የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ

(The Lion of the Tribe of Judah)
Original English By Norman Manzon
Translation By Zemen Endale Lashetew

 


ውድ አይሁዳውያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤

አባታችን ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ የአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች አባቶች በሆኑት አስራ ሁለቱ ልጆቹ ላይ
ትንቢት ተናግሮ ነበር፡ 8. ይሁዳ፥ ወንድሞችህ አንተን ያመሰግኑሃል እጅህ በጠላቶችህ ደንደስ ላይ ነው የአባትህ
ልጆች በፊትህ ይሰግዳሉ። 9. ይሁዳ የአንበሳ ደቦል ነው ልጄ ሆይ፥ ከአደንህ ወጣህ እንደ አንበሳ አሸመቀ፥ እንደ
ሴት አንበሳም አደባ ያስነሣውስ ዘንድ ማን ይችላል? 10. በትረ መንግሥት ከይሁዳ አይጠፋም፥ የገዥም ዘንግ
ከእግሮቹ መካከል፥ ገዥ የሆነው እስኪመጣ ድረስ የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል። (ዘፍጥረት 49፡8-10)

አንድ ቀን እጁ በጠላቶቹ ራስ ላይ የሚሆነው እና ለአመራሩም የዓለም መንግስታት በፈቃዳቸው የሚገዙለት
ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ ማን ነው?

የራባይ ተስተካካይ የሆነው የአንቄሎስ እና ራሺ አእማድ ይህንን ፍጹም ሰላማዊ እና ባለጸጋ ሰብዕ መሲሕ ብሎ
ይገልጸዋል፡፡ ትንቢቱ የተሰጠበት አንዱ ምክንያት እስራኤላውያን መሪዎችን መሲህ ነኝ የሚለውን ማኛውንም ሰው
የዘር ሃረግ በመቁጠር ከይሁዳ ነገድ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት የዘር ሃረግ መዝገቡን ለመመርመር እንዲችሉ
ለማድረግ ሲሆን የዘር ሃረግ መዝገቦቹ ግን በ70 ዓ.ም ሮማውያን መዝገቦቹ የተቀመጡበትን መቅደስ ሲያወድሙ
አብረው ወድመዋል፡፡ ይሄ ምን ማለት ነው? መሲሁ ከ70 ዓ.ም በፊት መጥቶ ሊሆን የገባል ማለት ነው፡፡ እናም
ደግሞ ከ70 ዓ.ም በፊት አንድ ሰው ብቻ ነው መሲሁ መሆኑን የተናገረው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ፡፡

ሁለተኛው ማንኛውም ሰው መሲሁ እንደሆነ የተናገረለት ሲሞን ባር ኮሲባ(ባር ኮችባ) ነው፤ በ132 እና በ135
ዓ.ዓ መካከል በራባይ አኪቫ መሲሁ እንደሆነ የታወጀለት ነው፡፡ ነገር ግን በስተመጨረሻ እና ለመጨረሻ ጊዜ
እርሱም መሲሁ እንዳልሆነ ታውጇል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የያዕቆብን ትንቢት ለማሟላት በጣም ዘግይቶ ነው
የተወለደው! ስለዚህ ኢየሱስ ብቻ ነው መሲሁ ሊሆን የሚችለው ብቸኛ አማራጭ፡፡

የዳንኤል መጽሐፍ መሲሁ የግድ ሊመጣ የሚገባበትን ጊዜ እና ሊሎች በርካታ ነገሮችንም ለይቶ አስቀምጧል፡፡

መልአኩ ገብርኤል ለዳንኤል እንደገለጸው፤ 24. ዓመፃን ይጨርስ፥ ኃጢአትንም ይፈጽም፥ በደልንም ያስተሰርይ፥
የዘላለምን ጽድቅ ያገባ፥ ራእይንና ትንቢትን ያትም፥ ቅዱሰ ቅዱሳኑንም ይቀባ ዘንድ በሕዝብህና በቅድስት ከተማህ
ላይ ሰባ ሱባዔ ተቀጥሮአል። 25. ስለዚህ እወቅ አስተውልም ኢየሩሳሌምን መጠገንና መሥራት ትእዛዙ ከሚወጣበት
ጀምሮ እስከ አለቃው እስከ መሢሕ ድረስ ሰባት ሱባዔና ስድሳ ሁለት ሱባዔ ይሆናል እርስዋም በጭንቀት ዘመን
ከጎዳናና ከቅጥር ጋር ትሠራለች። 26. ከስድሳ ሁለት ጊዜ ሰባትም በኋላ መሢሕ ይገደላል፥. . . (ዳንኤል 9፡24-26ለ)፡፡

ሰባት ሰባቶች ማለት የሰባት ዓመታት ሰባት ቡድኖች ወይም49 አመታት ማለት ነው፡፡ ደግሞም ስድሳ ሁለት
ሰባቶች ማለት የሰባት ዓመታት ስድሳ ሁለት ቡድኖች ወይም434 ዓመታት በአጠቃላይ ድምርም483 ዓመታት
ማለት ነው፡፡
1 የመጽሐፍ ቅዱስን‹‹መደበኛ የጸሐይ ዓመታት››2 አቆጣጠር በመጠቀም ከአዳም መፈጠር3 ዶ/ር
ዴቪድ ኩፐር እንዳጠኑት ከቂሮስ ንጉስ አዋጅ አመት ይኸውም በባቢሎን ግዞተኛ የነበሩትን አይሁዶች ወደ
እየሩሳሌም ተመልሰው ይሁዳን እንዲያድሱ እና እየሩሳሌምን እንደገና እንዲገነቡ፤ እየሩሳሌም እስክተገነባ ድረስ49
ዓመታት ነበር እናም ከ434 አመታት በኋላ መሲሁ ይገደላል፡፡
3
‹‹ከተገኙ አጠቃላይ መረጃዎች መመልከት
እንደምንችለው በአጠቃላይ የ483 ክፍለ ጊዜ ማብቂያ ዕለት የመሲሁ መወገድ ወይም ስለሕዝቡ ኃጢያት ሲል
የሚሰቀልበት ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ድምዳሜ በመነሳት ምንም አይነት ማምለጫ ሊኖር አይችልም፡፡››


‹‹እንደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ፤ ቅደም ተከተላዊ መረጃ ቂሮስ አዋጁን ያወጀበት ዓመት3589 ኤ. ኤች. ነው፡፡ ይህም
ማለት አኖ ሆሚኒሰ[የሰዎች አመት ወይም የፀሃይ ዓመት] ይህን ቀን የመበየኛው ስልት የሚጀምረው ከአዳመ
ፍጥረት ጋር አብሮ ሊሄድ ከሚችለው እና ታሪካዊ ቅድም ተከተሉን በቴናኽ(የእብራይስጥ መጸሕፍት) ውስጥ
ሙሉ ለሙሉ በመከተል ብሎም በ3589 ዓመት ላይ ቂሮስ በመልአኩ ገብርኤል አስቀድሞ እንደተነገረው አዋጁን
አወጣ፡፡››


አንድ ሰው በ3589 ኤ.ኤች. ላይ483 ኤ. አች. ዓመታትን ቢደምር4072 ኤ.ኤች ላይ ይደርሳል፡፡ በመጽሐፍ
ቅዱሳዊ የዓለም የጊዜ ቀመር መስመር ስሌት መሠረት ኢየሱስ የተሰቀለበት ዓመት4071 ኤ. ኤች. ነው፡፡
6

የስሌቶቹ አሻሚነትን ከግምት ውስጥ በማስገባት፤ የአንድ ዓመት መምታታት ለዚህ ጽሑፍ አቅራቢ በቀላሉ ሊታይ
የሚችል ቢሆንም ነገር ግን ቂሮስ አዋጁን ያወጀበትን ትክክለኛ ቀን ማንም ያሚያውቀው ከማይመስልበት እውነታ
በመነሳት በፍጹም በቀላሉ ሊብራራ አይችልም፡፡ ገብርኤል የጠቀሰው መሲህ የናዝሬቱ ኢየሱስን እንደሆነ ምንም
አይነት ምክንያታዊ አጠራጣሪ ነገር ማግኘት አይቻልም፡፡ በዚህ ነጥብ በርካታ ታላላቅ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን
ይስማማሉ፡፡

ትንቢቱ በተጨማሪም ከ62 ሰባቶች በኋላ መሲሁ እንደሚገደል እንደሚያውጅ አስተውሉ፤ ነገር ግን ከሰባው
ሰባቶች በኋላ የጽድቅን ዘመን ያመጣል፡፡ ከተገደለ በኋላ እንዴት ብሎ የጽድቅን ዘመን ያመጣል? አንድ መንገድ
ብቻ አለ፤ በትንሳኤ ከተነሳ፡፡

አዎ፤ ኢየሱስ፤ መሲሁ ታርዶ የነበረው፤ ግን ለራሱ አልነበረም፤ እንደ ድል አድራጊ ንጉሥ ሆኖ ይመለሳል፤
እናም ይሄ የሚሆነው በዛ የወደፊት እና ኤርሚያስ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፥ (ኤርሚያስ30፡7) ብሎ
በጠራው ጊዜ ከሰባኛው የሰባት ዓመታት ቡድን በኋላ ነው፡፡ ከዚያም እርሱ በኢየሩሳሌም ካለው ዙፋኑ ሆኖ
ይገዛል፤ የእስራኤል ሃብትን ይመልሳል፣ እናም የጽድቅ ዘመንን በመላው ዓለም ያመጣል፡፡

በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ
ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። (ኢሳይያስ 2፡4)

በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው። እግዚአብሔር
ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ። (ዘካርያስ 8፡23)

ፍጹም አይሁዳዊ የሆነው እና ሙሉ ለሙሉ በአይሁዳውያን ጸሐፍያን የተጻፈው(ሮሜ 3፡1-2) አዲስ ኪዳን፤
ከይሁዳ ነገድ መሆኑን የሚያሳየውን የኢየሱስን የትውልድ ሃረግ ያቀርባል(ማቴዎስ 1፡1-17፤ ሉቃስ 3፡23-38)፡፡

እናም በእብራውያን ቅዱሳት መጻሕፍት ስለመሲሁ የተተነበዩትን በርካታ ነገሮች እርሱ እንደፈጸማቸው
ይዘረዝራል፡፡ በዚህም መሲሁን ለማወቅ የሚያስችሉትን ሦስቱን የመምህርነት/የቤተ መቅደስ አዛዥነት ምልክቶች
በየስማቸው ለመግለጽ ያህልም አይሁዳዊ ለምጻምን መፈወስ፣ እውር ሆኖ የተወለደውን ሰው መፈወስ እና ዱዳውን
ሰይጣን ማስወጣት እንዴት እንደፈጸመ ዘርዝሯል፡፡ እንዲሁም እንዴት ጽድቅን የሚያስተዋውቅ የጽድቅ ህይወትን
እንደኖረ፤ ኢፍትሃዊነትን በመቃወም እና የታመሙትን በመፈወስ እንደኖረ፤ በዘመኑ ለነበሩት የተበላሹ መሪዎች
ስጋት ስለሆነ እንዴት እንደተሰቀለ፤ በትንሳኤ መነሳቱን እና ወደ ሰማይ ማረጉን፤ ከዚያም ወደፊት ይህንን ክፉ
የዓለም አሠራር ሊያስወግድ ተመልሶ መምጣቱን እናም እስራኤልን ለዘለአለም ከጠላቶቿ ነጻ እንደሚያወጣት እና
መንግስቱን እንደሚመሰርት ይናገራል፡፡

እርሱ ገና የምድር ንጉሥ አልሆነም፣ ነገር ግን አሁን የልቦቻችን ንጉሥ ሊሆን ይፈልጋል፡፡ እርሱ ምድርን ገና
ከድካም ነጻ አላወጣም፤ ነገር ግን አሁን በልቦቻችን ውስጥ ያለውን ድካም እንዲያሸንፍ እንድንፈቅድለት ይሻል፡፡

እናም ይህንንም በቀላሉ በእኛ በእርሱ በመታመን መሠረት ላይ ያደርገዋል፡፡ በእንባቆም 2፡4 ላይ እንደተባለው፤
ጻድቅ ግን በእምነቱ በሕይወት ይኖራል።

ምንን የግድ ልናምን ይገባናል? እግዚአብሔር በዘሌዋውያን 17፡11 ላይ የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና
ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ
ሰጠሁት። እግዚአብሔር ስለ እኛ ፋንታ ኃጢያትን ይቅር ለማለት እና እኛን ከኃጢያት ለማንጻት የንጹህ ደም
መፍሰስን የግድ ይጠብቃል፤ እናም መሲሁ ኢየሱስ በሙሴ ህግ የታዘዘው የክህነት መስዋዕት ሁሉ በሙላት
መፈጸሚያ ነው፡፡ እኛም በቀላሉ መሲሁ ለኃጢያታችን ሲል በኛ ቦታ በመስቀል ላይ የመሞቱን እውነታ ከያዝን
እና እዚአብሔር ከሙታን እንዳስነሳው በልባችን ካመንን፤ እግዚአብሔር ኃጢያታችንን ይቅር ይለናል፡፡ ከዚያም
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል የቅድስና ህይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤ እናም ስንሞት ወደ መንግስተ ሰማይ
ይመራናል፡፡

ኢየሱስ ኃጢያት የሌለበት ሰው ስለሆነ እና እርሱ በኢሳይያስ9፡6 ላይ በግልጽ እንደተመለከተው እግዚአብሔር
ስለነበረ እና አሁንም ስለሆነ በእኛ ቦታ ሊሞትልን ቻለ፡፡ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና
አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ
ይጠራል። አዎ የእግዚአብሔር ልጅ ስለሚወዳችሁ ስለኃጢያታችሁ በእናንተ ቦታ ሞተ፤ በእርሱ የሚያምን ሁሉ
የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ
ወዶአልና። (ዮሐንስ 3፡16)

ደግሞም ነብዩ ዘካርያስ እግዚአብሔር አንድ ቀን እንዴት መላው እስራኤልን በጠቅላላ መሲሁን ወደ ማወቅ
አንሚያመጣቸው አውጇል፡ በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ
አፈስሳለሁ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም
ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል። (ዘካርያስ 12፡10)

ነብዩ ኢሳይያስም በዛ ቀን እስራኤል እንደምታለቅስ ተናግሯል፡ 4. በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም
ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።5. እርሱ ግን ስለ
መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ
ተፈወስን።6. እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ
እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።(ኢሳይያስ 53፡4-6)

ዘካርያስ ደግሞ በ 13፡1 ላይ፡ በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ
ምንጭ ይከፈታል። ብሏል፡፡

ይህ ሁሉ የሚሆነው እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር የሚያደርገውን አዲስ ቃል ኪዳን ወደ ፍጻሜ ለማምጣት ነው፡
31. እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል፥ ይላል

እግዚአብሔር፡ 32. ከግብጽ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ
ቃል ኪዳን አይደለም እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር፦ 33. ከእነዚያ
ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግዚአብሔር ሕጌን በልቡናቸው
አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል። 34. እያንዳንዱ ሰው
ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን እወቅ ብሎ አያስተምርም ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ
ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር፦ በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኃጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ
አላስብምና። (ኤርሚያስ 31፡31-34)

ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር፡፡ በዛ የወደፊት ቀን እና ተከትሎ
በሚመጣው በመሲሁ መንግስት እያንዳንዱ ህያው የሆነ አይሁዳዊ ኢየሱስን እንደ ታረደላቸው የፋሲካ በግ እና
እንደ የስርየት ቀን መስዋዕት፤ እንደ ታዳጊያቸው እና መሲሃቸው አድርገው ያውቁታል ይቀበሉታልም፡፡

እናንተም በተመሳሳይ መንገድ በዚህች ቅጽበት ልትቀበሉት ትችላላችሁ፡፡ ራባይ ሳውል(ሓዋርያው ጳውሎስ
ተብሎም ይጠራል) እንዳብራራው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና።(2ኛ.
ቆሮንቶስ 5፡19)፡፡ የኃጢያት እዳችሁ ተከፍሏል፡፡ እናንተ ልትሠሩት የሚገባው የቀረ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር
ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። (ቁጥር 20) እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ያለውን የድልድዩን በር ክፍት
አድርጎ ይዞታል፡፡ በመሲሁ ታመኑ፤ ለእናንተ የሞተውን እና እንደገና የተነሳውን፤ እናም እግዚአብሔር
ከኃጢያታችሁ ይቅር ይላችኋል፤ ልክ እግዚአብሔር እርሱን ከሞት እንዳስነሳው እናንተንም ወደ አዲስ እና ክብር
የሞላበት ህይወት ያስነሳችኋል፡፡ በልባችሁ መኖሪያውን ያበጃል፤ በራሱ መቼም የማይቆም ክብር እና ቅዱስ
መገኘት የማያልቁ የዘለዓለም ህይወት በረከቶችን ይሞላችኋል፡፡ እጅግ ከፍ ያለውን እና ማንም ሊያገኘው
ከሚችለው ሁሉ በላይ ከሁሉም የተባረከውን ጥሪ ይኸውም እንደ እርሱ አምባሳደሮች ሆናችሁ ማገልገል
እንድትችሉ ህይወታችሁን ወደ መንፈሳዊ ማንነት ይለውጠዋል፡፡ በዚህም እናንተ ሌሎችን ወደ እርሱ ደኅንነት
በረከት መምራት ትችላላችሁ፡፡

ራባይ ሳውል፤ ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን
በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤. . . መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን
ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥(1ኛ ቆሮንቶስ 15፡1-4)

አዎ፤ ልክ እስራኤላውያን በግብጽ በበራቸው መቃን እና ጉበን ላይ የፋሲካ በግ ደም በማድረጋቸው የበኩር
ልጆቻቸውን ከሞት እንዳዳኑት እናንተም ከኃጢያት ቅጣት ይኸውም ሰቆቃ ወዳለበት በመሄድ ለዘለዓለም
ከእግዚአብሔር ከመለየት ትተርፋላችሁ፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና፤(1ኛ ቆሮንቶስ 5፡7) ልክ የፍየል ደም
ለስርየት ቀን መስዋዕት እንደሚፈስስ እና በምልክትነት የእስራኤልን ኃጢያት ወደ በረሃ እንደሚላክ(ዘሌዋዊያን 16፡7-10)፤
እንደዚሁ አንድ ቀን የእስራኤል ሁሉ ኃጢያት በክርስቶስ ቤዛነት ሥራ ይቅር ይባላል፡፡ ለምን በዚህ

ሰዐት ልባችሁን ወደ እግዚአብሔር አታነሱም እና ልጁን በቤዛነት ለእናንተ ስለሰጣችሁ እና ከኃጢያታችሁ ሁሉ
ይቅር ስላላችሁ አታመሰግኑትም? ምላሻችሁን ይጠብቃል፡፡ እያደመጠም ነው፡፡

የእናንተው አይሁዳዊ ወንድም


ናሁም ቤን አቭራሃም

 በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. * 

 

የግርጌ ማስታወሻዎች

1. እነዛ ሳምንታት እዚህ ጋ የታሰቡት በትንቢቱ ዓውድ እና በሌሎች ሳምንታትን እንደ ሰባት አመት ወቅቶች በሚቆጥሩት የመጽሐፍ አጠቃቀሞች እንደ የሰባት ዓመታት ተደርገው ነው፡፡
የዶ/ር ዴቪድ ኩፐርን“The Seventy Weeks of Daniel”; http://ariel.org/dlc/dlc-bk-swd02.htm. ምዕራፍ2, ክፍልII. A. ይመልከቱ፡፡
2. ዶ/ር ኩፐር ዳንኤል ባጠናቸው መጸሕፍት ላይ መሠረት አድርገው ዓመታቱ‹‹መደበኛ የጸሐይ ዓመታት›› እንደሆኑ በይነዋል፡፡ ኩፐር፡፡ ምዕራፍ2፡፡ ክፍል2 ንኡስ ክፍል2፡፡ ለ.፤ አንቀጾች1-3፡፡
3. ኩፐር፡፡ ምዕራፍ2፡፡ ክፍል4 የመጨረሻው አንቀጽ፡፡
4. ኩፐር፡፡ ምዕራፍ2፡፡ ክፍል5 የመጨረሻው አንቀጽ፡፡
5. ኩፐር፡፡ ምዕራፍ2፡፡ ክፍል4 የመጨረሻው አንቀጽ፡፡
6. World Timeline of Biblical History,
http://thewordnotes.com/worldtl.htm.

ለተጨማሪ ምንባብ

ዶ/ር ዴቪድ ኩፐር“Messiah: His First Coming Scheduled”; http://biblicalresearch.info/page1d.html, በተለይ ምዕራፍ. 3, 12, 13.

በዶ/ር ኩፐር ገለጻ መሠረት በ“The Shepherd of Israel” at http://www.biblicalresearch.info/page900.html, “አጠቃላይ የአኖ ሆሚኒስ ስልት በኔMessiah: His First Coming Scheduled. መጽሐፍ ውስጥ ተተንትኗል”፡፡

Fruchtenbaum, Dr. Arnold G. Messianic Bible Study 067: The Seventy Sevens of Daniel. በተለያዩ ይዘቶች በሚከተለው ዌብ ሳይት ላይ ቀርቧል፡፡ www.ariel.org.


 

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines