እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ
የእግዚአብሔርነት ሶስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ቅዱስ መንፈስ እግዚአብሔር
(ዘፍጥረት 1፤2) ስለሆነ መለኮታዊ ሥልጣኑን ይጠቀማል (ሐዋሪያት ሥራ 13፤2)፡፡ መንፈስ ቅዱስም
እንደ አብ እና ወልድ የማሰብ ችሎታ፤ ስሜትና ፍቃድ አለው፡፡ በሮሜ 8፤26 ላይ እንደተገለፀው
መንፈስ በድካማችን ያግዘናል፥ እንዴት መፀለይ እንደሚገባን አናውቅም፥ መንፈስ ግን በቃላት ሊገለጥ
በማይችል መቃተት ለእኛ ስለሚያግዘና ስለሚማልድ አማላጅነት የማሰብ ችሎታ እንዳለው ያሳየናል፡፡
በኤፌሶን 4፤30 ላይ የእግዚአብሔርን ቅዱስ መንፈስ እንደሚያዝንና ይህም መንፈስ ቅዱስ ስሜት
እንዳለው ያሳያል፡፡ እርሱ መንፈሳዊ ስጦታዎችን ለአማኞች በፍቃዳቸው ላይ ተመስርቶ ያከፋፍላል፤
ነገር ግን ይኸው አንዱ መንፈስ የተላያዩ ስራዎችን ይሰራል (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤11)፤ ስለዚህ ፍቃድ
አለው ማለት ነው፡፡

የመንፈስ ቅዱስ ከወልድ እና አብ የተለዩ ባህርያት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡

1. እርሱ የእግዚአብሔር አገልጋይና ልጅ ነው (ዮሐንስ 14፤26፥ ዮሐንስ 16፤13-14)፡፡

2. ያላመኑትን በሐጢአት እየወቅሰ በመሲሁ በማመን የሚገኝን ፅድቅና በማያምኑት የሚጣን ዘላለማዊ
ፍርድ በማሳየት ሰዎችን ስለ ሐጢአታቸው ይወቅሳል (ዮሐንስ 16፤8)፡፡

3. በጌታ የሚያምኑትን ያፀድቃቸዋል (ዮሐንስ 3፤6-7)፤ በውስጣቸውም ይኖራል (ዮሐንስ 14፤16-17)፤
በጌታ ላመኑትን ዋስትና ይሆን ዘንድ ያትምባቸዋል (ኤፌሶን 4፤30)፤ ወድ ክርስቶስ አካልነት
ያጠምቃቸዋል (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤13)፤ መንፈሳዊ ስጦታ ይሰጣቸዋል (1ኛ ቆሮንቶስ 12፤7-8)፤
ይመራቸዋል (ገላትያ 5፤18) ለቅድስና ኑሮ ኃይል ይሰጣቸዋል (ሮሜ 8፤14)፤ በአማኞች እራሱን
በመሙላት ለጌታ ፍቃድ እንዲገዙ ያደርጋል (ኤፌሶን 5፤18)፡፡

መ. የሦስቱ እኩልነት
ወልድ የአብ አገልጋይ፥ መንፈስ ቅዱስ የሁለቱም አገልጋይ ቢሆንም፤ ሶስቱም በእኩል ደረጃ እና
የአምላክነት ክብር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለዚህ ሂዱና አህዛብን ሁሉ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም
እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው (ማቴዎስ 28፤19) ይላል፡፡

ሠ. የሦስቱ ህብረት ወይም የሥላሴዎች እግዚአብሔርነት
ዘዳግም 6፤4 እንደተገለፀው እስራኤል ሆይ ስማ እግዚአብሔር አምላካችን አንድ አምላክ ነው፡፡
በእብራይስጥ ይህ አንድ የሚለው ቃል ኤቻድ ይባላል፡፡

በብዙ መልኮች ኤቻድ የሚለው ቃል ፍፁም
አንድ መሆንን ሲያመለክት በዘፍጥረት 10፤25 እንደተገለፀው ደግሞ አንድ የሚለው ቃል ፔልግ
ይባላል፤
አንዳንድ ጊዜ ግን ኤቻደ አንድ አካል ቢሆንም ብዙ ክፍሎች ያሉት አንድ አካል እንደ ሆነ
በዘፍጥረት 2፤24 ላይ ተገልጿል፡፡ በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፤16 ላይ የተቀመጠውና በዘፍጥረት 2፤24 ላይ
ያለው ኤቻድ ከአንድ በላይ ክፍሎች አሉት፡፡ ከጋለሞታ ጋር የተኛ ከእርሷ ጋር አንድ አካል እንደ ሆነ
አታውቁምን? ይላል፡፡ ሁለቱ አንድ አካል ይሆናሉ ተብሎ ተፅፏልና (ማቴዎስ 19፤4-6 )፤ ማርቆስ
10፤9 ደግሞ ከጋብቻ ጋር አዝምዶ ቢገልፀውም ከላይኛው ሃሳብ ጋር ተመሳሳይ መላእክት አለው፡፡

በመሆኑም ባልና ሚስት ኤቻድ ናቸው፤ ምንም እንኳን የተለያዩ አካልና መንፈሳዊ አቋም
ቢኖራቸውም፡፡ ስለዚህ ኤቻድ ከሁለት በላይ ሆነው ለተጣመሩ አካላት መጠሪያነት ያገለግላል ማለት

ነው፡፡

እዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን በዘዳግም 6፤4 ላይ የኤቻድን ስሜ ያገኘው ቃል ማንን
እንደሚገልፅ መገንዘቡ ላይ ነው፡፡ ይህ ቃል ጆሆቫን እንደ አንድ አምላክ ወይስ እንደ ብዙ ይገልፀዋል?
እነዚህን ነጥቦች እንመልከት፡፡

1. መጽሐፍ ቅዱስ ሶስት መለኮታዊ አካላት እንዳሉና አንድ ብቻ እንደ ሆኑ አይገልፅም፡፡

2. የያህዌ ስያሜ ከሶሰቱ አካላት ለአንዱ የተሰጠ ነው (ዘፍጥረት 19፤24፥ ዘካርያስ 2፤8-9)፡፡

3. ያቺድ የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ሁል ጊዜ በፍፁም አንድ ለሆነ አካል ይሰጣል፡፡

4. አብረሃም ብዙ ልጆች ቢኖሩትም በዘፍጥረት 22፤2 ሙሴ ኤቻድን ሳይሆን ያቺድ የሚለውን ቃል
የተጠቀመው ፍፁም አንድ ስለሆነው የአብረሃም ብቸኛ ልጅ ስለሆነው ስለ ይስሃቅ ነው፡፡

5. ሙሴ ያቺድ የሚለውን ቃል ፍፁም አንድ ለሆነ አካል መጠቀም ነበረበት-በያቺድ ፈንታ ኤቻድን
ተጠቅሟልና፡፡

በመሆኑም ሙሴ ኤቻድን ከያቺድ ይልቅ መጠቀሙ አንዱ አካል በዘዳግም 6፤4 ላይ
እንደተገለፀው ብዙ ክፍሎች ስላሉት ያህዌ ነው ብሎ ማጠቃለል ይቻላል መለት ነው፡፡ ሦስቱ አካላት
አንድ ናቸው፤ ነገር ግን አንድ የመሆናቸው ምክንያት ምንድ ነው? በዮሐንስ 10፤30 እንደ ተገለፀው
እየሱስ እኔ እና አብ አንድ ነን በማለቱ አንድነታቸው በዚህ ቦታ ላይ ተገልጿል፡፡ ይህንን ጉዳይ ዶ/ር
አርኖልድ ገ. ፍሩክተንባውም አብ እና ወልድ በመለኮት አንድ መሆናቸውን ይፅፈዋል፤ ይህም
የመለኮታዊ ባህርይ መሆኑን ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐተታዎች ለዮሐንስ 14፤10 የመጽሐፍ ክፍል
ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ክስቶስን በተመለከተ በ2ኛ ቆሮ 3፤17 ላይ ጌታ መንፈስ እንደሆነ
ተፅፏል፡፡ ዶ/ር ቻርለስ ራይሬ በዚህ ቁጥር ላይ ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ እኩል መለኮታዊ ክብር
እንዳላቸው ገልጿል፡፡

ዮሐንስ 10፤30 እንደሚያሳው አብና ወልድ አንድ አይነት መለኮታዊ ክብር አላቸው፡፡ 2ኛ
ቆሮንቶስ 3፤17 ላይ ደግሞ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ተመሳሳይ ክብር እንዳላቸው ተገልጿል፡፡ ስለዚህ
ስላሴዎች ተመሳሳይ መለኮታዊ ክብር አላቸው ማለት ነው፡፡ ያ የመለኮታዊ ባህርይ ምንድ ነው?
እየሱስም ስለ አብ መንፈስ መሆን እግዚአብሔር መንፈስ ነው (ዮሐንስ 4፤24) በማለት አስቀምጦታል፡፡

ስለዚህ የእግዚአብሔር መለኮታዊነት መንፈስ መሆኑ ነው፡፡ በ2ኛ ቆሮንቶስ 3፤17 ላይ ጌታ መንፈስ
እንደሆነም ተቀምጧል፡፡ ስለዚህ የወልድ መለኮታዊ ባህርይም መንፈስ መሆኑ ነውል፡፡ የመንፈስ
ቅዱስ መለኮታዊነትም መንፈስ ነው-መንፈስ ስም እና ቅዱስ ደግም ቅጽል በመሆኑ፡፡ ሶስቱ ሰዎች አንድ
ናቸው የሶስቱም መሰረታዊ መለኮታዊነት ደግም መንፈስ መሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ ስላሴዎች ሶስት
መለኮታዊ አካላት ሲሆኑ ሶስቱም መለኮታዊ መንፈስ ናቸው፡፡

እዚህ ላይ አንዱ መንፈሳዊ መለኮት የሌላውን ቦታ እንደማይወስድ መገንዘብ አለብን፡፡ ይህም
በሉቃስ 3፤22 ላይ ተገልጿል፡፡ መንፈስ ቅዱስም በእርግብ አምሳል ከሰማይ ወረደ፤ ከዚያም በአንተ
ደስ የሚለኝ የተወደድክ ልጄ ነህ የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ፡፡ እዚህ ቦታ ላይ የተጠቀሱት ሶስት
አካላት የተጠመቀው ወልድ፥ ድምጻቸው ከሰማይ የመጣው መንፈስ ቅዱስና አብ ናቸው፡፡ እዚህ ላይ
አንድ ሰው በፍጹም የሌላውን ሰው ባህርይ ሊወስድ ስለማይችል ስለ ስላሴዎች መሆኑን እንረዳለን፡፡

III. መላእክት

ያልተፈጠረው እግዚአብሔር ሶስት መለኮታዊ አካላት ሲኖሩት በመጀመሪያ መላእክትን ቀጥሎ
ደግሞ ሰውን ስለፈጠረ የእነርሱን አፈጣጠር ከመላእክት ጀምሮ እንመለከታለን፡፡ በቆላስይስ 1፤16
እንደምንመለከተው ክርስቶስ መላእክትን አንዲያገለግሉት ፈጠራቸው፡፡ ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሯል፤
በሠማይና በምድር ያሉ፥ የሚታዩና የማይታዩ፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፥ ገዢዎች ቢሆኑ ወይም
ባለ ሥለጣናት፥ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሯል፡፡ ዙፋናት፥ ኀይላት፥ ገዢዎች እና ሥልጣናት
የመላእክት የሥልጣን ደረጃዎች ሲሆኑ ቁጥራቸውም ሥፍር ቁጥር የለውም (ዕብራውያን 12፤22)፡፡

በኢዮብ 38፤4-7 ውስጥ እንደተጠቀሰው እግዚአብሔር ኢዮብን እኔ የምድርን መሰረት ስመሰርት
አንተ የት ነበርክ? ሲል ገሰፀው…. ቀጥሎም ከንጋት ክዋክብት ጋር በአንድ ላይ የዘመሩትና በደስታ
የጮሁት የእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ የተባለላቸው የተወከሉት በመላእክት ነው (ራእይ 1፤20፥ 9፤1፥
12፤3-4)፡፡ የእግዚአብሔር ልጆች (ዘፍጥረት 6፤2፥ 4፥ ኢዮብ 1፤6፥ 2፤1) እና የመጽሐፍ ቅዱስ
ክፍሉ በግልፅ እንደሚያሳየው እነዚህ የእግዚአብሔር መላእክት የተፈጠሩት ዓለም ሣይፈጠር በፊት
ነው፡፡ መላእክት እንደማይራቡ እንጂ (ማርቆስ 12፤25) መቼ እንደተፈጠሩ በመጽሐፍት የተገለፀ ነገር
ባይኖርም የተፈጠሩት ግን ሰማይና ምድር ከመፈጠራቸው በፊት ነው፡፡

ማጠቃለያ
አማልዕክት መናፍስት ናቸው (ዕብራውያን 1፤13-14)፤ እንደ ሰውም ያስባሉ (1ኛ ጴጥሮስ
1፤12)፥ ስሜት አላቸው(ኢዮብ 38፤7)፤ ፍቃድም አላቸው (ይሁዳ 1፤6)፡፡ የተቀደሱ ናቸው (ሉቃስ
9፤26)፥ አይሞቱም (ሉቃስ 20፤36)፤ ኃይልም አላቸው (2ኛ ዜና 32፤21)፡፡

እግዚአብሔር ሶስት መደብ መላእክትን ፈጠረ፡፡
1. ኪሩብ የሚባሉት መላእክት ከፍተኛ ማዕረግ ያላቸው ከእግዚአብሔር ህልውናና ክብር ጋር የሚኖሩና
(ሕዝቅኤል 1፤26-28፥ 9፤3፥ 10፤1-22) ከዙፋኑ ስር የሚያሸበሽቡ እርሱንም የሚጠብቁ (ዘፍጥረት
3፤24) ናቸው፡፡

2. ሴራፊም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ያሉ መላእክት ናቸው፡፡ ኢሳይያስ 6፤2-3 እንደሚያሳን እነዚህ
መላእክት ከእግዚአብሔር ዙፋን በላይ ሆነው እርሱን ያመልኩታል ፤ አርሱ የጠራቸውንም ይቀድሳሉ
(ኢሳይያስ6፤5-7)፡፡

ራእይ 5፤8-10፥14 እንደሚያሳየው ደግሞ እነዚህ መላእክት በጉን ያመልኩታል፤
በታላቁ የመከራ ዘመንም የእግዚአብሔርን ፍርድ በሚነደው እሳት ውስጥ ይፈፅማሉ (ራእይ 6፤1-7 እና
ራእይ 15 እና 16) ፡፡

3. አማልዕክት በሶስተኛና በመጨረሻው ምድብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የሰማይ ሠራዊት ሲባሉ
ሚካኤልም መሪያቸው ነው (ራእይ 12፤7)፡፡ በዳንኤል 10፤13-21 ላይ እንደተገለጸው ሚካኤል
በእስራኤል ላይ የተለየ ተቆጣጣሪ እና በዳንኤል 8፤15-27፥ 9፤20-27 እና ሉቃስ 1፤11-38
እንደተገለፀው መላዕኩ ገብርኤል የእግዚአብሔር መላእክተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡

ሴራፊም እና ኪሩቤል በብዙ ባህሪቸው እንደ ሰው የተከሰቱና በሌሎች ክፍሎች ደግሞ በንጉሳዊ
የመስዋዕት ሥነ ስርዓት እንደሚቀርቡ ንፁህ እንስሳት ተወክለዋል (ሕዝቅኤል 1፤5-28፥ ራእይ 4፤6-
11)፡፡ ሴራፊም ሶስት ጥንድ ክንፎች አላቸው (ኢሳይያስ 6፤2)፤ ኪሩቤል መላእክት ደግሞ አንድ ጥንድ

ክንፍ አላቸው (1ኛ ነገስት 6፤23-28)፡፡ የሶስተኛዎቹ ክፍል መላእክት ምድር ላይ ሲከሰቱ ወንድ
ወጣቶችና ክንፍ የሌላቸው በመሆን ነው (ዘፍጥረት 18፤1-2፥ 16-18፥ ማርቆስ 16፤5)፡፡

መላእክት ህፃናትን እንዲጠብቁ ተመድበዋል (ማቴዎስ 18፤10)፡፡ እነርሱ በጌታ የሚያምኑትንና
ቤተ ክርስቲያንንም እንዲጠብቁ ቢመደቡም የእግዚአብሔርን አገልግሎትና ጥሪ እንዲፈፅሙ መላአእክቱ
ያገለግሏቸዋል (መዝሙር 34፤:7፥ 91፤11-12፥ የሐዋርያት ሥራ 8፤26፥ 12፤7-11፥ 27፤21-26፥
ራእይ 1፤1፥ 2፤1፥ 8፥12፥ 18፥ 3፥1፥7፥14)፡፡ መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል
የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን (ዕብራውያን 1፤14) ?

ከዚህ በፊት እንደተመለከትነው
ሚካኤል የእስራኤል ጠባቂ ነው፡፡

አንድ በምድር ላይ በተለያዩ ጊዚያት የተገለፀ ያህዌ የሚባል መላእክ (ዘፀአት 3፤2፥4) ይገኛል፡፡

ይህ በተለያዩ ክፍሎች ውስጥ ያህዌ የሚባለው እግዚአብሔር ነው፡፡ በዘካርያስ 2፤8-9 ጆሆቫ የሚባሉት
አብና ወልድ ሲሆኑ እንግዲህ ጥያቄው እግዚአብሔር የተባለው ጆሆቫ የቱ ነው? በዘፀአት 3 እና 4
እንደተገለፀው እርሱ እስራኤልን ከግብፅ ያወጣና በቀይ ባህር ውሰጥ በደረቅ ምድር ያሻገረው በ1ኛ
ቆሮንቶስ 10፤1-4 ላይ የተገለፀው ዘላለማዊው ክርስቶስ እርሱ ጆሆቫ ነው፡፡ የዚህ ጆሆቫ የተባለው
መላእክ የተለየ አገልግሎቱ ምንድነው?

የመጽሐፍ ቅዱስን ክፍሎች ስንመረምር እርሱ የእስራኤልን ታሪክ ያስዋበና ታሪክ የሆናቸው
እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በእርግጥ እርሱ ከአብረሃም እስከ ክርስቶስ የመስቀሉ ሥራ ድረስ ያለውን ታሪክ
ጎለቶ እንዲታይ ያደረገ ነው፡፡ እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ የእግዚአብሔር መላእክ ይስፍራል፥
ያድናቸዋልም (መዝሙር 34፤7) ስለሚል፡፡ ይሁንና ይህንን መላእክ በዚህ ዘመን የቤተ ክርስቲያን
አገልግሎት ውስጥ ጎልቶ አናየውም፡፡

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ጉዳይ መላእክትን ማምለክና ወደ እነርሱ መፀለይ እንደማያስፈልግና (ቆላስይስ
2፤18፥ ራእይ 19፤10፥ 22፤8-9) ወደ አብ ብቻ መፀለይ እንዳለብን (ማቴዎስ 6፤9) መረዳት
አለብን፡፡

IV. ሠይጣንና አጋንንቶች

ቅዱሳን መላእክት ስፍር ቁጥር የሌላቸው

መሳሪያዎች እርሱ በተፈጠረበት ቀን የተፈጠሩ መሆናቸውን ያሳያል፡፡ እነዚህን የሙዚቃ መሳሪያዎች
በውስጡ በመያዝ ከእግዚአብሔር ዙፋን በላይ የነበረው ሴራፊም (ኢሳይያስ 6፤2)ና ኪሩቤል (ሕዝቅኤል
10፤1) የአማልክት ሁሉ መሪዎች ሆነው እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ሠይጣን
በእግዚአብሔር ላይ በማመፁ ምክንያት እርሱንና ተከታዮቹን ከሰማይ ወደ ምድር ከባቢ አየር
ተወረወሩ፡፡ በመሆኑም የአሁኑ የሠይጣን ስልጣን የአየር አለቃ ነው (አፌሶን 2፤2)፡፡ ሠይጣን
በእግዚአብሔር ላይ ካመፀ በኋላ በእነዚህ ስያሜዎች ይታወቃል፡፡
1.

የሠይጣን ባህርይ
ክፉ ነው (ማቴ 6፤13፥ ዮሐንስ 17፤15፥ 2 ተሰሎንቄ 3፤3፥ 1ኛ ዮሐንስ 5፤18-19)፡፡ እርሱ
ተፅእኖ በሚያሳድረውና በሚሰራው ስራ ሁሉ ሙሉ በሙሉ ከፉ ባህርይ አለው፤ ባለጋራም
ነው፡፡ ይህ
ሥያሜውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሃምሳ ጊዜ በላይ ተፅፎ ሲገኝ የእግዚአብሔር፥ የአማኞችና
የሰዎች ሁሉ ባለጋራ ነው (1ና ዜና 21፤1)፡፡

2.

ዓላማው
የሚደመስስ፥ የጥልቁ ጉድጓድ መላእክ (አብዶን)፥ የጥልቁ ገዢ (ኦጶልዮን) (ራእይ 9፤11)
ነው፡፡ ይህ ገዢ በአሰቃቂዎቹ አንበጦች/ አጋንንቶች ላይ ንጉስ ነኝ በማለት (ራእይ 9፤1-10)
የእግዚአብሔርን እቅድ ማበላሸት፥ እራሱን መሲሁ ነኝ በማለት ሰውነ በማሳሳት እንደሚያገሳ አንበሳም
ክርስቲያኖችን እየዞረ (1ኛ ጴጥሮስ 5፤8) እምነትንና የአማኞችን አካሄድ ያበላሻል፡፡

3. ዓላማውን የሚያሳካባቸው መንገዶች
በመፈተን (ማቴዎስ 4፤3፥ 1 ተሰሎንቄ 3፤5)፡፡ ይህ መታወቂያው የተሰጠው ሰዎችን ለኃጢአት
ፈተና በማባበሉ ምክንያት ነው፡፡ ሠይጣን አታላይ ነው፡፡

ሠይጣን የዓለም አታላይ በመሆኑ ብዙ
ሠዎችን እግዚአብሔርንና የእርሱን መንገድ እንዳይከተሉ ያሳስታል (በራእይ 12፤9) ፡፡ አማኞች
የእግዚአብሔርን ምክር እንዳይቀበሉ በማሳሳቱ ምክንያት የእርሱን ብልሃት መቃወም አለብን (ኤፌሶን
6፤11) ፡፡

የብርሃን መላእክ በመባልም ይታወቃል (2ኛ ቆሮንቶስ 11፤14)፡፡ ይህ ስያሜ የሚያሳየው ሠይጣን
የማታለሉን ሥራ የሚሰራው እውነተኛውን ግብረ ገብ እና መንፈሳዊ መረዳት በውሸትና በልመና ዓለም
የተሞላችበትን የሌጊዮን ሀሰተኛ ሀይማኖት፥ ፍልስፍና፥ እምነት እና አመለካከት በመስጠት ነው፡፡
ሌለኛው ስያሜው ሠይጠን

ሲሆን ይህም ከሣሽ ወይም ሐሜተኛ በእግዚአብሔርና በእግዚአብሔር
ሰዎች መካከል እንዲሁም በእግዚአብሔር ሰዎች መካከል መከፋፈልን ይፈጥራል፡፡ከሳሽነቱም በአዲስ
ኪዳን ውስጥ ብቻ ሲገኝ ሰላሳ አምስት ጊዜም ተጠቅሷል፤ (ራእይ 12፤10፥ ኢዮብ 1፤9-11ና 2፤5)
ኢዮብንም በፊቱ ከሧል፡፡
4.

ሁኔታዎችን ሁሉ እነዴት እንደሚጠቀም
ሠይጣን እባብ በሚባል ስያሜ እንደተጠቀሰ በአስር የመጽሐፍ ክፍሎች ውስት ሲገኛ በተለይም በዘፍጥረት
3፤1 ላይ እንዴት በብልጠቱ እና በተንኮሉ ሔዋንን እነዳሳሳታት ማንበብ ይቻላል፡፡ በራእይ 12 ላይ
ደግሞ ድራጎን ተብሎአል፡፡ ይህ ስያሜው ሠይጣን ያለውን ታላቅ ኃይል በመጠቀም የጌታ ልጆችን
እንደሚያሳስት (ማቴዎስ 2፤ ራእይ 12፤4) ወደፊትም ይህንን ኃይሉን በመጠቀም ሴቲቷን፥ ህፃኑ
የተወለደበትን የእስራኤል ነገድ (ራእይ 12፤13) ያሳስታል፡፡

 

ሀ. የአሁኑ የሠይጣን ሥልጣን
ሀ. ከሌሎች አጋንንቶች አንፃር ያለው ቦታ
የአጋንንቶች ልዑል የሚባል ሲሆን ይህ ስያሜው በማቴዎስ 12፤24 እና ሉቃስ 11፤15 ማየት
እንደምንችለው ሥላጣኑ በሌሎች አጋንንቶች ሁሉ ላይ መሆኑን ነው፡፡ የአየሩ ኃይላት ልዑል መሆኑንም
በኤፌሶን 2፤2 የምናገኝ ሲሆን ይህም ሠይጣን አሁን በአየር ውስጥ እንደሚገኝና ከበታቹ ያሉትን
አጋንንቶች የሚያዝ መሆኑን ነው፡፡

ለ.በአሁኑ የአለም ሥርዓት ውስጥ ያለው ድርሻ
ሠይጣን የዚህ ዘመን ገዢ በመባልም የሚታወቅ ሲሆን ይህ ስያሜው በ2ኛ ቆሮንቶስ 4፤4 ላይ
ይገኛል፡፡ ይህንንም ዓለም እንደተቆጣጠረና አገዛዙ ከክርስቶስ ተቃራኒ መሆኑን ነው፡፡

የዚህ ዓለም ልዑል፡፡ ይህ መለያው የሚገኘው በዮሐንስ 12፤31፥ 14፤30 እና 16፤11 ነው፡፡ ይህንን
ጉዳይ የግሪኩ ቃል ኮስሞስ የሚለው ሲሆን ይህም በዓለም ስርዓት ውስጥ ያለው ሠይጣናዊ መንፈስና
መዋቅሩ ከእግዚአብሔር መንግስት ሥርዓትና መዋቅር ጋር ሲተያይ ተቃራኒ መሆኑን ነው፡፡ በኢሳይያስ
14፤4 ላይ ደግሞ የባቢሎን ንጉስ ሲባል ይህንም ክፍል ከኢሳይያስ 14፤17 ጋር ስናመሳክረው የአህዛብ
ነገስታት ሁሉ ተቆጣጣሪ መሆኑን እንረዳለን፡፡ በሕዝቅኤል 28፤11-19 ደግሞ ሠይጣን የጢሮስ ንጉስና
የአህዛብ ነገስታት ሁሉ ንጉስም ነው፡፡

ሐ. ሥለ ሠይጣን ያሉ አመለካከቶች
ቤልሆር የሚለው ስያሜው የሚገኘው በ2ኛ ቆሮንቶስ 6፤15 ላይ ሲሆን ይህም ማለት ሠይጣን
በእግዚአብሔር እይታ የመሆን ችሎታው ወይም የሚሰራው ስራ ሁሉ የማይረባ መሆኑን ነው፡፡ በሌሎች
ክፍሎችም ሠይጣን ብዔልዜቡል
የሚባል ሲሆን ይህም
ማለት የዝንቦች ጌታ ማለት ነው (ማቴዎስ
10፤25፥ 12፤24፥ 27፥ ማርቆስ 3፤22 እና ሉቃስ 11፤15፥ 18 እና 19)፡፡ ይህም የሚያስገርም
በአይሁድ የሐይማኖት መሪዎች ለሠይጣን የተሰጠው ስም የልዑል ቤተ መንግስት ጌታ የሚለውን የግሪክ
ስያሜ ይወክላል፡፡

V. ክርሰቲያኖች ከሠይጣን ጋር የሚያደርጉት ውጊያ

የክርስቲያኖች ውጊያ ሠይጣን የሚቆጣጠረውን ዓለም (1 ዮሐንስ 2፤15-17)፥ ሥጋዊ ባህርይን
(ሮሜ 7፤5) እና ሠይጣንንና ገዚዎቹን (ኤፌሶን 6፤11-12) ያጠቃልላል፡፡ ይህ ጥናት የሚያጠቃልለው
አማኞች በሠይጣንና በገዢዎቹ ላይ የሚጠቀሙበትን ጦር ዕቃ ነው፡፡ የሠይጣን ዓላማ የእግዚአብሔርን
ሥራዎች ማጥፋት፥ ነፍሳት በጌታ አምነው እንዳይድኑ ማድረግ፥ የሙታንን ትነሳኤ መከላከል፥ ዓለማችን
ወደ ቀድሞ ክብሯ እንዳትመለስ ማድረግና በእሳት ባህር ውስጥ መኮነን እንዲሁም እግዚአብሔርን ከዙፋኑ
ላይ ማውረድና በእርሱ ቦታ እራሱን አምላክ በማድረግ መሾም ናቸው( ኢሳይያስ 14፤12-14፥ 2
ተሰሎንቄ 2፤3-4)፡፡ ይህንን ዓላማውን ለማሳካት እየሱስን ከመሰቀሉ በፊት ለመግደል አቅደ (ማቴዎስ
2፤1-18፥ 4፤1-11፥ 25፤6)፥ የጌታን ዳግም ምፃት ለማስቀረት አይሁዶችን ለማጥፋት ፈልጎ ነበር
(ዘካርያስ 13፤8፥ ማቴዎስ 23፥39፥ ራእይ 12፤6፥13-15)፥ የሰዎችን ድነት ለመከልከል መንፈሳዊ
እውር በማድረግ ነፍሳት በጌታ አምነው ሳይድኑ እንዲሞቱ ፈልጎ ነበር (2 ቆሮ 4፤3-4፥ ያዕቆብ 4፤1)ና
የቤተ ክርስቲያንን አስተሳሰብና ሥራ ማበላሸት ናቸው (ሐዋ ሥራ 20፤29-30) ፡፡

ክርስቲያኖች ለሠይጣን ውጊያ ምን አይነት ምላሽ መስጠት እንዳለባቸው፤

የክርስቲያኖች ጠላት ሰው እንዳልሆነና ሠይጣንና ተከታዮቹ መሆናቸውን በማወቅና
የእግዚአብሔርን ቃል በመሞላት አምላካዊ ሃሳቦችን ማሰብ ያፈልጋል (2ኛ ቆሮንቶስ 10፤3-5፥ ኤፌሶን
6፤10-18)፡፡ ሠይጣንንም ወደ ህይወታቸን እንዳይገባ ምንም መግቢያ ቀዳዳ ባለመስጠት መቃወም
አለብም (ኤፌሶን 4፤26-27፥ ያዕቆብ 4፤6-7፥ 1ኛ ጴጥሮስ 5፤8-9)፡፡ እየሱስ ክርስቶስ ሠይጣንን
በመቃወም እንዴት እንዳሸነፈው (ማርቆስ 8፤31-33፥ ሉቃስ 4፤1-14) ምሳሌውን መከተል
ያስፈልጋል፡፡

ክርስትያን በጌታ የማያምኑትን እነርሱን ጠላቶቻቸው አንኳን ቢሆኑ መውደድ አለባቸው (ማቴዎስ
22፤39፥ ገላቲያ 5፤14፥ ያዕቆብ 2፤8)፡፡ ለእነርሱም የእግዚአብሔርን ኃያልነት የሚያሳይ የርህራሄ
ሥራ በመስራት ማሳየት ያስፈልጋል (ማቴዎስ 14፤15-21፥ 20፤34፥ ያዕቆብ 1፤27)፡፡ ከሁሉ በላይ
የእግዚአብሔርን የማዳን ወንጌል በመስበክ ደቀ መዝሙር ማድረግ አለብን (ማቴዎስ 28፤18-20)፡፡

ሠይጣን ለሠው ልጆች ኃጢአት የሚሞተውን የእግዚአብሔር በግ ከመሞት፤ የመረጣቸውንም ወደ እርሱ
ከመምጣትና የእርሱን ምፅአት መከልከል አይችልም፡፡ ነገር ግን ጌታ የጦርነቱን ድል በእርሱ መሪነትና
ኃያልነት ጥላ ስር ለእኛ ሠጥቶናል፡፡

VI. የሰው ዘር ባህርይ

በሚቀጥለው ክፍል ውስጥ በእግዚአብሔር ስለተፈጠረው የሰው ዘር እንመለከታለን፡፡ አዳም እና
ሔዋን በዘገምተኛ የፍጥረት ለውጥ ሳይሆን የተፈጠሩት በእግዚአብሔር በራሱ ነው፡፡ የዘገምተኛ የፍጥረት
ለውጥን ክርስቲያን ያልሆኑ ሣይንቲስቶችም ሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ይህ የፍጥረት አፈጠጠር የለውጥ
ሂደት የማይቻል መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በዘገምተኛ የህይወት ለውጥና በእግዚአብሔር ፍጥረት መካከል ያሉ ልዩነቶች
1. የዘገምተኛ የህይወት ለወጥ የማይቆጠሩ ተከታታይ የሆኑ የእድገት ደረጃዎች ቢኖሩትም
የእግዚአብሔር አፈጣጠረ አንድ የእድገት ደረጃ ብቻ አለው፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ከምድር አፈር
ወስዶ ሠውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የህይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሠውም ህያው ነፍስ ሆነ
(ዘፍጥረት 2፤7)፡፡

2. እንደ ዘገምተኛ የህይወት ለውጥ አስተማሪዎች ሃሳብ የሰው ልጅ አሁን ያለበት ደረጃ ለመድረስ ብዙ
መቶ ሚሊዮን ዓመታት ፈጅቷል፤ ነገር ግን እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ እግዚአብሔር የሠውን
ልጅ በአንድ ሃያ አራት ሰዓት በሚይዝ ቀን ውስጥ በራሱ መልክ ፈጠረው (ዘፍጥረት 1፤27)…. መሸ፥
ነጋም፥ ስድስተኛ ቀን (ዘፍጥረት 1፤31)፡፡ እዚህ ላይ አንድ ቀን የሚለው የጂኦሎጂውን ቀን ሳይሆን
ሃያ አራት ሠዓት የሚይዘውን ቀን ማለት ነው፡፡ ዶ/ር ፍሩክተነባዉም እንደሚያስቀምጠው በእብራይስጥ
ስድስት ከቀን ጋር ሲያያዝ አንድ ቀን መሆኑን ያመለክታል፤ ምሽት እና ንጋትም ቀንን ይወክላሉ፡፡

ሠው የተፈጠረው በእግዚአብሔር መልክ ነው (ዘፍጥረት 1፤26-27)፡፡ ይህ አፈጣጠር የሰውን
መንፈስ እንጂ ሥጋውን ለማለት አይደለም፤ እግዚአብሔር ሥጋዊ አካል ስለሌለውና መንፈስ ስለሆነ
(ዮሐንስ 4፤24)፡፡ ይህ የሚያሳየው ሰው ብቻ ከእግዚአብሔር ጋር በመንፈሱ ህብረት ማድረግ
እንደሚችል ነው (1ኛ ዮሐንስ 1፤7)፤ ይህም የእግዚአብሔርን የዘላለማዊነት ባህርይውን ያመለክታል
(ዮሐንስ 17፤3)፡፡ በዚህ ረገድ እግዚአብሔርን የሚያመልኩት መላእክት እንኳን ከእርሱ ጋር ህብረት
የላቸውም፡፡

VII. ኃጢአት

ኃጢአት ማንኛውም የእግዚአብሔርን የትክክለኛነት እውቅትን የሚቃረን መንፈሳዊ ሁኔታ፥
አስተሳሰብ፥ ቃል ወይም ድርጊት ነው (ሮሜ 14፤23፥ ያዕቆብ 4፤17፥ 1ኛ ዮሐንስ 3፤4)፡፡ የኃጢአት
አደገኛነት የሚለካውና የሚረጋገጠው ሰው በኃጢአት ከመውደቁ በፊት ለኑሮ አመቺ የነበረችው መሬት
ከሰው ልጅ በኃጢአት ውድቀት በኋላ ለኑሮ ተስማሚ አለመሆኗን ስንገነዘብ ነው፡፡ ከሰው ልጅ
በኃጢአት ውድቀት በኋላ ህመም፥ ድህነት፥ ረሃብ፥ ስቃይ፥ ሞት፥ ጦርነት፥ ምድረ በዳነት፥ ውድመት
እና የዓለማችን ብክለት፥ የእግዚአብሔር ልጅ ለሐጢአታችን መሰቀልንና ሲሶ መላእክትና የማያምኑ
ሰዎች ወደ እሳት በህር መጣልን አስከተለ (ራእይ 19፤20፥ 20፤10፥14፥15)፡፡

እግዚአብሔር የመጀመሪያ ቤተሰቦቻችንን (አዳምንና ሔዋንን) በባህርያቸው፥ በአስተሳሰባቸው፥
በቃላቸው እና በድርጊታቸው ኃጢአት የሌለባቸው አድርጎ ቢፈጥርም እነርሱ ግን እግዚአብሔር
የሰጣቸውን አንድ ትዕዛዝ በመተላለፍ በኃጢአት ወደቁ (ዘፍጥረት 2፤16-17፥ 3፤1-6)፡፡

ሐጢአታቸውም የሚከተሉትን መዘዞች አመጣ፡፡

1. የመንፈሳቸው መበላሸት መጽሐፍ እንደሚናገር ሐጢአተኛ ሥጋዊ ባሕርይን (ኤርምያስ 17፤9፥ ሮሜ
7፤18፥23፥ ገላትያ 5፤16፥19-21፥ ኤፌሶን 2፤3) ያዘ፡፡

2. ይህ ሐጢአተኛ ሥጋዊ ባህርይ በትውልድ አማካይነት ከእየሱስ ክርስቶስ በስተቀር ወደ ሰዎች ሁሉ
ተላለፈ (መዝሙር 51፤5፥ ሉቃስ 1፤35፥ ሮሜ 5፥18)፤

3. ሰውን ከእግዚአብሔር በመለየት መንፈሳዊ ሞት አመጣ (ዘፍ 2፤17፥ 1ቆሮ 2፤14፥ ኤፌ 2፥1)፤

4. የአዳም ኃጢአት ወደ ሠዎች ሁሉ ከቤተሰብ ወደ ልጅ ሳይሆን በቀጥታ ወደ እያንዳንዱ ሰው ተላለፈ
(ሮሜ 5፤12-21 ዕብራውያን 7፤9-10)፡፡

5. የሥጋ ሞትን አስከተል (ዘፍጥረት 3፤19) የተረገመች ምድርን ፈጠረ (ዘፍ 3፤17-19)፡፡

ከድነት በፊት ሁሉም ሠው በኃጢአት እስራት ቁጥጥር (ሮሜ 3፤9፥ 7፤14፥ ገላትያ 3፤22)፥
በሠይጣን ኃይል (2ኛ ቆሮንቶስ 4፤3-4፥ ኤፌሶን 2፥1-2፥ ቆላስይስ 1፤13፥ 1ኛ ዮሐንስ 5፤19) እና
በእግዚአብሔር ነቀፌታ (የሐዋርያት ሥራ 13፤38፥ ሮሜ 3፤10፥ ቆላሥያስ 1፤14፥ 1ኛ ቆሮንቶስ
6:9፥ 2ኛ ተሰ 2፤10፥12፥ 2ኛ ጴጥሮስ 2፤13፥ 1ኛ ዮሐንስ 2፤12) ሥር ነበረ፡፡

የእኛ የቀድሞ ዝርዮች ኃጢአትን በየግላቸው ፍቃዳቸውን በመከተል ሰርተዋል፡፡ እኛም
በፍቃዶቻችን ተስበን ኃጢአትን ሰርተናል( ሮሜ 3፤23 ፥ 1ኛ ዮሐንስ 1፤8)፤ ነገር ግን የስጋ ፍቃዳችን
በእኛ ሥጋዊ የኃጢአት ባህሪያችን የመጣ ነው፡፡ ለምግብነት የሚያገለግለው የብርጭቆ ወተት መርዝ
ሲጨመርበት እንደሚገድል ሁሉ በጌታ ያላመኑ ወላጆቻችንን መንፈስ ለኃጢአት በማዘጋጀት የልጆችን
መንፈስ ሙሉ በሙሉ ኃጢአት በማጣመም ይመርዘዋል፡፡ ይህንን የተጣመመ የሰውን መንፈስ መጽሐፍ
ቅዱስ የተበላሸ ሲለው ይህም ከሐጢአተኛ የሰው ባህርይ የመነጨ ነው( ሆሴ 5፤2፥ 9:9፤ ሮሜ 1፥28;
1ኛ ጢሞቴዎስ 6፤5፥ 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፤8)፡፡ ይህንን የተበላሸ መንፈስ ሁሉም ሰው (በጌታ ያመነው
እንኳን ቢሆን) ይኖረዋል ፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሰው መልካም/ደግ ነገር በማድረግ/በመስራት
ድህንነቱን ሊፈፅም የማይችለው (ኤፌሶን 2፤8-9)፡፡ በዚህ ምክንያት ነው በጣም ታመኝ የሆኑ
አገልጋዮች እንኳን እንከን የሚወጣላቸው፡፡

VIII. ድነት

ማን ነው አዳኝ የመሆን መስፈርትን የሚያሟላው? ምንስ ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅበታል?
1. እርሱ እግዚአብሔር የሰዎችን የኃጢአት ፍርድ ቅጣት ለመክፈል ፍቃደኛ መሆን አለበት
(መዝሙር 40፤7-8; ዮሐንስ 12፤27፥ 17፤19፥ 18፤11)፡፡

2. እርሱ የሌሎች ሐጢአተኞችን የኃጢአት ቅጣት ለመክፈል ምንም ኃጢአትና የኃጢአት ባህርይ
የሌለበት መሆን አለበት (ሉቃስ 1፤35; ዮሐንስ 8፤46)፡፡

3. እርሱ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ኃጢአት መሰዋዕት እንዲከፍል የፈለገውን አይነት የሰው አካል
የለበሰ ሰው መሆን አለበት (መዝሙር 22፤16፥ ኢሳይያስ 52፤13 – 53፤12)፡፡

4. እርሱ ለአንድ ሌላ ነፍስ ብቻ የሚበቃ መስዋዕት ብቻ ሳይሆን ለሰው ሁሉ ድነት የሚበቃ መስዋዕት
መክፈል አለበት (ዮሐ 1፤3፥29፥36፤ ቆላ 1፤15-17፥19፥ 2፤9)፡፡

እነዚህን ሁሉ መስፈርቶችና የእገዚአብሔርን የዓለም ኃጢአት ቅጣቶች ሊሸከምና ሊከፍል የቻለ
ጌታ እየሱስ ብቻ ነው፡፡ ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም
በስተቀር ከሠማይ በታች የለምና (የሀዋርያት ሥራ 4፤12)፡፡ በዮሐንስ 17፤3 ላይ ደግሞ አውነተኛ
አምላክ የሆንከውን አንተንና የላከውንም እየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት (ዮሐንስ
17፤3) ናት ይላል፡፡

ድነት ማለት ከኃጢአትና ከሠይጣን አገዛዝ ወደ እግዚአብሔር አገዛዝ (ሮሜ 1፤16፥ 1 ቆሮንቶስ
15፤56-57፥ ኤፌሶን 2፥1-6)፤ ከኃጢአት ኩነኔ ወደ እግዚአብሔር ይቅርታ (ኤፌሶን 1፤7፥ ቆላስይስ
1፤14)፤ ከግብረ ገብ እና መንፈሳዊ ጨለማ ወደ ብርሃን (1 ተሰሎንቄ 5፤5፥ 1 ዮሐንስ 1፤5)፤ ትርጉም
ከሌለው ህይወት፥ ዓላማ እና ምክንያት ወዳለው ህይወት (ማቴዎስ 28፤18-20)፤ ከዘላለማዊ ስቃይ ወደ
ዘላለማዊ እረፍት (ዮሐንስ 3፤16፥ ራእይ 20፤15) በመምጣት መገላገል ማለት ነው፡፡ ይህ በስጋም
በነፍስም የእግዚአብሔር ህልውና ወዳለበት መምጣት ማለት ነው (ሮሜ 8፤23፥ 1 ቆሮንቶስ 15፤12-
58፥ 1 ተሰሎንቄ 4፤13-17)፡፡ ድነት ዘላለማዊ ስለሆነ የዳነ ሰው በፍፁም ዳግመኛ በሐጢአት
ውድቀት ካልወደቀ በስተቀር ሊያጣው አይችልም (ዮሐንስ 10፤28፥ 1 ጴጥሮስ 1፤5፥23፥ ይሁዳ
1፤1)፡፡

ድነት በሐይማኖታዊ ሥርዓት (ፊሊጵስዩስ 3፤4-9)፤ በመልካም ሥራ (ኤፌሶን 2፤8-9)፤
በማህበረሰብ ዘንድ የተከበሩ በመሆን (1ኛ ቆሮንቶስ 1፤26-29፥ ያዕቆብ 2፤5) ወይም በጌታ አምነው
የዳኑ ቤተ ሰብ አባል በመሆን (የሐዋርያት ሥራ 16፤33) አይገኝም፡፡ ሁሉም ሰው በመስቀሉ ሥራ
ሐጢአተኞች ናቸው (ሮሜ 11፤32)፤ ድነትም በወንጌል በማመን ብቻ ይገኛል (ዮሐንስ 3፤16፥ ሮሜ
10፤11-13)፡፡

አሁንም ወንድሞች ሆይ፤ የሰበኩላችሁንና የተቀበላችሁትን ደግሞም ጸንተችሁ የቆማችሁበትን
ወንጌል ላሳስባችሁ እወዳለሁ፤ የሰበኩላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፥ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፥
አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው፡፡ እኔ የተቀበልሁትንና ከሁሉ በላይ የሆነውን ለእናንተ
አስተላልፌያለሁ፥ ቅዱሳት መፃህፍት እነደሚሉት ክርስቶስ ስለ ሐጢአታችን ሞተ (1ኛ ቆሮንቶስ 15፤1-4)፡፡

 

ክርሰቶስ በእኛ ቦታ ለሐጢአታችን ሞተ፡፡ መሞቱ በመቀበሩ የተረጋገጠ ሲሆን እግዚአብሔር
ሐጢአተኛ አለመሆኑን ለማሳየት ከሞት አስነሳው፤ ሥልጣንም በሠይጣንና በሞት ላይ እንዲሁም ሌሎችን
በትንሳኤ ወደ እግዚአብሔር ሙላት እንደሚያደርስ አሳየ (1ኛ ቆሮንቶስ 15፤12-57፥ 1ኛ ተሰሎንቄ
4፤13-18) ፡፡

አንድ ሰው ለመዳን የግድ በክርስቶስ ማመን አለበት (ማቴዎስ 7፤13-14፥ ዮሐንስ 8፤24 እና
14፤6፥ የሐዋርያት ሥራ 4፤12)፡፡ ነገር ግን ስለ እርሱ በፍፁም ያልሰሙት ምን ይሆናሉ? ይህንን
የተመለከት ህግ በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፤ አንድ ሰው የመጣለትን ብርሃን ከተቀበለ እግዚአብሔር
ወደ ብሩህ ብርሃን እየመራው ለድነት ያዘጋጀዋል (ኤርምያስ 29፤12-14፥ ማቴዎስ 7፤7-8)፡፡ ለምሳሌ
አንድ ሰው የፈጣሪን የፍጥረት ሥራ ካደነቀ (መዝሙር 19፤1-4፥ ሮሜ 1፤18-20)፤ አግዚአብሔር
የበለጠ ብሩህ የብርሃን ወንጌሉን በአንድ ወንጌላዊ በኩል እስከሚያሰማው ድረስ ያሳየዋል፡፡

ነገር ግን ሰዎች በድሮ ጊዜ እግዚአብሔር የናዝሬቱ እየሱሰ በሚባል አዳኝ የመስቀል ሥራ በኩል
እንደሚያድን ያልተገለጠላቸው እንዴት ይድናሉ? እግዚአብሔር እርሱ ባለፈው ጊዜ ባልገለጠው የማዳን
ሥራ በኩል ሣይሆን እርሱ በገለጠው የማዳን ሥራ እንዲያምኑ ይፈልጋል፡፡ ለምሣሌ እግዚአብሔር
አዳምንና ሔዋንን ለማዳን የፈለገው ከሴቲቱ የሚወለደውና ለጊዜው በሠይጣን ቢቆስልም በመጨረሻ
ሠይጣንን ባሸነፈው ልጅ እንዲያምኑ ነው (ዘፍጥረት 3፤15)፡፡ እየሱስ ለአንተ ኃጢአት እንደሞተ፥
እንደተቀበረ እና እግዚአብሔር ከመቃብር የማስነሳቱን እውነት ትቀበላለህ? ይህንን በፍቅር የተሞላ እና
ኃይለኛ የእግዚአብሔርን ሥራ በማመን የዘላለምን ድነት ተቀበል፡፡

IX. እስራኤል

ጌታ አብራምን እንዲህ አለው፤

1.
"
ከአገርህ ውጣ፤ ከዘመዶችህና ከአባቶችህ ቤት እኔ ወደ ማሳይህ ምድር ውጣ፤
2. ታላቅ ህዝብ አደርግሀለሁ፤ በረከትም ትሆናህ፤
3. የምትባርካቸውን እባርካለሁ፤ የምትረግማቸውንም እረግማለሁ፡፡ ባንተ የዓለም ህዝቦች ሁሉ
ይባረካሉ….. ለዘሮችህ ሁሉ ይህንን ምድር አወርሳለሁ

አለው (ዘፍጥረት 12፤1-3፥7):: በዚህ
እግዚአብሔር ለአብርሃም በገባው ቃል ኪዳን ምክንያት ህዝቦች በአብረሃም በኩል ይባረካሉ፡፡

ትንሿ እስራኤል የታሪክና የትንቢት ማዕከል ናት፡፡ እሷ የዓለም ዜና ትኩረት እና እምብርት
ናት፡፡ ለዓለም ስልጣኔ እና ታሪክ ከመሬት ስፋቷ በላይ አስተዋፅኦዋ በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ እርሷ
ከእግዚአብሔር ጋር ያላት ህብረት ከመጨረሻዎቹ ዘመናት ክስተቶች ጋር ይዛመዳል፡፡ ከእርሷ ጋር
ግለሰቦችም ሆኑ መንግስታት ያላቸው ግንኙነት በመጨረሻቸው ላይ ተፅእኖ አለው፡፡ እግዚአብሔር
ለእስራኤል ባለቤት መሆኑን ቃል ገብቷል፤ የምትባርካቸውን እባርካለሁ፤ የምትረግማቸውንም እረግማለሁ
(ዘፍጥረት 12፤3) በማለት፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ስለ እስራኤል የሚለውን ማጥናት በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

ይህ ክፍል እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ ከአብረሃም ጋር የገባው ቃል ኪዳን የአብረሃም ቃል
ኪዳን ይባላል፡፡ ሌሎቹ ቃል ኪዳኖች በዘፍጥረት 13፤14-17፥ 15፤1-21፥ 17፤1-21 እና 22፤15-18
ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ይህ ቃል ኪዳን ዛሬም ይስራል ምክንያቱም፤

 

1. እግዚአብሔር ይህንን ቃል ኪዳን ከአብረሃም ወደ ይስሃቅ (ዘፍጥረት 26፤2-5፥24)፥ ያዕቆብ
(ዘፍጥረት 28፤13-15) ስሙም እስራኤል ወደ ተባለው ያዕቆብ (ዘፍ 32፤28)እና የእስራኤል ልጆችንና
አስራ ሁለቱን ነገዶችን አሳልፏል (ዘፍ 49፤1-28፥ ቁጥር 10)፡፡

2. በዚህ የቃል ኪዳን ክፍል ውስጥ እግዚአብሔር ለአብረሃምና ለዘሮቹ የገባቸው ቃል ኪዳኖች የሚገኙት
(ዘፍጥረት 12፤7፥ 13፤15-16፥ 15:5፥13፥18፥ 17፤7-10) ክፍል ውስጥ ነው፡፡

3. እግዚአብሔር በግልፅ በዘፍጥረት 17፤7 ላይ እንደገለፀው ከአብረሃምና ከትውልዱ ጋር “በእኔና
በአንተ፥ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር ከትውልድ እስከ ትውልድ ኪዳኔን እመሰርታለሁ፤ በዚህም የአንተ
እና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ” ቃል ኪዳን ገብቷል፡፡

4. በሮሜ 11፤27 ላይ ጳውሎስ እግዚአብሔር ለእስራኤል የገባውን ቃል ኪዳን ሐጢአታቸውን
በማስወገድ (ኢሳይያስ 59፤19-21) አሳይቷል ፡፡እግዚአብሔር ከአብረሃም ጋረ የገባው ሶስት ቃል
ኪዳን ከእስራኤላውያን ጋርም በመቀጠል እስከ ዘመኑ ፍፃሜ ድረስ ይቀጥላል (ሮሜ ቀ፤4፥ 11፤29)፡፡

እነርሱም የርስት (ዘዳግም 29፤1-30፥ 20)፤ ከዳዊት ጋር የገባው (2ኛ ሣሙእል 7፤11-16፥ 1ኛ ዜና
መዋዕል 17፤10-14) እና አዲስ (ኤርምያስ 31፤31-37) ቃል ኪዳኖች ናቸው፡፡ እነዚህ ቃል ኪዳኖች
አሁንም ቢሆን ለእስራኤል የተሰጡ ቢሆንም (ሮሜ 9፤4)፤ እግዚአብሔር ዓለም ወደ መንፈሳዊ ባርኮት
እየሱስን በማመን እንዲገባ አድርጓል (ኤፌሶን 2፤12-22፥ 3፤6፥ ገላቲያ 3፤13-14)፡፡ እስራኤልንም
የመረጠው የተለዩ ህዝቦች ለመሆን ፈልገው ወይም መልካም በመስራታቸው እንዲሁም መመረጣቸው
የተሻሉ እና ከሌሎች ህዝቦች ጥቂት ኃጢአት የሚሰሩ ስለሆኑ አይደለም፡፡ መመረጣቸው በእግዚአብሔር
ፍላጎት ብቻ ነው፡፡ እርሱ በሉአላዊነቱ ቅድስናውንና ክብሩን ለሌሎች ህዝቦች ሊያሳይ፥ የመጀመሪያዎቹ
ከአብረሃም ዘመን ጀምሮ የእግዚአብሔር ቃል ተቀባዮች በመሆናቸው፥ ለሌሎች ህዝቦች ትንቢቱን
ለማሳየት፥ መጽሐፍ ቅዱስንና መሲሁን ወደ ዓለም ለማምጣት፥ የጥንቷ ቤተ ክርስቲያንን ለመመስረት፥
ለማስተማርና ለመመራት፥ ለዓለም ወንጌልን ለማዳረስ፥ በታሪክ ውስጥ ብቸኛዋ ብሄራዊ የእግዚአብሔር
ድነት ያገኘች አገር እንድትሆን፥ በመሲሁ በኩል ከአብረሃም ጀምሮ የመጀመሪያዋ የዓለም የወንጌል
ማዕከል እንድትሆን መረጣት፡፡ በእርግጥ እርሱ ሁሉንም ያሳካል፡፡

እግዚአብሔር አንድ ሌላ ቃል ኪዳን ከእስራኤላውያን ጋር የገባው-የሙሴ ቃል ኪዳን- ወይም
በቀላሉ ህገ ደንቡ በዘፀአት 20፤1 እና ዘዳግም 28፤68 መካከል ይገኛል፡፡ ስለዚህ ሁኔታ አራት ነጥቦችን
ማንሳት ያስፈልጋል፡፡

1. ህጉ ለእስራኤላውያንና ለእነርሱ ብቻ ተሰጠ (ዘፀአት 20፤1-17፤22)፡፡

2. ሕጉ የተሰጣቸውም ከሌሎች ህዝቦች የተለዩ እንዲሆኑ (ዘሌዋውያን 11፤44-45; ዘዳግም 7፤6፥ 14:1-
2)፤ ሊቀድሳቸው፥ ቃሉንና መሲሁን የሰጣቸው እሱ እንዲያምኑ (ሮሜ 8፤1-4፥ ገላቲያ 3:24-25)
ነው፡፡

3. እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የገባቸው ቃል ኪዳኖች ሁሉ በእግዚአብሔር ታማኝነት ላይ ብቻ
የተመሰረቱ ሲሆኑ በሙሴ በኩል የተሰጠው ቃል ኪዳን ግን በእስራኤል ታዛዥነት ላይ የተመሰረተ ሆኖ
እስራኤል ቃል ኪዳኗን በማፍረሷ ምክንያት ይህ ስምምነት ዛሬ አይሰራም (ኤርምያስ 31:32)፡፡ ህጉ
በመስቀሉ ስራ ላይ ተፈፃሚ አልነበረም (ሮሜ 10:4; ኤፌሶን 2:15; ቆላስይስ 2:13-14; ዕብራውያን
7:18; ዕብራውያን 10:19)፤ የሙሴ ትእዛዛት በሙሉ አስርቱ ትዕዛዛት እንኳን ሳይቀሩ ዛሬ ሊፈፀሙ

አይችሉም (2 ቆሮንቶስ 3:2-11) የሠንበት ትዕዛዝ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በተለየ መልኩ እንደ ክርስቶስ
ህግ ይታያል (ሮሜ 8፤2፥ ገላ 6፤2)፡፡

4. ያልተፈፀሙ የቃል ኪዳን ተስፋዎች ወደ ፊት የሚፈፀሙት በተሻረው ህግ ሳይሆን በማይገደበው
እግዚአብሔር ለአብረሃም፥ ለምድሪቱ፥ ለዳዊትና በአዲስ ቃል ኪዳን ነው፡፡.

X. ቤተ ክርስቲያን

እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ ቤተ ክርሰቲያን ደግሞ ከጴንጤ ቆስጤ ጀምሮ እስከ ዳግም
ትንሳኤ ጊዜ የሚኖሩ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ ልጆች ናቸው (ዮሐንስ 3፤6-7)፡፡ ከዚህ ቀጥሎ
በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱትን ሶስት አይነት ቤተ ክርስቲያናት (ዓለም ዓቀፍ፥ አጥቢያና
የሚሲዮናውያን መላእክተኞቹን ቤተ ክርስቲያናት) እንመለከታለን፡፡

ሀ. ዓለም አቀፋዊዋ ቤተ ክርስቲያን
ዓለም ዓቀፋዊቱ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ስያሜዎች በተጨማሪ የክርስቶስ አካል ትባላለች (ሮሜ
7፤4፥ 1ኛ ቆሮንቶስ 10፤16 እና ኤፌሶን 4፤12)፡፡ ይህ ስያሜ የሚያሳየው በክርሰቶስ እየሱስ ያመኑ
እውነተኛ አማኞችን ህብረት ሲሆን የዚህ ህብረት ራስ ደግሞ ክርስቶስ ነው (ኤፌሶን 1፤22፥ 4፤15፥
5፤23፥ ቆላስይስ 1፤18፥ 2፤19)፡፡ ዓለም ዓቀፋዊቱ ቤተ ክርሰቲያን ሁሉንም በዓለም ያሉ እና
ክርስቶስን አምነው የሞቱ ከጴንጤ ቆስጤ እስከ ንጥቀት ያሉትን እውነተኛ አማኞች ያጠቃልላል፡፡

የሐዋርያት ሥራ 1፤5፥ 2፤1-4፥ 10፤44፥ 11፥15-16 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12፤13 እንደሚያሳዩት ዓለም
ዓቀፋዊቱ ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረችው በጴንጤ ቆስጤ ቀን ጀምሮ ነው፡፡ በየሐዋርያት 11፤15-16 ላይ
ጴጥሮስ እንደሚለው ጴንጤ ቆስጤ ማለት መጀመሪያ ማለት ሲሆን ይህቺ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ቀን
በፊትና ከንጥቀት በኋላ በሚኖሩት አማኞች የተለየችው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፡፡

1. ከጴንጤ ቆስጤ እለት በፊት ካሉት አማኞች (ጥቂት አማኞች ያልሆኑም) ጭምር ብቻ የእግዚአብሔር
መንፈስ ነበረባቸው፤ ሁሉም አማኞች ከጴንጤ ቆስጤ እስከ ዳግም ንጥቀት ድረስ ያሉት በውስጣቸው
የእግዚአብሔር መንፈስ አለባቸው (ዘኁልቁ 11፤17-25፥ 27፤18፥ 2 ነገስት 2፤9-12፥ ዮሐንስ
7፤37-39፥ 14፤16-17)፡፡

2. በሮሜ 12፤5፥ 1 ቆሮንቶስ 1፤2፥ 15:18 ያሉት ብቻ በክርስቶስ ያመኑት ናቸው፡፡
3. ከእነዚህ ውስጥ የሞቱና በህይወት ያሉ በዳመና ሲነጠቁ ከጴንጤ ቆስጤ እለት በፊት የነበሩት አማኞች
እስከ ንጥቀት ጊዜ አካላቸው በመቃብር ሲቆይ ከንጥቀት በኋላ እስከ ዳግም ምፅአት ያመኑ አማኞች
በታላቁ መከራ ወቅት በምድር ላይ ይቆያሉ፡፡

 

እነዚህ ክስተቶችና ሌሎች የተለያዩ የአለም አቀፋዊቱ
ቤተ ክርስቲያን ባህርያትን ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡

ለ. የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማለት በሽማግሌዎች ና በዲቆናት አመራር ስር ለታላቁ ተልእኮ
ራሳቸውን አደራጅተው የጥምቀትንና የጌታ እራትን ስርአት በሚያካሄዱ፥ እግዚአብሔርን በማምለክ የቤተ
ክርስቲያን አካል የሆኑ፥ ህብረት ያላቸው፥ ቃሉን የሚያስተምሩና መንፈሳዊ ስጦታዎችን የሚላማመዱ
እንዲሁም በመሲሁ በማመን የተጠመቁ አማኞችን ያጠቃልላል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግልፅ ዓለማ ያለውን ህብረት ቢያበረታታም ለጋራ አገልግሎት በየጊዜው
የሚካሄድን ህብረት እንኳን በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ እንደ ሙሉ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን

አይቆጥረውም፡፡ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ግልፅ ዓላማ ከሌላቸው ህብረቶች ይልቅ ድርጅት፥ ሥልጣን፥
ሃላፊነት እና ተአማኒያን ናቸው፡፡ ዓለም አቀፋዊ የክርስቶስ አካል የተመሰረተችው ከጴንጤ ቆስጤ እለት
እስከ ንጥቀት ባሉት እውነተኛ አማኞቸ የተመሰረተ እና ክርስቶስም የቤተ ክርስቲያኒቱ ራስ የሆነላት
ናት፡፡ አንድ ዓለም አቀፋዊ የክርስቶስ አካል የሆነች ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው ቁጥር ሥፍር
በሌላቸው አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት እና በቤተ ክርቲያትያን መመስረቻ ዘመን ውስጥ ነው፡፡ የዓለም
አቀፍ ቤተ ክርስቲያን አካሏ የተዋቀረው ከእውነተኛ አማኞች ሲሆን ይህችም እውነተኛ አጥቢያ ቤተ
ክርስቲያን በአማኞች መመራት ቢኖርባትም በውስጧ የማይታወቁ የማያምኑ አባላት ሊኖሯት ይችላል
(ማቴዎስ 13፤24-30፥31-32)፡፡

አንድ ሰው እውነትን ፈላጊ ከሆነ የቤተ ክርስቲያን ስብሰባዎችን መካፈል ቢችልም አባል መሆን
የሚችለው ግን በክርስቶስ አምኖ ንስሀ ከገባ ብቻ ነው፡፡ የዓለም አቀፏ ቤተ ክርስቲያን መከሰት
የጀመረችው ከጴንጤ ቆስጤ እስከ ንጥቀት ባለው ጊዜ ውስጥ በሁሉም የዓለም ክፍል ቢሆንም አጥቢያ
ቤተ ክርስቲያን በማንኛውም የቤተ ክርስቲያን መመስረቻ ዘመን ሲሆን ይህን ያህል እድሜ ይኖራቸዋል
ተብሎ መገመት ሳይቻል በአንድ ቦታ (ጥቂት አባሎቿ ተዘዋዋሪ አገልጋዮች ቢሆኑም) ሊገኙ ይችላሉ፡፡

ዓለም አቀፋዊቷ የቤተ ክርስቲያን አካል እንዳንዴ የማትታየው ቤተ ክርስቲያን ስትባል ጌታ ብቻ
ሁሉንም አባላቷን ያውቃል፤ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባላትን ግን በተፈጥሮ አይን ይታያሉ፡፡

ሐ. ሚስዮናውያን
ሌለኛው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለፀው ስመ ጥር የሆነ የዓለም አቀፏና የአጥቢያ ቤተ
ክርስቲያናት መልክ የሆነው የሚሲዮናውያን አገልግሎት ነው፡፡በዚህ እጅግ ስመ ጥር በሆነው
የሚሲዮናውያን አገልግሎት ውስጥ የጳውሎስን አገልግሎት እንመለከታለን፡፡ ይህ አገልግሎት በመላው
ዓለም ላይ የምትገኘው የጌታን ትዕዛዛት የምተፈፅመዋ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ ነው… ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱና
ደቀ መዛሙርቴ አድርጓቸው (ማቴዎስ 28፤19)፤ ይህ የወንጌላውያንና (የሐዋርያት ሥራ 8፤5፥ 26-35)
እና የሚሲዮናውያን ወንጌልን ወዳልተደረሰባቸው ቦታዎች የማድረስ አገልግሎት ቢሆንም፡፡ ጳውሎስ ወደ
ሮሜ ሰዎች በላከው መልእክት ሌላው በጣለው መሠረት ላይ እንዳልገነባ ብዬ፥ ክርስቶስ ባልተጠራበት
ስፍራ ወንጌልን መስበክ የዘወትር ምኞቴ ነው ተብሎ እንደተፃፈ "ያልተነገራቸውን ያያሉ፤ ያልሰሙትን
ያስተውላሉ

(ኢሳይያስ 52:15)
"
(ሮሜ 15:20-21) እንዲሁም ወደ ቆሮንቶስ ወንጌልን ላልደረሰባቸው
ማዳረስ ያስፈልጋል እንጂ በሌሎች በተሰራው ሥራ መፎከር አይደለም(2 ቆሮ 10፤16)፡፡

በአገልግሎቱ እጅግ ውጤታማ ለመሆን ጳውሎስ ቅድስናውን በማይነካ መልኩ የእያንዳንዱን
ባህልና ግለሰብ ሳይነቅፍ እራሱን አዘጋጀ (የሐዋርያት ሥራ 17፤19-23፥ 1 ቆሮንቶስ 9፤19-23፥
ቆላስይስ 4፥6)፡፡ እርሱና ባልደረቦቹ ወንጌልን ሰበኩ፥ ቤተ ክርስቲያንን መሰረቱ፥ ሽማግሌዎችን ሾሙ
(ቲቶ 1፤5) እንዲሁም አዳዲስ አማኞችን በማሰልጠን ሥራውንና የአግዚአብሔርን ቃል በሁሉም መልኩ
አባዙ (2ኛ ጢሞቴዎስ 2፡2)፡፡ በህይወት አደገኛ በሆኑ ቦታዎች ልክ ለመስበክ ምቹ እንደሆኑ
ስፍራዎች ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወንጌልን ሰበኩ (የሐዋርያት ሥራ 4፤19-20፥ 23-29፥ 2
ቆሮንቶስ 11፥21-33)፡፡ ሁሉን ነገር በአንዴ መገንዘብ አልቻሉም ነበር (የሐዋርያት ሥራ 15)፥ ጌታ
እቅዳቸውን በባህር ላይ አንኳን ሳይቀር አስቀየራቸው (የሐዋርያት ሥራ 16፤7-9)፥ ከራሳቸው ጋር
ከፍተኛ የሆነ አለመስማማትና ውጊያ ቢኖርባቸውም (የሐዋርያት ሥራ 11፤2፥ 15፤36-40፥ ገላትያ

2፤12-14 አገልግሎታቸው ከሁሉም ተቃውሞ እና የሰው ችግሮች እንደሚበልጥ እግዚአብሔርም
ሥራቸውን እነደሚሰራ አመኑ እንጂ አላፈገፈጉም፡፡ ጳውሎስና ሌሎች የወንጌል ሚሲዮናውያን
ብቻቸውን በሰሜናዊ የሜድተራንያን ባህር ዳርቻ ቤተ ክርስቲያንን በመመስረት አገልጋዮችን አሰለጠኑ፡፡

እየሱስም እንደተናገረው የገሀነም ደጆች የማይቋቋማትን ቤተ ክርስቲያን መሰረተ (ማቴዎስ 16፤18)፡፡

የጳውሎስ የአገልግሎት ባልደረቦች ግልፅ መረዳት ነበራቸው፡፡ ይህ ለአህዛብ ሃዋሪያ እንዲሆን
የመሪያቸው ተልዕኮ ነበር፡፡ ግልፅ መሆን ያለበት ጉዳይ ቢኖር አግዚአብሔር ጴጥሮስን ለአይሁድ
ጳውሎስን ደግሞ ለአህዛብ ሃወሪያ (ገላትያ 2፤7) አድርጎ ቢቀባም ወንጌል ለአህዛብ ሲሰበክ በመጀመሪያ
ለአይሁዶች (ሮሜ 1፤16) ቀጥሎ ደግሞ ለአህዛብ መሆኑ አስፈላጊ ነው (የሐዋርያት ሥራ 13፤46)፡፡

የየሐዋርያት ሥራ መጽሐፍን ስናነብም ይህ እውነት እነደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ጳውሎስ በፊት
ወዳገለገለባቸው ቦታዎች ሲመለስ እንደ ቀድሞው አገለገላቸው (የሐዋርያት ሥራ 18፤19፥ 19፤1-8)፡፡

በመጀመሪያ እስከ ዛሬ ሥራ ላይ ያለውን ትዕዛዝ ለአይሁዶች ቀጥሎም ለዘጠኝ መቶ ዓመታት ይህንን
አገልግሎት ችላ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አገለገለ፡፡ ለዚህ የጌታ ሥራ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንና
ሚሲዮናውያን የተለዩለት መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንዱም ለሌላው በስልጣንና በሃላፊነት እኩል
ደረጃ ላይ በመገኘታቸው አንዱ ሌላውን ያገለግላል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ባርናባስንና ሳኦልን ለጠራኋቸው
ሥራ ለዩልኝ ሲል የአንፆኪያ ቤተ ክርስቲያን በፆም፥ በፀሎትና እጅ በመጫን ለአገልግሎቱ እንዲለዩ
አደረጉ (የሐዋርያት ሥራ 13፤1-3)፡፡ የጳውሎስ ጉዞ ከቢታንያ ወደ ሜቆዶንያ በጌታ ፍቃድ ሲቀየር
(የሐዋርያት ሥራ 16፤7-10)፥ እርሱ ወደ ሜቆዶንያ ለመሄድ ሲወስን (ቁጥር 10) የአንፆኪያና
የእየሩሳሌም ሽማግሌዎች ፍቃድ አልጠየቀም፡፡.

የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አባላት የጳውሎስን ቡድን ተቀላቀሉ (የሐዋርያት ሥራ 12፤12፥
16፤1-3፥ 20፤1-4)፤ በራቸውንም ከፈቱላቸው (የሐዋሪያት ሥራ 16፤14-15)፤ ፀለዩላቸው (ቆላስይስ
4፤13፥ ኤፌሶን 6፤19)፤ በገንዘብ ረዷቸው (2ኛ ቆሮንቶስ 8፤3፥ 5፥ 11፤9፥ ፊሊጵስዩስ 4፤14-16)
እንዲሁም ለእነርሱ ዋጋ ከፈሉላቸው (ሮሜ 16፤3-4)፡፡ በተቃራኒው ሚስዮናውያኑ አጥቢያ ቤተ
ክርስቲያንን እየመሠረቱ ከእነርሱ ጋር ለረጅም ጊዜ እየቆዩ እንደ አስፈላጊነቱም ከእነርሱ ጋር በመቆየት
መፅናታቸውን ለማረጋገጥ እና በእግዚአብሔር ቃል ለማነፅ ተመላለሱ፡፡ ጳውሎስም አብያተ
ክርስቲያናትን እያበረታታ በሶሪያና በኪልቅያ አለፈ (የሐዋርያት ሥራ 15:41)፥ በቆሮንቶስም
የእግዚአብሔርን ቃል እያስተማረ አንድ ዓመት ከስድስት ወር አብሮአቸው ቆየ (የሐዋርያት ሥራ
18፤9-11)፤ ለኤፌሶን ሽማግሌዎችንም እያስጠነቀቀ ሶስት ዓመት ሙሉ ሌሊትና ቀን ሳያቋርጥ በእንባ
እያንዳንዳችውን መከራቸው (የሐዋርያት ሥራ 20፤31)፥ ቲቶንም ያልተስተካከለውን ነገር
እንድያስተካክልና በየከተማው ሽማግሌዎችን እንዲሾም አዘዘው (ቲቶ 1፤5፥ የሐዋርያት ሥራ 20:28-
32፥ ሮሜ 16፤17-19፥ ፊልጵስዩስ 3፤15-16፥ 1 ቆሮንቶስ 5፥ 1 ተሰሎንቄ 5፤12-22)፡፡ እርሱ
አጥቢያ ቤተ ክርስቲያንን በደብዳቤ እንዲሁም ከአገልግሎት ባልደረቦቹ ጋር ደግሞ የሚጎላቸውን
በማሟላት ያገለግሉ ነበር፡፡ የእየሩሳሌም ቅዱሳንን እርዳታ ሲፈልግ ከጳውሎስ እና ከአገልግሎት
ባልደረቦቹ እርዳታ ያገኙ ነበር (ሐዋ ሥራ 11፤29-30፥ 1 ቆሮ 16፤1-3)፡፡

ጊዜው በመለወጡ ምክንያት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሥራዎች፥ የፀጋ አገልግሎቶች፥ ዘመናዊ
የስብከት አገልግሎቶች እና የመሳሰሉት መልካም እና በጎ የሆኑ ነገሮች እየተካሄዱ ነው፡፡ ቢሆንም እንደ

ጆሹዋ የተባበሩት አሜሪካ አለም ዓቀፍ አገልግሎት እቅድ (joshuaproject.net)፤ የዓለም 41 ከመቶ
የሚሆነው ክፍል ወንጌል ስላልደረሰው እንደ ጳውሎስ ያሉ አገልጋዮች ያስፈልጋሉ፡፡ እየሱስ ክርስቶስ
ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት የተናገረው አሁንም ይሰራል፡፡ መከሩ ብዙ ነው፤ የመከሩ ሰራተኞቹ ግን
ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ ወደ መከሩ ሠራተኞችን እንዲልክ ለምኑት (ማቴዎስ 9፤37-
38)፡፡ እግዚአብሔር ጠንካራ፣ ደፋር፣ ጥበበኛ እና የተሰጡ ወንድ እና ሴት አገልጋዮችን አስነስቶ ብርቱ
የሆኑ ሚሶናውያንን ወንጌል ላልደረሰባቸው የዓለም ክፍሎች ይላክ፡፡ አሜን!

                                                                            XI. የወደፊቱ የእግዚአብሔር እቅድ

ዓለም ለረዥም ጊዜ አሁን ባለችበት ኃጢአት፥ ዋይታ እንዲሁም በተፈጥሮም ሆነ በሰዎች ምክንያት
በሚከሰቱ መቅሰፍቶች እየታወከች ለዘለዓለም አትቀጥልም፡፡ እግዚአብሔር ለወደፊቱ የድነት ፋና
የሚሆን ላልዳኑት ማስጠንቀቂያና ለሁሉ የሚሆን የእርሱ ፍትህ እና ምህረት ማረጋገጫ አዘጋጅቷል፡፡

ሀ. ንጥቀት
አንድ ጊዜ የክርስቶስ አካል ሙሉ በሙሉ ከተሰራ በኋላ (ሮሜ 11፤25)፥ እግዚአብሔር ሁሉንም
የሞቱትን አማኞች ትንሳኤ በመስጠት እና በህይወት በምድር ላይ ያሉትን አማኞች በመንጠቅ በእርሱ
ህለውና ውስጥ በሰማይ ያኖራቸዋል (1 ቆሮንቶስ 15፤12-57፥ 1 ተሰሎንቄ 4፤13-18)፤ እነርስም ከጌታ
ጋር ለዘላለም ይኖራሉ (1 ተሰሎንቄ 4፤17)፡፡ በዚህ ሰማያዊ ኑሮ ውስጥ በክርስቶስ ያመኑት ብቻ
ይሰበሰባሉ (1 ተሰሎንቄ 4፤16)፡፡ የብሉይ ኪዳን አማኞችና በታላቁ መከራ ዘመን የዳኑ አማኞች ትንሳኤ
የሚያገኙት በመሲሁ ዳግም ምፅአት ጊዜ ጀምሮ ነው (ኢሳይያስ 26፤19፥ ዳንኤል 12፤2)፡፡ ንጥቀት
በአይን እርግብግቢት ቅፅበት የሚከናወን ሲሆን አሁን ደካማና ለበሽታ ተጋላጭ የሆነው አካላች
የማይበላሽ፥ ኃይለኛ አና የማይሞት ይሆናል (1 ቆሮንቶስ 15፤52-54)፡፡ አካላችን ለተረገመችው
ምድራዊ ኑሮ ምቹ እንደሆነ ሁሉ ለሰማያዊ ክብሩ እና ህልውናው ምቹ እንዲሆን ተደርጎ በተቀደሰው
እግዚአብሔር ፊት ለዘላለም ይለወጣል፡፡

ለ. ታላቁ የመከራ ዘመን
ከቤተ ክርስቲያን ንጥቀት በኋላ የሰባቱ ዓመት የታላቁ መከራ ጊዜ ይጀምራል (ዳንኤል 9፤27፥
ማቴዎስ 24፤21)፡፡ ይህም ዘመን ከእግዚአብሔር እና ከሰው ዘንድ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ
የጦርነት፥ የውድመት እና የመቅሰፍት ዘመን ይሆናል፡፡ ይህም እግዚአብሔር እርሱን ለተቃወሙት
ያዘጋጀው የስቃይ ፍርድ ጊዜ ነው(2 ተሰሎንቄ 2፤8-13)፡፡ ቤተ ክርስቲያንም በመነጠቅ ከክርስቶስ ጋር
በሠማይ ትሆናለች (1ኛ ተሰሎንቄ 1፤10፥ 5፤2-9፥ ራእይ 3፤10)፤ በዚያም እያንዳንዱ በክርስቶስ
የተቀደሰ ስለ ምድራዊ አገልግሎቱ ሽልማቱን ይቀበላል (ሮሜ 14፤10-12; 1ኛ ቆሮንቶስ 3፤11-15፥
2ኛ ቆሮንቶስ 5፤10)፤ ሙሽሪቷ ቤተ ክርስቲያንም ለሙሽራው ክርስቶስ ትሞሸራለች (ራእይ 19፤6-
8)፡፡

በምድር ላይ ለሠይጣን ፍቃድ ሙሉ በሙሉ እራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተቃዋሚ በግልፅ በህዝቦች
መካከል ይነሳል (2ኛ ተሰሎንቄ 2፤1-3)፤ እስራኤልም እርሷን ለማጥፋት በከበቧት አገሮች ስጋት ራሷን
ለማዳን ለሰባት ዓመታት ከእርሱ ጋር ሰምምነት ሰታደርግ የታላቁ መከራ ዘመን መጀመርያ ይሆናል፡፡

ከሶስት ተኩል ዓመታት በኋላ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቃል ኪዳኑን በማፍረስ በተቀደሰችው የእየሩሳሌም ቤተ
መቅደስ እራሱን ‘’እኔ እግዚአብሔር ነኝ” በማት በአዋጅ የአይሁዶችን አምልኮ ይፈልጋል፤ የአህዛብን

ጦረኞች ሰብስቦም ድምጥማጧ እንዲጠፋ ያደርጋል (ዳንኤል 9፤27፥ ማቴዎስ 24፤15-16፥ 2ኛ ተሰ
2፤3-4፥ ራእይ 11፥1-2፥ ራእይ 12፤13-15)፡፡

በታላቁ የመከራ ዘመን እግዚአብሔር ሶሰት ታላላቅ ጉዳዮችን ያከናውናል፡፡

1. እስራኤል መሲሁን ባለ መቀበሏ ምክንያት የደረሰባትን ስድብ በመስበር በዚያን ዘመን በህይወት
ያሉትን አይሁዶች በሰባቱ የመከራ ዘመን እንዲድኑ ያደርጋል (ኢሳይያስ 28፤14-22፥ ሕዝቀኤል
20፤33-38፥ ዘካርያስ 13፤1፥ ማቴዎስ 23፤39)፡፡

2. ህዝቦችን ከዓለም ነገዶች ሁሉ በማመን ወደሚገኝ ድነት ያመጣል (ራእይ 7፤1-4፥ 9-17)፡፡

3. እርሱ ጠማማውን የዓለም ሥርዓት እና የክርስቶስን አዳኝነት የሚቃወሙትን ያስወግዳል (ኢሳይያስ
13፤9፥ 24፤19-20፥ ዘካርያስ 12፤2-9፥ ራእይ 17፤1፥ 18፤2፥ 19፤2)፡፡ እስራኤል ስትድን መሲሁ
ቤተ ክርስቲያንን በመምራት ይመጣል (ሮሜ 11፤26-27፥ ይሁዳ 1፤14-15)፡፡ እርሱ የእስራኤልን
ጠላቶች ያጠፋል (ራእይ 19፤11-21)፤ ሠይጣንን ሺህ ዓመት በማሰርም ይገዛል (ራእይ 20፤1-3፥ 5፥
7)፡፡

ሐ. የመሲሁ የሺ ዓመት ዘመን
ሠውና አስተዳደሩ በምድር እና በሠው ልጆች ሁሉ ላይ ታላቅ ውድመትና ተነግሮ የማያልቅ
ስቃይን አምጥቷል፡፡ ጌታ ግን በእየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ ምድርን ሁሉ ሲገዛ ነገሮች ይለወጣሉ
(መዝሙር 2፤6-8፥ ኢሳይያስ 9፤6-7፥ ሉቃስ 1፤30-33)፡፡ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳንና በታላቁ
የመከራ ዘመን የተሰውትን ቅዱሳን ትንሳኤ ይሰጣቸዋል (ኢሳይያስ 26፤19፥ ዳንኤል 12፤2) ምድርንም
የምታሰገርም እና ውብ ያደርጋል (ኢሳይያስ 2፤4፥ 11፤6-9፥ 35፤1-2፥ 65፤17፥20) የበጉና
የሙሽራይቱ ቤተክርስቲያን ዘመንም ይጀምራል (ራእይ 19፤9)፡፡

ዳግማይቱ ቤተ ክርስቲያንና ትንሳኤ ያገኙት የታላቁ መከራ ቅዱሳን ከመሲሁ ጋር ምድርን
ይገዛሉ (ራእይ 20፤4)፤ ንጉሱ ዳዊት እስራኤልን ሲገዛ፤ አስራ ሁለቱ ሐዋርያትም በዳዊት ስር በመሆን
አስራ ሁለቱን የእስራኤል ነገዶች ይገዛሉ (ሕዝቅኤል 34፤23-24፥ኤርምያስ 30፤9፥ ማቴዎስ 19፤28፥
ሉቃስ 22፤28-30)፡፡ ለእስራኤል ቃል የተገቡት ምድራዊ በረከቶች ሁሉ የፈፀማሉ፡፡ እግዚአብሔር
እስራኤላውያንን ከተበተኑባቸው አገራት ሁሉ ወደ ተስፋይቱ ምድር ከሰበሰበ በኋላ በታላቅ ሰላምና
ደስታ እያኖራቸው ከህዝቦች ሁሉ የተለዩ ታላቅ ህዝብ ያደርጋቸዋል (ዛግም 15፤6፥ 28፤1፥13፥
30፤5፥ ኢሳ 11፤11-12፥ 61፤6፥ ማርቆስ 13፤27)፡፡

በእስራኤል መንግስት ውስጥ የተወለዱ ሁሉ ይድናሉ (ኢሳይያስ 44፤5፥ 45፤17፥ ኤርምያስ
24፤7፥ 31፤33-34፥ 50፤19-20፥ ሕዝቅኤል 11፤19-20፥ 36፤25-27)፤ እስራኤልም የመጀመሪያዎቹ
የመሲሁ ተገልጋዮች ይሆናሉ (ዘካርያስ 8፤20-23)፤ እርሷና ቤተ ክርስትያን በእግዚአብሔር መንግስት
ውስጥ ካህናት ይሆናሉ (ዘፀአት 19፤6; 1ኛ ጴጥሮስ 2፤9፥ ራእይ 1፤6፥ 5፤10)፡፡ ለስደተኛዋ
እስራኤል መጠጊያና ሥንቅ የሰጡ የአህዛብ በጎች ድነት አግኝተው ወደ መንግስቱ ይገባሉ (ማቴዎስ
25፤31-40)፡፡ በመንግስቱ ውስጥ የተወለዱ ድነትን ያገኙ አህዛብ ሁሉ (ኢሳይያስ 65፤20)፤ የምድር
ነገዶች ሁሉ (ዘካርያስ 14፤17-19) እና በሁሉም ዘመናት የዳኑት ንጉሱን በቅድስቲቷ እየሩሳሌም መቅደስ
ንጉሱን ያመልኩታል (ኢሳይያስ 2፤2-4፥ ሕዝቅኤል 40፤1-46:24)፡፡

መ. ዘላለማዊ ፍርድ

ሁሉም ቅዱሳን መላእክት በእግዚአብሔር ህልውና ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ (ዕብራውያን
12፤22)፡፡ ሠይጣንና መላእክቱ ግን ለዘለዓለም ወደ ሚነደው የእሳት እቶን ይጣላሉ (ማቲዎስ 25፤41፥
ራእይ 19፤11-21፥ 20፤1-2፥ 10)፡፡ ሰዎችን በተመለከተ ዕብራውያን 9፤27 እንደሚናገረው ሰው
አንድ ጊዜ ሊሞት ከዚያም በኋላ በፍርድ ፊት ሊቆም ተወስኖበታል፡፡ ዳግም ሥጋ መልበስ የለም፡፡

ምንም በጎ ወይም መጥፎ የሚባል ነገር ፍፁምነት እስኪመጣ ድረስ የለም፡፡ ማን ነው ይህንን ፍፁምነት
ሊያገኝ የሚችለው? የዳኑት ቅዱሳን ድነት በመሲሁ ፍፁምነት የማዳን ሥራ ነው፤ የእርሱ ፍፁምነትና
ቅደስና የእርሱን መስዋዕትነት ስናምን የእኛ ይሆናል (1ኛ ቆሮንቶስ 1፤30)፡፡ በሁሉም ጊዜ የዳኑት
ለዘላለም ከእግዚአብሔር ጋር ሲኖሩ (ዮሐንስ 3፤16) ያልዳኑት ግን በሺህ ዓመቱ መጨረሻ በነጩ ዙፋን
ፊት በእሣት እቶን እንደሚቀጡት የቅጣት መጠን ይፈረድባቸዋል (ዳን 12፤2፥ ራእይ 19፤20፥
20፤5፥10-15)፡፡

ሠ. ዘላለማዊ ዘመናት
በክፉዎች ላይ ከተፈረደ በኋላ፤ እግዚአብሔር አዲስ ሠማይንና አዲስ ምድርን ይፈጥራል፤የመጀመሪያዋ
ሠማይና ምድር አልፈዋልና (ራእይ 21፤1) እናም ሁሉም ቅዱሳን መላእክት የሁሉም ዘመን ቅዱሳን
አባት እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚገኝበት፤ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከሠማይ ወደ ሚያረፉባት ምድር
አዲሲቷ እየሩሳሌም ይወረዳሉ (ዕብራውያን 12፤22-23፤ ራእይ 21፤1-22፡5)፡፡  


  
በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. * ማጣቀሻዎች

በዚህ ደራሲ ሃሣብ መሠረት
1. ለወደፊቱ በጣም አስፈላጊ ሊሆን የሚገባው የመሲሁ ዱካ የተባለው በ‘‘Dr. Arnold G. Fruchtenbaum’’ ተፅፎ የታተመ እና በተለያዩ የኤለክተሮኒክ አቀራረብ በ ‘‘www.Ariel.org, or Ariel Ministries, P.O. Box 792507, San Antonio, TX 78279-2509, USA’’ የሚገኝ የቃሉ መከሪ መጽሐፍ፡፡
2. በፍጥረት ለምን እናምናለን ክፍል 3 (Why We Believe in Creation: Part III) ተብሎ በ‘‘Herbert Nilsson, Dr., University of Lund, Sweden’’. የተጠቀሰው መጽሐፍ ፤ የቅሪተ አካል ዘገባ (The Fossil Record) በ" Winkey Pratney (Pretty Good Printing, Last Days Ministries, Lindale, TX., 1984) ’’ የተጠቀሰው መጽሐፍ
3. መሠረታዊ ሥነ መለኮት በ‘‘Charles Ryrie, Dr. Basic Theology’’ (Chicago: Moody Press, 1981) የተፃፈው መጽሐፍ
4. ሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐተታ በዮሀ 4፤8 ላይ (Commentary on the Whole Bible, on 1 ዮሐንስ 4:8) በ‘‘Jamieson, Fausset and Brown እንደተፃፈ
5. ሥርዓት ተክትሎ የተፃፈ ሥነ መለኮት (Systematic Theology, Volume 1, 245) በ“Chafer, Dr. Louis Sperry.” የተፃፈ መጽሐፍ.
6. Fruchtenbaum, Dr. Arnold G. የሬዲዮ ፅሁፍ ቁጥር 63: የመሲሁ አምላክነት፥ San Antonio: Ariel Ministries Press. P. 12).
7. Ryrie, Dr. Charles Caldwell. የራይሬ መጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ፥ Chicago: Moody, 1978.
8. Fruchtenbaum, Dr. Arnold G. የሬዲዮ ፅሁፍ ቁጥር 186, "ሠባቱ የእግዚአብሔር የመፍጠሪያ ቀናት፤ "
San Antonio: Ariel Ministries Press. Pp. 14-15.
9. Fruchtenbaum, Dr. Arnold G. የመሲሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ገፅ 106: አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ገፅ . 5. San Antonio: Ariel Ministries Press.

የመጽሐፍ ቅዱስ ህገ መመሪያ በኖርማን ማንዞን 2002 ዓ.ም፣ ዩኤስ ኤ፤ የደራሲው መብት የተከበረ
ነው፡፡
ይህ መጽሐፍ በወንድም ዘመን እንዳለ በኩል በኢትዮጵያ አገር በነፃ የሚሠራጭ ነው፡፡


 

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines