የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ጥናትየተባረከ ህይወት ቁልፍ

(THE KEY TO A BLESSED LIFE) 
Original English By Norman Manzon
Translation By Zemen Endale Lashetew

 


ናንት ውድ ቤተ እስራኤላውያን ወንድሞቼ እና እህቶቼ፤

ራባይ ሳውል፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም
ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው
(የሐዋ. 17፡26) ብሏል፡፡

እኛ ከተለያዩ ዓለማት የመጣን ብንሆንም ነገር ግን ተመሳሳይ ነን፡፡ ሁላችን በልባችን
ውስጥ ያሉትን ጥልቅ የሆኑ ጥያቄዎችን እንደ የህይወትን ትርጉም ማግኘት እና ሌሎችን
ልንባርክበት የምንችለውን ወደ ተባረከ ህይወት የሚያስገባውን በር ቁልፍ ማግኘት ያሉትን
መልስ ለመስጠት እንሞክራለን፡፡ እኔና ሌሎች ብዙዎች ይህን ቁልፍ አግኝተውታል፡፡

የኔን ግኝት ታሪክ እንድትመለከቱት እለምናችኋለሁ፡፡

እኔ በኒው ዮርክ ከተማ እውነተኛ(Orthodox) አይሁድ ሆኜ ነበር ያደግኩት፡፡ የሙሴን አምስት
መጻሕፍት፣ የአንዳንዶቹን ራባዮች ጽሑፎች እና እንዴት ትክክለኛውን (Orthodox) የአይሁድ
ሕግ መፈጸም እንደሚቻል እንደ የመጀመሪያ ደረጃ ትምሕርቴ አካል ተደርገው
ተምሬያቸዋለሁ፡፡ የአፍላ ወጣትነት ዕድሜዬ ላይ ስደርስም፤ ምንም ሊያረኩኝ ስላልቻሉ
ከመደበኛዎቹ የተለመዱ ኃይማኖታዊ ተግባራት ተለየሁ እና ከአይሁድ ክበብ ውጪ ያለውን
ዓለም መመርመር ጀመርኩ፡፡

የህክምና ትምሕርት ለመማር የሚያበቃኝን የኮሌጅ ትምሕርት ጀመርኩ ነገር ግን በውስጤ ያለው
ጥልቅ ጥማት ጥብቅ በሆኑ እውነታዎች ላይ በተመሰረቱት እና ከፍ ያለ የማስታወስ ችሎታ
በሚጠይቁት እንድወስዳቸው በምገደዳቸው ትምህርቶች ላይ ማተኮር እንዳልችል አደረገኝ፡፡

ስለዚህም ፊቴን በቀላሉ ላነበው እና ልደሰትበት ብሎም የደራሲያኑን አመለካከቶች በማየት
የራሴን አመለካከት ለማዳበር እንድችል ወደ የእንግሊዘኛ ሥነ ጽሑፍ ፊቴን አዞርኩ፡፡ ይህንኑ
ለማጠናከርም የፍልስፍናና እና የተነጻጻሪ ኃይማኖቶች ኮርሶችም ወሰድኩ፡፡ የኮሌጅ መዘምራን
ቡድንን ተቀላቅዬም ያለፉትን ሰባት መቶ ዓመታት በጣም ድንቅ የሆኑ በርካታ ታሪካዊ ሥራዎች
ዘመርን፡፡ ጌታ በአስደናቂ መንገዶች ይሠራል፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳየው እርሱ ጥንታዊ
መልዕክቶችን( ገና በታዳነቴ ካጠናኋቸው በእብራይስጥ ከተጻፉ ቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን
ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍትም ጭምር) በልቤ ላይ ለመትከል እንዴት ያንን የመዘምራን ቡድን
አባልነቴን እንደተጠቀመበት ማየት ችያለሁ፡፡ እነዛ ምንባቦች ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳን፣
የመሲሁ ኢየሱስን ፍቅር እና ኃይል የሚናገሩ ነበሩ፡፡

ከኮሌጅ ስመረቅ ማኅበረሰቡን ስሜ ተሰናበትኩ እና አስቀድሜ ወደ ማውቀው የደስታ አኗኗር፣
የአዲስ ነገር አሰሳ፣ መቀዣበር ውስጥ ወደ ሚከቱ እጾች እና ለተጨማሪ ምርምር በኃይማኖቶች፣
ፍልስፍናዎች እና ዓለማዊ የህይወት ዝይቤዎች ውስጥ በእግሬ እና በአእምሮዬ ዘው ብዬ ገባሁ፡፡

ሃያ ሦስት ዓመት ሲሆነኝ በቅርብ ሚስቴ የምትሆነውን ወጣት ሴት ሱዛንን ተዋወቅኩ፡፡ ብዙም
ሳይቆይ በምዕራብ ዳርቻዎች እና በደቡብ ምዕራባዊ አሜሪካ ከመንደር መንደር ከየአዲሱ ዘመን
እንቅስቃሴ ዝግጅት ወደ አሽራም(የሂንዱ እምነት ተከታዮች ዝግጅት)፤ ሊፍት(በመኪና ጭነው
እንዲወስዱን) ለማግኘት የሚያስችል ወርቃማ የልመና እጅ ይዘን፤ ህጻን ሴት ልጅ እና በዚህች
ምድር ላይ ያለንን ሃብት(በአብዛኛው የሽንት ጨርቆች እና ብርድ ልብሶች ናቸው፡፡) የያዘ የጉዞ
ሻንጣ ይዘን በየመንገዱ የሚሄድ መኪና እየተለመነ የሚኬድበት ጉዞ አብዛኛውን ጊዜ የት ልናድር
እንደምንችል ሳናውቅ ምሽቱን በኒው ሜክሲኮ ባሉት በሚያማምሩ የመሲሁ ደም ተራሮች ላይ
ይሁን፤ በከተማ ውስጥ ባለ የተጨናነቀ አፓርታማ ከሌሎች ተጓዦች ጋር ይሁን፤ ጫካ ውስጥ
ከተጣለ በቆየ ማደሪያ ያለው ተጎታች መጫኛ ላይ ወይም በሎስ አንጀለስ ባለው ቤተ መንግስት
መሳይ የክሪሽና ቤተ መቅደስ ወይም የደህንነት ሠራዊት ባዘጋጀልን ሆቴል ወይም ወደ ውስጥ
እንድንገባ በፈቀዱልን ደግ ቤተሰቦች ቤት ወይም እርሻ ውስጥ እያደርን በነጻ የልመና የመኪና
ጉዞ ወደ ላይ ወደ ታች ስንል ከረምን፡፡

በዚህች ህይወቴ ለዘለአለም ከኔ ጋር የሚኖረው አንድ ትዝታዬ እኔና ሚስቴ በአንድ አውራ ጎዳና
ጠርዝ ላይ እኔና ሚስቴ ህጻን ሴት ልጃችንን ይዘን በዝናብ በስብሰን ከብዙ መቶ እና መቶ
መኪናዎች መካከል እንደ የለሊት መናፍስት የግንባር መብራታቸውን ቦግ እያደረጉብን ከሚሄዱት
መካከል የሚያሳፍረን መኪና ለማግኘት ስንሞክር ነው፡፡

እነዛ ቀናት ለበርካታ ነገሮች አይኖቻችንን ከፍተዋል፤ አለም አቀፋዊ አመለካከት እና የህይወት
ዘይቤ ለማግኘት በራሳችን መንገድ ብለን ያካሄድነው አሰሳችን ግን ከአንድ ውድቀት ወደ ሌላ
ውድቀት የሚሸጋገር ነበር፡፡ በመጨረሻም አንድ ሰው በአገሩ የሚበቅለውን ፍራፍሬ በነጻ እየበላ
እንደሚኖርባት ወደ ሰማናት ሃዋዪ በአራት መቶ አስደናቂ ሄክታር መሬት ላይ ለመኖር በረርን፡፡

በአገሩ ለአንድ የኒው ዮርክ ልጅ ለመረዳት እጅግ ሊያስደንቅ በሚችል ሁኔታ የተትረፈረፈ
መልካም ፍራፍሬ ነበር፤ አራት መቶ ሄክታር የተባለው መሬት ግን በምትሃት ተጨምቆ ወደ
አራት ወረዷል፤ እኛም ያለምንም ውሃ እና መብራት አገልግሎት ከሌሎች ጋር ተዳብለን በአሮጌ
ጎጆ ውስጥ ነበር የኖርነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ በከባድ ሁኔታ ይዘንብ ነበር፡፡ እኛ በፍራፍሬው
ስንንበሻበሽ ፈረስ ፈረስ የሚያካክሉ ትንኞች ደግሞ በኛ ይንበሻበሹ ነበር፡፡ እኔ በጣም ከስቼ እና
እግሬ ላይ የከፋ የቆዳ ቁስለት(ኢንፌክሽን) ወጣብኝ፤ ትዳራችንም ወደ በረዶነት ተቀየረ፡፡ ችላ
ሊባል በማይችል ጭንቀት ውስጥም ገባሁ እና የሆነ የባህር ማዕበል መጥቶ ይገላግለኛል ወይም
ኒውክሌር ቦምብ ጭንቅላቴ ላይ ወድቆ ሁሉንም እንዲያበቃ ያደርገዋል ብዬ ተስፋ ማድረግ
ጀመርኩ፡፡ ልክ በዚህ ሰአት እግዚአብሔር ከመንግስተ ሰማይ ቁልቁል ተመልክቶ ‹‹አሁን ዝግጁ
ነው፡፡›› ሳይል አይቀርም፡፡

አንድ ቀን ከሚያምረው ሰማያዊው የሃዋዪ ሰማይ ስር ባለች በአንድ አሮጌ ወለል አልባ፣ ጣራ
አልባ የድንጋይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጅግ የተዋበ እና በአበባ የተንቆጠቆጠ የሃይቅ ዳርቻ
ሠርግ ታደምኩ፡፡ ሙሽራው እና ሙሽሪቱ እንዴት ወደ መሲሁ እንደመጡ እና በህይወታቸው
ያመጣቸውን አስደናቂ ለውጦች መሰከሩ፡፡ አገልጋዩ ደስ በሚል የተለመደ አላባበስ ጋብቻ
አንዴት የመሲሁን እና የእርሱን ተከታዮች ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ሊሆን እንደሚገባው ይኸውም
መሲሁ ለእርሷ ካለው ወሰን የለሽ ፍቅር የተነሳ እንዴት እራሱን ለቤተ ክርስቲያን አሳልፎ
እንደሰጠ እና የእርሱ ተከታዮች ከእርሱ የፍቅር እራስን አሳልፎ መስጠት የተነሳ እንዴት
እንደሚወዱት እና እንደሚያገለግሉት ተናገረ፡፡ ይሁንና በቀድሞው ህይወቴ በመንፈሳዊ
እንቅስቃሴዎች እና መሪዎች ግራ መጋባት ውስጥ የገባሁ ብሆንም አገልጋዩን ‹‹ምናልባት አንተ
ልትረዳኝ ትችላለህ፡፡›› ልለው ሄድኩ፡፡ ስለ እየሱስ ብዙ ሞገትኩት፤ እርሱም ለእያንዳንዱ
ጥያቄ እና ሙግት መጽሓፍ ቅዱሱ ውስጥ ያለ አንድ ገጽ የገልጥ እና ያነባል፤ በመየነበው
የትኘውም ምንባብ የሆነ እውነት ወደ ልቤ ያቃጭላል፡፡ ስብሰባዎቻቸውን ተካፈልኩ፤
ለምጠይቀው ለእያንዳንዱ ጥያቄ አርኪ የሆኑ መልሶችን አገኘሁ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላም
ህይወቴን ለአዳኙ ሰጠሁ እና ከዛች አሮጌ የድንጋይ ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በሰማያዊው የሃዋዪ
ውሃ ውስጥ ተከተትኩ፡፡ የመሲሁ ኢየሱስ የህይወት መንፈስ እየሞተ በነበረው የኔ መንፈስ ላይ
አዲስ ህይወትን እፍ አለበት፤ ተስፋ ብሩህ ተስፋ እና ደስታ ወደ ህይወቴ ተመለሱ፡፡

መጽሓፍ ቅዱስ ኮሌጅ ወይም ሴሚናሪ ፈጽሞ ገብቼ አላውቅም፤ ነገር ግን ስለእውነት ዋጋ
ከፈልኩ፡፡ እናቴ የኢየሱስ ተከታይ መሆኔን ስትሰማ የሙት መታሰቢያ ሻማ ልትለኩስ ምንም
አልቀራት ነገር ግን ወንድሜ አናግሮ አስተዋት፡፡ በ1979 እኔና ሱዛን ቤታችንን ሸጥንና እኔ
የጌታን ፍቅር ከአይሁዳዊ ልብ ለጀርመኖች እና ለሙስሊሞች በማካፈል ወዳገለገልኩበት አውሮፓ
ሄድን፡፡ ከሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ሃዋዪ ከሚስቴ እና ሁለት ልጆቼ ጋር ምንም ገንዘብ፣ ቤት
እና ሥራ ሳይኖረን ተመለስን፡፡ እግዚአብሔር ግን በፍጥነት መንገድ አዘጋጀልን፤ ይሄ ግን ሌላ
እራሱን የቻለ ታሪክ ነው፡፡ ላካፍላችሁ የምችለው በርካታ ምሳሌዎች አሉኝ፤ ነገር ግን በቀላሉ
አንድ ሰው ስለ እውነት ለሚከፍለው የትኛውም ዋጋ እግዚአብሔር እጅግ ብዙ ግዜ እጥፍ
እንደሚከፍለው እናገራለሁ፡፡

ኢየሱስ፤ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥
ይከፈትላችሁማል
(ማቴዎስ7፡7) ብሏል፡፡


በነብዩ በኢሳያስ በኩል እግዚአብሔር፤

እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፥ ወደ ውኃ ኑ፥ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ። ገንዘብን
እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው

~ ኢሳይያስ 55:1-2 ~

ብሏል፡፡

እናንተ የእግዚአብሔርን ፍቅር በግላችሁ እስከአሁን ያለወቃችሁ ከሆነ፤ የእግዚአብሔር ብርሃን
ልክ የእኔን ጨለማ ሰንጥቆ እንደገባ በቀጥታ ወደ ልባችሁ ሰንጥቆ ሊገባ ይችላል ብዬ ስግራችሁ
እመኑኝ፡፡ ለብዙ ዓመታት ቅዠት ዓለም ውስጥ የሚከቱ እጾችን በመውሰዴ እና በእርኩሰታዊ
ልምምዶች፣ ሰይጣናዊ ኃይማኖቶች እና የሐሰት ፍልስፍናዎች ውስጥ በመሳተፌ በአጋንንቶች
ተሞልቼ ነበር፡፡ የኢየሱስ ደም ግን ነጻ አደረገኝ!

ኃጢያት የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ መለኮታዊ በሆነ ፍቅሩ ወዷችኋል እናም የኃጢያታችሁን
ዋጋ የራሱን ደም በመስቀል ላይ ከፍሎአል፡፡ በ2ኛ ቆሮንቶስ5፡19፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ
ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና
፡፡ የኃጢያታችሁ ዋጋ ተከፍሏል፡፡ ልታደርጉት

የሚገባው የቀራችሁ ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ (ቁጥር20) የሚለውን መፈጸም ነው፡፡

እግዚአብሔር በእርሱ በኩል ያለውን የድልድዩን መጨረሻ በር ከፍቷል፡፡ እናንተ ልታደርጉ
የሚገባችሁ ነገር በእናንተ በኩል ያለውን የድልድዩን መጨረሻ በር መክፈት እና ወደ እቅፉ
መሮጥ ነው፡፡ በየደህንነቱ መልካም ዜና እመኑ ከዚያም እግዚአብሔር ኃጢያታችሁን ይቅር
ይላል፡፡ በልባችሁ ውስጥ ያለውን የእርሱን የመኖሪያ ቦታ ይወስዳል፤ እንደ የእርሱ አምባሳደሮች
እንድታገለግሉት ህይወታችሁን መንፈሳዊ አድርጎ ይለውጠዋል፤ ከዚያም ወዲያውኑ የዘለአለማዊ
ህይወትን ማቆሚያ የሌለው በረከት መቼም ከማይቆመው የእርሱ መገኘት ጋር ይለግሳችኋል፡፡

ራባይ ሳውል (በኢየሱስ አማኞች መልዕክተኛው ጳውሎስ በሚል ስምም ይታወቃል) እንዲህ ሲል
መልካሙን የምስራች ተናግሯል፡፡

ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤. . . . እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥


~ 1ኛ ቆሮንቶስ15፡1-4~

ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥
በዚህ እመኑ እና ዳኑ
፡፡


ልክ መሲሁ ለኃጢያታችሁ እንደሞተ እርሱ ለእናንተ ያደረገውን የቤዛነት ሥራ ማመናችሁ
እግዚአብሔር በህይወታችሁ ላይ የነበሩት የኃጢያት ክስ እና ኃይል እንዲሞቱ ያደርግ እና
መሲሁ ተቀብሮ እንደነበረው ይቀብራቸዋል፡፡ ከዚያም ልክ እርሱ በኃጢያት፣ በሰይጣን እና
በሞት ላይ ድል ተቀዳጅቶ ከሞት እንደተነሳው እግዚአብሔር ወደ ድል አድራጊነት፣ ወደ
አዲስ፣ ተንሳኤን ወዳገኘ እና በእርሱ የሆነ ዘለአለማዊ ህይወት ያስነሳችኋል፡፡ ከእግዚአብሔር
ጋር ተስማሙ
፡፡


እባካችሁ ቀጥሎ ያሉትን ልብ በሏቸው፡
ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤(ሮሜ3፡23)

የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን
የዘላለም ሕይወት ነው።
(ሮሜ6፡23)


በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ
ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።
(ዮሐንስ3፡16)


መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች
ሌላ የለምና።
(የሐዋርያት ሥራ4:12)


በእግዚአብሔር ልጅ ቤዛነት እመኑና ዳኑ፡፡ ለምን ልባችሁን አሁኑኑ ወደ እግዚአብሔር
አንስታችሁ ልጁን ስለእናንተ መስዋዕት ስላደረገው እና ከኃጢያታችሁ ሁሉ ይቅር ስላላችሁ
አታመሰግኑትም! ለዘለአለም በዚህኛው እና በመጪው ህይወታችሁ የእግዚአብሔርን በረከቶች
ታገኛላችሁ፡፡


በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. * 

 


 

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines