የእግዚአብሄር መገለጫዎች
(The Attributes of God)
By Norman Manzon
 

I. ወሰን የለሽነት

እግዚአብሔር ወሰን የለውም፡፡ እግዚአብሄር ወሰን የለውም ማለት የህልውናው መኖር በየትኛውም ቁሰዊ ነገር፣ የሀይል  ቅርጽ፣ ነፍስ፣ መንፈስ፣ አስተሳሰብ፣ ስሜት፣  ስፍራ፣ ወይም በየትኛውም ሌላ ነገር ወይም በመለኮታዊ ክስተት ወይም የተፈጥሮ ግዛት አይገለልም፣ በምንም መልክ አይገደብም ወይም አይወሰንም  ማለት ነው፡፡ 1 ነገስት 827 በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ፥ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም ይልቁንስ እኔ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!

II. ፍጽምና

እግዚአብሄር ፍጹም ነው፡፡ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ውስጥ ፍጹም ተብለው የተተረጎሙ የተለያዩ ቃላት አሉ ደግሞም በአጠቃላይ የተሟላ እና እጥረት እና እንከን የለሽ ሚል ትርጉም አላቸው፡፡ (ፍጹም የሚለው ቃል ለአማኝ ጥቅም ላይ ሲውል ብስለት ማለት ነው)፡፡ ማቴ 548 እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።

III.  ዘላለማዊነት

እርሱ ለዘላለም የሚኖር ነው፡፡ ዘላለማዊነት ማለት ጊዜን በተመለከተ ያለማቋረጥ ወይም ያለገደብ በሀላፊ፣ በአሁንና በወደፊት ጊዜአት ያለማቋረጥ የመኖር ብቃት ነው፡፡

 

መዝሙር 902 ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ። ዘዳግም 3327፡መኖሪያህ የዘላለም አምላክ ነው፥ የዘላለምም ክንዶች ከአንተ በታች ናቸው፤ ጠላትህን ከፊትህ አውጥቶ፦
አጥፋው ይላል።

IV. ስብእና

እግዚአብሔር ለዘላለም በሶስት እኩል አካላት ይኖራል፡፤ ምንም እንኳን እግዚአብሄር ሀይልን ቢጠቀምም ሀይል ብቻ አይደለም፤ የአጽናፈ አለሙ ጥቅል   እና ህይወት ያላቸው ነገሮች ድምርም አይደለም፡፡ በርግጥ እርሱ ከፍጥረቱ የተለየ እና ትክክለኛ ስብእና ያለው ነው፤ ሶስት አካል- ልክ እንደ አንተ እና  እኔ የስጋ ሰውነት አይደለም መንፈሳዊ ስብዕና እንጂ (ዮሐ 424)፡፡

በአጠቃላይ ስብእና ሶስት መሠረታዊ መገለጫዎች አሉት ተብሎ ይታመናል፡ እግዚአብሄርም እነዚህ ሶስት ነገሮች አሉት፡

. እውቀት

እውቀት የማሰብ የአመክንዮ እና የማቀድ ችሎታ ነው፡፡ ኢሳ 118 ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር

. ስሜት

ስሜት በሰው መንፈስ ውስጥ በሚለካ  መንገድ የመሰማት ችሎታ ነው፡፡

 ዘጸ 414 የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ  

 ኡፌ 430 የእግዚአብሔርንም መንፈስ አታሳዝኑ

ዘፍ 131 እግዚአብሔርም ያደረገውን ሁሉ አየ፥ እነሆም እጅግ መልካም ነበረ።  

እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

ኢሳ 5310

. ፈቃድ

ፈቃድ የነገሮችን የመምረጥ ችሎታ ነው

ዘፍ 13 እግዚአብሔርም፦ ብርሃን ይሁን አለ፤ ብርሃንም ሆነ።

V. በሁሉም ስፍራ መገኘት

እግዚአብሄር በሁሉም ስፍራ ይገኛል፡፡ ወሰን የለሽነት ከገደብ አንጻር የእግዚአብሄርን ህልውና ሲያመላክት በሁሉ ስፍራ መገኘት የእግዚአብሄርን ህልውና ከልክ አንጻር ያመለክታል፡፡ እግዚአብሔር በመላ ማንነቱ በሁሉም ጊዜ በሁሉም ስፍራ ይገኛል” (ዶክተር ቻርለስ ሪሪ፣ መሰረታዊ ስነመለኮት፡ ሙዲ ፕሬስ፣ 1981 ገጽ 41)፡፡

መዝሙር 1397-10

ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።

VI. ሁሉን ቻይነት

እግዚአብሄር ሁሉን ይችላል፡፡ ሁሉን ቻይ ማለት እግዚአብሄር ያለ ምንም ገደብ  ብርቱ ነው ደግሞም   በማንነቱ ልክ   ሁሉንም ነገር ማድረግ ይችላል ማለት ነው፡፡ ዘፍ 11 እግዚአብሄር በመጀመሪያ ሰማይና ምድርን ፈጠረ፡፡  ሐዋ ስራ 530 እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፡፡

እግዚአብሄር ምንም አንኳን ያለምንም ነገር መፍጠር እና ማስነሳት ቢችልም ከማንነቱ ተቃራኒ ለሆነ ለየትኛውም ነገር የማይችል ነው፡፡ ለምሳሌ አምላክ መሆኑን መተው አይችልም (ዘዳ 3327) ራሱን መካድ አይችልም ( ቃሉን ተመልከት) (2 ጢሞ 213) ለሀጢአት ፈተናዎች የማያወላውል ነው (ያቆብ 113) ሊዋሽ አይችልም (ቲቶ 12 እብ 618)፡፡ 

VII. ሁሉን አዋቂነት

እግዚአብሔር ሁሉን ያውቃል፡፡ ሁሉን ማወቅ ማለት በሁሉም ጊዜአት  በየትኛውም ግዛት   - - -   እስከ  - - -  የሁሉንም ነገሮች እውቀት ሙሉ በሙሉ መያዝ እና በትክክል ማወቅና ማወቅ መቻል ማለት ነው፡፡ ሐዋ ስራ 1518 ስራዎቹ በሙሉ አስቀድመው በእርሱ የታወቁ ነበሩ፡፡  መዝሙር 13916 ያልተሠራ አካሌን ዓይኖችህ አዩኝ፤ የተፈጠሩ ቀኖቼ ሁሉ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍህ ተጻፉ። እብ 413፡እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።

VIII. ፈጣሪ

እግዚአብር የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ ነው፡፡ ፈጣሪ አንዱ የእግዚአብሄር ማንነት አይደለም ከመጠሪያዎቹ አንዱ እንጂ፡፡ የእርሱ ሁሉንም ነገር መፍጠር በእርሱ ማንነቶች ሊሆን የቻለ ድርጊት ነው፡፡ እግዚአብሄር ከፍጥረቱ  ጋር አንድ አይደለም ከርሱ የተለየ ነው እንጂ፡፡ ፈጣሪ አለ ተፈጣሪም አለ፡፡ እግዚአብሔር ፈጣሪ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከሌሎቹ ነገሮች በሙሉ  አስቀድሞ የሚኖር ነው ከዚያም ሌሎቹን ነገሮች  በሙሉ ፈጠረ፡፡ ዘፍ 11 እግዚአብሔር በመጀመሪያ ሰማይንና ምድርን ፈጠረ፡፡   ቆላ  116 የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው፤ ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል፡፡

አፍተርዎርድ

እነዚህ ዝርዝሮች በምንም ሁኔታ ሁሉም እንደሆኑ መታሰብ የለበትም፡ አቤቱ አምላኬ፥ ያደረግኸው ተአምራት ብዙ ነው፥ አሳብህንም ምንም የሚመስለው የለም፤ ባወራም ብናገርም ከቍጥር ሁሉ በዛ።   መዝ 405

እግዚአብሄር አብ

በዚህ ጥናት ውስጥ እግዚአብሄር አብን በተመለከተ ቅዱሳት መጻህፍት ምን እንደሚናገሩ እንመረምራለን፡፡

እንደገና የንግግሩን አስፈላጊ ክፍል በማንበብ እንጀምር፡

ስላሴ- ሶስት አንድ

እግዚአብሔር አንድ እንደሆነ ራሱን ግን በተለያዩ እና በተለዩ ሶስት  አካላት እንደገለጠ እናምናለን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ስላሴ እንደሆነ እናምናለን፡፡ አብ፣ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ፡፡ እግዚአብሄር የሁሉም ነገር  ፈጣሪ ነው፡፡ የማይገደብ እና ፍጹም፣ እያንዳንዱ የአምላክነት ማንነትን እና የስብዕና ጠባይም በያዙ ሶስት እኩል አካላት ለዘላለም የሚኖር ነው፡፡ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ፣ ሁሉን የሚችልና ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ (ዘዳ 64 ኢሳ 4816 ማቴ 2819 ዮሐ 627 ሐዋ ስራ 53-4 2 ቆሮ 1314 እብ 18)፡፡

በንግግሩ ውስጥ ስብዕና ማለት ዋናዋና መገለጫዎቹ እውቀት፣ የማሰብ ችሎታ፣ አመክንዮ እና ማሰብ፤ ስሜት  በአንድ ሰው መንፈስ በሚነካ  ሁኔታ  የመሰማት ችሎታ እና ፈቃድ፣ የሆነ ነገርን የመምረጥ ችሎታ የሆኑ   ሰውነት ማለት ነው፡፡

እግዚአብሔር አብ

መግለጫው  እንዲህ ይቀጥላል፡

ክፍል 1 እግዚአብሔር አብ በፍጥረታቱ ሁሉ ላይ አባት እንደሆነና  ስለዚህም የፍጥረቱ ልኡል ገዢ መሆኑን እናምናለን፤ እንደልዩ ህዝቡ አድርጎ የመረጠው የእስራኤል አባት፤ የሰው ዘርን እና ፍጥረትን  እንዲዋጅ ወደ አለም የላከው የመሲሁ የጆሹዋ (ኢየሱስ) አባት፤ ደግሞም በበጎ ስጦታው ለሚያምን ሁሉ አባት እንደሆነ እናምናለን ፡፡

(ዘጸ  422 ማቴ 317 ዮሐ 112 316 ሐዋ ስራ 1729 ገላ 326)፡፡

እግዚአብሔር አብ

1.    አብ እግዚአብሄር ነው፡፡ ገላ 13 ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

2.    አብ ሰው ነው፡፡  በዮሐ 316 ማየት እንደሚቻለው እግዚአብሄር እውቀት፣ ስሜት  እና ፈቃድ አለው፡፡  በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

. አብ እውቀት አለው፡፡  ለሰው ዘር ያላሰለሰ  ፍትህ እና መዋጀት ርካታ  እቅድን የሚያቅድ የትኛውም ፍጡር  እውቀት እንዳለው ግልጽ ነው፡፡

. አብ ስሜት አለው፡ ለአለም ያለው የእግዚአብሄር ፍቅር ስሜት እንዳለው ያሳያል

. አብ ፈቃድ አለው፡ ሀጢአተኞችን ለማዳን አንድያ ልጁን መስጠቱ በጎ ፈቃድ አንዳለው ያሳያል፡፡

በፍጥረታት ሁሉ ላይ አባት መሆኑን እናምናለን

1 ቆሮ 86 ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን . . .  

ስለዚህ ደግሞ የፍጥረቱ ልኡል ገዚ

ኢዮብ 95-7 (እርሱ)ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትም፤  በቍጣውም ይገለብጣቸዋል። ምድርን ከስፍራው ያናውጣታል፥  ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ። ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ያትማል።

የእስራኤል አባት

ዘጸ 422 እግዚአብሄር እንዲህ ይላል እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤

ለራሱ ልዩ ህዝብ አድረጎ የመረጠውን

ዘዳ 76 ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ።

የመሲሁ የጆሹዋ(የኢየሱስ) አባት

ማቴ 317 እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

የሰውን ዘር እንዲዋጅ ወደ አለም የላከው

ዮሐ 316 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።

የፍጥረትም

ሮሜ 821 ተስፋውም ፍጥረት ራሱ ደግሞ ከጥፋት ባርነት ነፃነት ወጥቶ ለእግዚአብሔር ልጆች ወደሚሆን ክብር ነፃነት እንዲደርስ ነው።

በበጎ ስጦው ለሚያምን ሁሉ

ዮሐ 112 ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

እግዚአብሔር ወልድ

እግዚአብሔር ወልድን በተመለከተ የኤኤምሲ ዶክትሪናል መግለጫ እንደሚከተለው ይነበባል
ክፍል


2
እግዚአብሄር ወልድ እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሄር መንፈስ በተጸነሰ እና ከአይሁዳዊት ድንግል፣ ከድንግል ማርያም በተወለደ ለእስራኤል ተስፋ ሆኖ በተሰጠ መሲህ በናዝሬቱ ኢየሱስ  አካል ስጋ ሆኖ እንደመጣ እናምናለን፡፡ በፍጹም አምላክነቱ፣ በፍጹም ሰውነቱ፣ በሀጢአት አልባ ህይወቱ እና በተአምራቱ እናምናለን፡፡ መሲሁ ኢየሱስ በስጋው ከሙታን እደተነሳ፣ ወደ ሰማይ እንዳረገ፣ በአብ ቀኝ ተቀምጦ ለአማኞች እንደሚማልድ እናምናለን፡፡ በምድር ላይ የሺ አመት መንግስቱን ሊመሰርት ዳግም  በክብር ይመጣል፡፡ (ኢሳ 714 967 ኤር 2356 ሚክያስ 52 ሉቃስ 126-79 ዮሐ 11 214-18)፡፡

በእዚህ  ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን ክሌይም ለማረጋገጥ  ወደ ቅዱሳት መጻህፍት እንመልከት፡፡ በተቻለ መጠን ከዕብራይስጥ ቅዱሳት መጻህፍት ከታናክ ማረጋገጫዎቻችንን እናመጣለን፡፡

I.የአረፍተ ነገር 1 መግለጫ

እግዚአብሄር ወልድ

ታናክ እግዚአብሔር ወልድን ያውጃልን? ኢሳ 96 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።

ታላቁ ነብይ ኢሳይያስ በስጋ የተወለደውን ታላቅ አምላክና ዘላለማዊ አባት (ወይም ለዘላለም የሚኖር አባት) ብሎ ለማወጅ ይደፍራልን ወይስ እንደዛ አይደለም?  እንደዛ እንዳልሆነ ግልጽ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አንድ ሰውን እግዚአብሄር ወልድ ብሎ ማወጁ ግልጽ ነው፡፡ ከወልድ መጠሪያዎችም ደግሞ መንግስቱ በትከሻው ላይ እንደሆነና ይህ እግዚአብሄር ወልድ መሲህም መሆኑ  ግልጽ ነው፡፡

ስጋ እንደሆነ እናምናለን

ሆነ የሚለው እግዚአብሄር ወልድ ስጋዊ ልደቱን የሚቀድም እንደሆነ ያመለክታል፡፡ ቅዱሳት መጻህፍት ይህን ይደግፋሉን?

መዝ 26-9 እኔ ግን ንጉሤን ሾምሁ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ። ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ። ለምነኝ፥ አሕዛብን ለርስትህ የምድርንም ዳርቻ ለግዛትህ እሰጥሃለሁ። በብረት በትር ትጠብቃቸዋለህ፥ እንደ ሸክላ ሠሪ ዕቃዎች ትቀጠቅጣቸዋለህ።


ይህ
አውደ ምንባብ መሲሃዊ እንደሆነና በወልድ አዋጅ ተብሎ እንደተጠራም ግልጽ ነው፡፡  አዋጁ በጌታ አንተ ልጄ ነህ  የሚል አዋጅን ይዟል፡፡ በዚህ አዋጅ እግዚአብሄር አብ የኢሳይያስ 96  መሲሃዊው ወልድ   ልጄ ነህ ብሎ ይጠራዋል፡፡ ስለዚህ መሲሁ ወልድ  የእግዚአብሄር ልጅ እንደሆነም እንመለከታለን፡፡ ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ካለፈው ዘላለም ጀምሮ ነው እንዲሁም ካለፈው ዘላለለም ጀምሮ ነው  እግዚአብሔር አብ ከእግዚአብሔ ወልድ ጋር የተነጋገረው፡፡ ስለዚህ መሲሁ ወልድ  ስጋዊ ውልደቱን እንደሚቀድም ግልጽ ነው፡፡

በርግጥ የሹዋ ለኒቆዲሞስ ባደረገው በዚህ አዋጅ ቅድመ ህላዌውን ያመለክታል፡፡ ዮሐ 313 ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።  ከሰማይ ከወረደ ከስጋዊ ውልደቱ አስቀድሞ አለ ማለት ነው፡፡

በማጠቃለል ወደፊት መሄድ
 

እግዚአብሄር ወልድ

ለእስራኤል ተስፋ ሆኖ በተሰጠ መሲህ

በናዝሬቱ ኢየሱስ  አካል ስጋ መሆን

ከእግዚአብሄር መንፈስ እንደተጸነሰ እና

ከአይሁዳዊት  ድንግል፣ ከድንግል

ማርያም እንደተወለደ እናምናለን፡፡

በዚህ ክፍል ውስጥ ገና አድሬስ ያልተደረጉ አራቱ ዋና ዋና ክሌይሞች  ወልድ ስጋ ሆነ የሚሉ ናቸው . . .

ለእስራኤል ተስፋ በተገባው መሲህ

በናዝሬቱ ኢየሱስ  አካል ስጋ መሆን

ከእግዚአብሄር መንፈስ እንደተጸነሰ እና

ከአይሁዳዊት  ድንግል፣ ከድንግል ማርያም እንደተወለደ

ለሌሎቹ መሠረት ለመጣል በሁለተኛው ክሌይም እጀምራሁ፡፡

ለእስራኤል ተስፋ በተገባው   መሲህ

ይህ አስገራሚ እና በዝርዝር የሰጠው የኢሳይያስ ትንቢት ከኢያሱ መወለድ 700 አመት በፊት ነበር የተጻፈው፡ ኢሳ 531-11- 11፡፡

የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል፤ መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም። የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።

ደግመን አንድ ጊዜ፣ ነገር ግን ከትንሽ ሐቲት ጋር እንመልከተው፡ ኢሳ 531-11

1.      የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል?  በርግጥ ብዙ አይሁድ  እስከዛሬ ድረስ ይህን ሪፖርት አላመኑም ግን በመጽሐፍ ቅዱሳዊ  አመክንዮዎች  አይደለም

2.      እርሱ (መሲሁ) በፊቱ (በእግዚአብሔር አባቱ ፊት ) እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል ( ይህ ከዛፍ ስታምፕ እንደሚወጣ ትንሽ ሹት ነው፡፡ ዮሽዋ ከዳዊት ንጉሳዊ ዘር ነበር ነገር ግን በሮማን ግዛት ከተጨቆነ ህዝብ፣ ከደሀ ቤተሰብ ውስጥ ነበር፡፡  መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።

3.      የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። የራሱ የአይሁድ ህዝቦች በመሪዎቻቸው  ተነሳስተው አስከመጨረሻው አልተቀበሉትም፡፡

4.      በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።

5.      እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

አዲስ ኪዳን የኢየሱስን መገረፍ እና መቁሰል ይናገራል፡ (ጲላጦስ) ኢየሱስን ግን ገርፎ ሊሰቀል አሳልፎ ሰጠማቴ 2726

ይህ የኢሳያስ ክፍል እንደሚያደርገው ሁሉ የምትክነት መከራውንና ለሀጢአት መሞቱን በግልጽ ያውጃል፡፡ 2 ቆሮ 521 እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን  እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

6.      እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።

 

7.      ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።

 

የሮማው ገዢ ጲላጦስ ኢየሱስን ሲጠይቀው ስንት ያህል እንዲመሰክሩብህ አትሰማምን? አለው። ገዢውም እጅግ እስኪደነቅ ድረስ አንዲት ቃል ስንኳ አልመለሰለትም።

 

ማቴ 2713-14

 

8.      በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?

 

9.      ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ -  የእብራውያን ምሁራን ኬይል እና ዴሊትች በተሸለ መንገድ እንደዚህ ሊተረጎም እንደሚችል ይናገራሉ፡  መቃብሩ ከሀጢአተኞች  ጋር እንዲሆን ሰጡት -  ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤   ማቴ 1543-46 አንድ የኢየሱስ ባለጸጋ  ደቀመዝሙር የአርማቲያው ዮሴፍ በራሱ መቃብር እንደቀበረው ይናገራል - ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር።   (2 ቆሮ 521 ሀጢአትን አላወቀም፡፡”)

 

10.  . እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት  አድርጎ እንዲሰጥ

 

ይህ የዘሌዋውያን 1711 ፍጻሜ ነው፡ የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።

 

10.  እርሱ (መሲሁ)  ዘሩን  (መንፈሳዊ ልጆቹን) ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል (ረጅም አድሜ ይኖራል) የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።

 

11.  ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ እንዴት ነው መሲሁ ሞቶ ተቀብሮ እና ወደፊት ደቀመዛርቱን የተራዘመ ሀይወት ሲኖሩና የጌን ስራ ሲያሳኩ  የሚያየው; ሊሆን የሚች አንድ መልስ ብቻ ነው ያለው፡ ትንሳኤ፡፡ ኃጢአታቸውን ይሸከማል።  

 

አሁን አንደኛውን፣ሶተኛውን እና አራተኛውን ክሌይም አድሬስ ለማድረግ

እግዚአብሄር ወልድ

በናዝሬቱ ኢየሱስ  አካል ስጋ እንደሆነ

ከእግዚአብሄር መንፈስ እንደተጸነሰ እና

ከአይሁዳዊት  ድንግል፣ ከድንግል ማርያም

እንደተወለደ እናምናለን፡፡

ይህንን ክሌይም የሚያረጋግጡ ተከታታይ ቅዱሳት መጻህፍትን አቀርባለሁ፡ ሉቃስ 130-35፡፡

30 መልአኩም እንዲህ አላት፦ ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ።31 እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። 32 እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ 33 በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘለላም ይነግሣል፥ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም። 34 ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። 35 መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

ቁጥር 31 እግዚአብሔር ወልድ በኢየሱስ አካል እንደተወለደ ያረጋግጣል፡፡ ቁጥር 35 በእግዚአብሄር መንፈስ እንደተጸነሰ፤ 30-31 ከማርያም እንደሚወለድ ያሳያል፡፡

በአባቱ በዳዊት በሚለው ሀረግ ውስጥ ማርያም አይሁዳዊት እንደሆነች በቁ 32 ላይ ተገልጾአል ፡፡ ቁጥር 32 እና 33 ይህ ወልድ መሲህ አንደሆነም ግልጽ ያደርጋሉ፡፡

ማርያም ድንግል እንደሆነች ኢየሱስም ከናዝሬት እንደሆኑ ማሳየት ይኖርብናል፡፡

ምንም እንኳን ማርያም በታናክ ውስጥ ስሟ ባይገለጽም የድንግል መውለድ ግን ተተንብዮአል፡ ኢሳ 714 ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።

በክፍሉ መሠረት የልጁ መወለድ ምልክት ይሆናል፣ ገላጭ ተአምር፣ ተአምር ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች የሚል ነው፡፡ በተጨማሪም አማኙኤል ማለትም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር - ሁለትዮሽ- መለኮታዊና ሰባዊ ማንነቱን ገላጭ ነው፡፡

ከናዝሬት

ማቴ 223 በነቢያት፦ ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።

 

ጥቅሱ ስለማርያም ባል ስለ ዮሴፍ ኢየሱስን ወደናዝሬት ማምጣት ይናገራል፡ ናዝራዊ ተብሎ ይጠራል የሚለው በታናክ ውስጥ አይገኝም ነገር ግን በርግጥም በህይወቱ የተፈጸመውን በታናክ ውስጥ የተተነበየውን የኢየሱስን የህይወት ገጽታ ያጠቃልላል፡፡ (ሳሜሽን ተብሎ የሚጠራው የሆነ የታናክን ክፍል የማጠቃለል ዘዴ በሌላ የአዲስ ኪዳን ክፍል  ውስጥም ይገኛል፡፡)

በኢየሱስ ዘመን የናዝሬት ነዋሪዎች በሌሎች አይሁዶች ይናቁ ነበር ኢየሱስም እንደዛው  ተንቋል ምክንያቱም ከናዝሬት ስለነበር፡፡ ይበልጥ ግን  እንዲፈረድበት ወደ አህዛብ ባመጡት በገዛ ወገኖቹ ተንቆ ነበር ፡፡ ኢሳያስ እንደሚናገረው፡ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።  ኢሳ 533፡፡ በርግጥም ኢየሱስ በሁለት አቅጣጫ ናዝራዊ ነበር፡፡ በመጀመሪያ ናዝሬት ስላደገ በሁለተኛ ደረጃ መሲህ ነኝ  በማለቱ በሰዎች ስተናቀ፡፡

II. የሁለተኛው አርፍተ ነገር መግለጫ

ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው መሆኑን እናምናለን

መሲሁ በአንድ ጊዜ መለኮትና ሰው መሆኑ ከድንግል መወለዱን በሚተነብየው በኢሳ 714 ውስጥ አንድ ሆኗል ሆኗል፡፡

 

መላኩ ማርያምን እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ ብሎ በሚነግራት በሉቃስ 131 ውስጥም ልክ እንደቀን ግልጽ ተደርጓል፡፡

በቁ. 34 ውስጥ፡

ማርያምም መልአኩን፦ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል? አለችው። መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

በድንግልና የተወለደው ሰው የሆነው ኢየሱስም ቅዱሱ እና የእግዚአብሔር ልጅ ተብሎ ተጠርቷል፡፡

ኢየሱስም ተመሳሳይ ነገር ተናግሯል፡፡ በምድራዊ አካሉ ቆሞ ከሸንጎው አባል ከመመምህር ኒቆዲሞስ ጋር ሲነጋገር፣  ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው ብሎ ተናገረ (ዮሐ 313) በሰማይ ያለው የሰው ልጅ፡፡  በአንድ ጊዜ የሰው ልጅ  በምድርም በሰማይም ነበር፤ ፍጹም ሰውና ፍጹም አምላክ፡፡

ሀጢአት አልባ ህይወቱ

ትንቢት የተነገረው የመሲሁ ህይወት ሀጢአት አልባነት በታናክ ውስጥ የሚገኝ  ነው፡፡ እንደተመለከትነው  ኢሳ 714 ወደፊት ድንግል አማኤል፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር  የተባለ ልጅ  ስለ መውለዷ ይናገራል፡፡  ኢሳ 96 ደግሞ ልጁ አምላክነቱን የሚናገሩ ስሞች እንደሚሰጡት ይናገራል፡ ታላቅ አምላክ እና የዘላለም አባት (ወይም ዘላለማዊ አባት)፡፡

እግዚአብሔር ሀጢአት አልባ መሆኑ ምንም መረጋገጥ አያስፈልገውም፤ ግን ኢየሱስ ስለተባለው ሰውስ?  ሉቃስ 135 እንመለክት እንደገና፡ መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፦ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፥ የልዑልም ኃይል ይጸልልሻል ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።

የማርያም ስጋና ደም ህጻን ነው ቅዱሱ ተብሎ የተጠራው ማለት ገና በፍጥረቱ ፍጹም ሀጢአት አልባ ነው ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ በሀጢአት ማንነት አልተወለደም ፍጹም በሆነ ቅዱስ ማንነት እንጂ፡፡ ይህም የተከናወነው በማርያም ላይ በእግዚአብር መንፈስ ቅዱስ መጸለል እውነተኛ አደራረግ ነው፡፡ ኢየሱስ አገልግቱን በሙሉ  ሲነቅፉ የነበሩትን ጸሀፍትንና ፈሪሳውያንን  ከእናንተ ስለ ሀጢአት የሚወቅስኝ ማን ነው? ይላቸዋል (ዮሐ 846)፡፡

ተአምራቶቹም

ዮሐ 31  ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው።

ኢየሱስ ተአምራት ማድረጉ በታናክ ውስጥ የመሲህ ትንቢት ፍጻሜ ነው፡  ኢሳ 354

ፈሪ ልብ ላላቸው፦ እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው። 5 በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዓይን ይገለጣል የደንቆሮችም ጆሮ ይከፈታል። 6 በዚያን ጊዜ አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘልላል፥ የድዳም ምላስ ይዘምራል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ፈሳሽ ይፈልቃልና።

III. የአርፍተ ነገር ሶስት አገላለጽ

መሲሁ ኢየሱስ በስጋው ከሙታን እንደተነሳ እናምናለን

1 ቆሮ 153 እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥

እዚህ ከተጠቀሱት ቅዱሳት መጻህፍት መካከል መዝሙር 1610 አንዱ ነው ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።

መዝሙረኛው ዳዊት ስለራሱ ቅዱስህ ብሎ አያውቅም የእርሱ ሰውነትም በርግጥ በዚህ ሰኣት ከተቀበረ 3000 አመታት ሆኖታል፡፡ ስለዚህ  ዳዊት ስለራሱ ትንቢት የተናገረ አይደለም፡፡ ስለዳዊት ልጅ ስለመሲሁ እንጂ፡፡ በትክክል እንዲህ ብሏል፡ የመሲሁ አካል፣ የቅዱስህ፣ የሰውነት መበስበስን አያይም ምክንያቱም እግዚአብሔር ነፍሴን በሲኦል አይተዋትም (ሲኦል፣ ጊዜአዊ የሙታን መቆያ ነው)፡፡” “በሌላ አባባል እግዚአብሔር ያስነሳኛል ማለት ነው፡፡

ወደሰማይ አርጓል

ሐዋ ስራ 19 ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።

 ሮሜ 834 የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

መሲሁ በአብ ቀኝ መሆኑ የትንቢት ፍጻሜ ነው መዝ 1101 እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።

መዝሙረኛው ዳዊት  ጌታ እግዚአብሔር፣ ለዳዊት ጌታ . . . አለው፡፡ የዳዊት ጌታ ማን ሊሆን ይችላል; እግዚአብሄር ይህ የዳዊት ጌታ በስልጣኑ ቀኝ እንዲያደርግ በትንቢት ቢድ አርገዋል፡፡ ፀላጾቹንም ከግሩ በጻች ለማስገዛት ቃል ገብቶለታል፡፡ ከመሲሁ ሌላ እግዚአብሔር ለማን ሊናገር ይችላል?

IV. የአርፍተ ነገር 4 አገላለጽ

ዳግም ይመጣል

መሲሁ  ካረገ በኋላ ወደምድር ይመጣል የሚለው ለተናክ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ሆሴዕ 515 በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፥ ፊቴንም እስኪሹ ድረስ ሄጄ ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ በመከራቸው ጊዜ እጅግ አድርገው ፊቴን ይፈልጋሉ።

ከአውዱ መለኮዊ ሰው ለእርሱ የሐጢአት ኑዛዜ እንደሚደረግ እና እነርሱም፣ እስራኤል ፊቱን እንደሚሹ ይናገራል፡፡ ይህ መለኮታዊ ሰው ወደ ስፍራው ይኸውም ወደሰማይ ይመለሳል ከዚያም ተመልሶ ይመጣል፡፡ ራዕይ 19 11-16 ደግሞ እንደሚመጣ ይነግረናል፡፡

በክብር

ራዕይ 1911-16

11 ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፥ እነሆም አምባላይ ፈረስ፥ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፥ በጽድቅም ይፈርዳል ይዋጋልም። 12ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፥ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፥ ከእርሱም በቀር አንድ እንኳ የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ 13 በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፥ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሎአል።  14 በሰማይም ያሉት ጭፍራዎች ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በአምባላዮች ፈረሶች ተቀምጠው ይከተሉት ነበር። 15 አሕዛብንም ይመታበት ዘንድ ስለታም ሰይፍ ከአፉ ይወጣል፤ እርሱም በብረት በትር ይገዛቸዋል፤ እርሱም ሁሉን የሚገዛ የእግዚአብሔርን የብርቱ ቍጣውን ወይን መጥመቂያ ይረግጣል። 16 በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት፦ የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ የሚል ስም አለው።

. 13 የእግዚብሔር ቃል ተብሎ  በሚጠራበት በዚህ አውደ ምንባብ ውስጥ ያለው ሰው መሲሁ ኢየሱስ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ዮሐ 11 እንመልከት፡ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ . . . 14 ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን።

የቁ.1 ቃል ስጋ ሆነ በመካከላችንም አደረ፡፡  በሌላ አባባል፣ ቃሉ መለኮታዊ ቅድመ ህላዌ የነበረው፣ ሰው ሆኖ ተወለደ፡፡ ማን እንደሆነ ተመልክተናል፡ የዮሐንስ  1 መሲሁ የእግዚአብሄር ቃል እና ራእይ 1913 ኢየሱስ፡

የሺ አመት መንግስቱን  ቃል በቃል በምድር ላይ  መመስረቱ

መንግስቱ ለሚሊንየም፣ ለአንድ አመት ይቆያል፡፡ ይህ በራእይ 204 ውስጥ በግልጽ ተነግሯል፡ ከክርስቶስም ጋር ሺህ ዓመት ኖሩና ነገሡ።

የርሱ ለሆኑት የርሱ መንግስት በአስደናቂ በረከቶች ይገለጣል

እነዚህ በረከቶች በታናክ ውስጥ ትንቢት ተነግረዋል፡፡ ኢሳ 611-3 

የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። 2 የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።

*አሜን ጌታ ኢየሱስ ሆይ !*

ራእይ 2220

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

የስላሴ መግለጫው  እንዲህ በማለት ይደመድማል፡

ክፍል 3 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ

ሩሀክሀቆዴሽ (መንፈስ ቅዱስ)አካል ያለው እንደሆነ እናምናለን፡፡ የተለዩትን ሁሉንም የአምላክነት እና የሰውነት አትሪቢቶች ይዟል፡፡ ለራሱ ትኩረትን አይሰጥም ደግሞም ስመሲሁ ኢየሱስን ሊያከብርና ስለርሱ ሊመስክር ነው ለዘላለም የሚኖረው፡፡ ዛሬም መንፈስ ቅዱስ አለምን ስለሀጠኢት ስለጽድቅ፣ ስለፍርድ እየወቀሰ እንዳለ እናምናለን፡፡

ሪጄኔሬት ያደርጋል፣ አማኞቸን ለጽድቅ ህይወት ይለያል፣ ያትማል፡፡ በደህንነት ጊዜ እያንዳንዱ አማኝ  ይጠመቃል ወደመሲሁ አካል በመንፈስ ቅዱስ ይጠመቃል፡፡ በዚያው ጊዜም የመንፈስ ቅዱስ የዘላለም መኖርያ ይሆናል፡፡ ሁሉም አማኞች በመሲሁ ሙሉ ናቸው ደግሞም የትኛውም መንፈሳዊ በረከት አላቸው፡፡ በደህንነት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሉአላዊነት ለእያንዳንዱ አማኝ የመሲሁን አካል ለማነጽና ለማስታጠቅ ቢያንስ አንድ ጸጋ እንደሰጠ እናምናለን፡፡ (ነህምያ 920፤መዝሙር 1397 ዮሐ 15261613-15 ሐዋ ሥራ 54 1 ቆሮ 210111211 2 ቆሮ 1314)፡፡

የሚከተለው አባባል እንደሚያሳየው የመንፈስ ቅዱስን ሰውነት እና አምላከነት እውነታዎች መከላከል መቻል አስፈላጊ ነው፡ የተቀደሰ ስም እንቅስቃሴ ከእግዚአብሄር ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን መኖር ይቃወማል ነገር ግን እንደ እግዚአብሄር ሀይ መገለጥ ሰዋዊ ያልነ መገለጥ”  ( የተቀደሰ ስም እንቅስቃሴ፣ ጴት ኮዚያር፣ ሾፋር 2)፡፡

ሩአክሀቆዴሽ (መንፈስ ቅዱስ) ሰው/ስብዕና  እንደሆነ እናምናለን፡፡

1.    መንፈስ ቅዱስ ስብዕና  ነው

. መንፈስ ቅዱስ እውቀት አለው፡፡ ሮሜ 826 . . . እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤ ምልጃ እወቀትን ይሻል

. መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው፡፡ ኤፌ 430 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።

. መንፈስ ቅዱስ ፈቀድ አለው፡፡ ሉቃስ 226 በጌታም የተቀባውን ሳያይ ሞትን እንዳያይ በመንፈስ ቅዱስ ተረድቶ ነበር።  የሆነ ነገርን በንቃት መግለጥ የፈቃድ ድርጊት ነው፡፡

ልዩ የሆኑትን የአምላክነት እና የሰውነት መገለጫዎችም አሉት

2.    መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሄር  ነው፡፡ ሐዋ ስራ 1312 በዚያን ጊዜ አገረ ገዡ የተደረገውን ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ።
 

3.    ስለ መንፈስ ቅዱስ ሌሎች ነጥቦች

ለራሱ ትኩረትን አይሻም ሁልጊም ያለው መሲሁን ኢየሱስን ሊያብርና ስለርሱ ሊመሰክር ነው” 

ዮሐ 1613-14 ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል። እርሱ ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶ ይነግራችኋልና።

ዛሬም መንፈስ ቅዱስ አለምን ስለሀጠኢት ስለጽድቅ፣ ስለፍርድ እየወቀሰ እንዳለ እናምናለን፡፡

ዮሐ 168 እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል፤

ሪጄኔሬት ያደርጋል

ዮሐ 36-7 ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው፡፡ ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ።

ያትማል

ኤፌ 430 ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።

አማኞችን ለተቀደሰ ህይወት ይለያል

ገላ 516 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።

በደህንት ጊዜ እያንዳንዱ አማኝ ወደ መሲሁ አካ በመንፈስ ይጠመቃል

1 ቆሮ 1213 አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና።

ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።

በዚያው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ለዘላለም በርሱ ውስጥ ይኖራል

ዮሐ 1416-17 እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤ እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።

በደህንነት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በሉአላዊነት ለእያንዳንዱ አማኝ የመሲሁን አካል ለማነጽና ለማስታጠቅ ቢያንስ አንድ ጸጋ እንደሰጠ እናምናለን

1 ቆሮ 127-8 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል። ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥

የሶስቱም አካሎች አኩልነት

አብ፣ ወልድን እና መንፈስ ቅዱስን አጥንተናል፡፡ አንድ ተጨማሪ የእኛ ክይም መታየት አለበት፤ የሶቱ እልነት

እግዚአብር የማይገደብ እና ፍጹም፣ በሶስት  እኩል አካላት የሚኖር ነው፡፡

ከምን አንጻር ነው ስቱ እኩል የሆኑት; ሁሉም በሰውነት እና በአምላክነት መገለጫዎች ኢንዶውድ ናቸው፡፡ ማቴ 819 አንድ ጻፊም ቀርቦ፦ መምህር ሆይ፥ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው።

እግዚአብሄር ስላሴ

ሁለተኛው የኤኤምሲ ዶክትሪናል መግለጫ  ነጥብ በአይሁድ አለመቀፍ ክሬዶ፣ እግዚአብሔር ራሱን አንድ ብሎ በሚያውጅበት በሼማ ፊት የሚያልፍ የሚመስለው፣በስላሴ፣ በሶስቱ ስላሴ ማመን፣ ያውጃል፡፡ ስለዚህ ቅዱሳት መጽሐፍትን በጥንቃቄ እንመልከት፡፡

ሼማ

ዘዳ 64 እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው፡፡

ባለፈው ጥናታችን በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ሶስት የመለኮትና የስብእና ማንነትን ያያዙ ቅዱሳት መጽሐፍትም እግዚአብሄር አብ፣ የሹዋ ወልድ እና ሩአክሀቆዴሽ መንፈስ ቅዱስ ብሎ የሚያውቃቸውን ተምረናል፡፡ የእግዚአብሔርን ሶስትነት የሚመለከት ከባድ ሊፊቲንግ ተከናውኗል የእግዚአብሄርን ሶስትነት ለመረዳት ቁልፉን የያዘው፣ ሼማ ራሱ ቸል መባል የሌለበት   ግን ገና ልብ መባል ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡

የኤኤምሲ የስላሴ አነጋገር መግለጫ

ስላሴ

እግዚአብር አንድ እንደሆነ ነገር ግን ራሱን በሶስት በተለዩ እና በተለያዩ ሰዎች እንደገለጸ እናምናለን፡፡ ስለዚህ እግዚአብሄር ስላሴ/ሶስት እንደሆነ እናምናለን፡ አብ ፣ወልድና መንፈስ ቅዱስ፡፡ እግዚአብሄር የሁሉም ነገሮች ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱ የማይወሰን እና ፍጹም፣ ለዘላላም በሶስት እኩል ሰውነቶች የሚኖር፣ እያንዳንዱ ሶስቱ የአምላክነትን ማንነት የያዙ የሰውነትንም ጠባዮች እንዲሁ የያዙ፡፡ በሁሉም ስፍራ ይገኛል፣ ሁሉን ቻይና ሁሉን አዋቂ ነው፡፡ (ዘዳ 64 ኢሳ 4816 ማቴ 2819 ዮሐ 627 ሐዋ ስራ 534 2 ቆሮ 1314 እብ 18)

I.             ሶስት የተለዩ መለኮታዊ ሰዎች

ሶስት መለኮታዊ ሰዎች/አካላት መኖራቸው ተመስርቷል፤ ነገር ግን እርስ በርስ የተለያዩ መሆናቸው በኢሳ 4812-16 ውስጥ በግልጽ መታየት ይችላል፡፡

12 ያዕቆብ ሆይ፥ የጠራሁህም እስራኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ነኝ፤ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ።  16 ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

. 12 እንደመጀመሪያና መጨረሻ የቁጥር 16  እኔን ያሳያል፣ የዘላለም መገለጫን የሚያውጅ የመለኮት መጠሪያ (ከዘላለም ሃላፊ አስከ ዘላላም ወደፊት) በዮሐ ራእይ 1 4-8 ለመሲሁ ኢየሱስ ጥቅም ላይ የዋለ መጠሪያ፡፡ ይህንን በአእምሮአቸን አድርገን፣ 16 እንመልከት፡ . . . አሁንም ጌታ እግዚአብሔር (እግዚአብሄር አብ)  እና መንፈሱ  (መንፈስ ቅዱስ) ልከውኛል (መሲሁ ኢየሱስ)

በአንድ ቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ሶስት  የተለያዩ መለኮታዊ አካላት፡

በሉቃስ 322 መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

አንድ አካል፡ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ሌላ አካል፡ እርሱ፣ ልጄ፡፡  ግን  ሌላ፡  ተናጋሪው ከሰማይ፣ አብ፡፡ ሶስት የተለያዩ  መለኮታዊ አካላት፡፡

 

II.            ሶስት ብቻ ናቸው ?

በቅዱሳት መጻህፍት ውስጥ ለመለኮት ልዩ የሆኑ መገለጫዎችን እንደዘላለማዊነት በሁሉም ስፍራ መኖርን ሁሉን አዋቂነትን እና ሁሉን ቻይነትን ያዙ ሦስት ብቻ አሉ፡

 

III.          ያሉት ሶስት መለኮታዊ አካላት ብቻ ከሆኑ  ሼማ ያህዌ አንድ አምላክ እንደሆነ ለምን ያናገራል?

በታናክ (በእብራውያን መጽሐፍ ) ውስጥ አሃዱ/አንድ ጥቅም ላይ እንደዋለ እንመልከት ከዚያም እንዴት በሼማ ውሰጥ ጥቅም ላይ እንደዋለ እንመለከታን፡፡

በታናክ በሌላ ስፍራ ውስጥ አሀዱ/ አንድ እንዴት ነው ጥቅም ላይ የዋለው?

 

1.    ያኬድ- ሁልጊዜም ፍጹም አንድ ማለት የሆነው፣ በሼማ ውስጥ ጥቅም ላይ አልዋለም

ዶክተር ፍሩቸንቦም እንዲህ ይጽፋል፣

ሌላ የዕብራይስጥ ቃል አለ ፍጹም አንድ ማለት የሆነ፣ ያኬድ፡፡   ይስሀቅ ብቸኛ የአብርሀም ልጅ እንደሆነ አጽኖት በሚሰጠው በዘፍ 222 ላይ ጥቅም ላይ ውሏል ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን ፍጹም አንድነት አጽኖት ማድረግ ቢፈልግ ኖሮ (በሼማ ውስጥ ) ያኬድ የሚለውን ቃል ይጠቀም ነበር፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሄር አንድነት ያንን ቃል አልተጠቀመም፡፡ ስለዚህ ዘዳ 64 የእግዚአብሄር አብ ብዙህነትን የሚደግፍ ነው ደግሞም ይህን የአንዱን እግዚአበብሔር ብዙህነት ጥምረት ያስተምራል፡፡

(ፍሩችቴንም፣ ዶክተር አርኖልድ . ሬዲዮ ማስክሪፕት . 50 ስላሴ፡፡  ሳን አንቶንዮ ኤርየል ሚኒስትሪስ ፕሬስ ገጽ 10-11)

2.    ያህዌ ሁለት እንጂ አንድ ሰው ብቻ የማያመለክትበት  በታናክ ውስጥ 2 ምሳሌዎች አሉ

እነርሱም ዘፍ 1924 እና ዘካርያስ 28-9 ናቸው፡፡ ከሁሉም ግልጽ የሆነው ክፍል የኋለኛው ነው፡

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ከክብሩ በኋላ ወደ በዘበዙአችሁ አሕዛብ ልኮኛል፤ የሚነካችሁ የዓይኑን ብሌን የሚነካ ነውና። እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።

ዘካርያስ 28-9

ሁለቱም ላኪውና የሚላከው ጆሆቫ ተብለው ይጠራሉ- በቁጥር ሁለት እንጂ አንድ አይደሉም፡፡ ያኬድ ጆሆቫ ተብለው የሚጠሩትን የሁለቱን ሰዎች ውህድ አንድነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ መዋል አይችልም ኤካድ ግን ይችላል፡፡

3.    በስላሴ ውስጥ ሶስት መለኮታዊ አካላት አሉ፡፡ ያለፈው ጥናታችን ይህንን ያሳያል ከማረጋገጫ አውድማ ባለፈ፡፡

4.    ማቴ 2819 እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስምሯቸው

ሶስት አካላት፣ አንድ ስም፡፡ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን  በሶስቱ መለኮዊ አካለት ጥምረት/ አንድነት አመለካከት እንዲያጠምቁ ተልዕኮ ሰጣቸው፡፡

5.    ማጠቃለያ

1.    ያኬድ- ኤካድ አይደለም፣ በዘፍ 222 ጥቅም ላይ ውሏል የአብርሃምን ብቸኛ ልዩ ልጅ የይስሀቅን ፍጹምነት አጽኖት ለመስጠት፡፡

2.    በታናክ ውስጥ የአካላት ብዝሃት እንደ ያህዌ ተመላክቷል፡፡

3.    ቅዱሳት መጻህፍት ሶስት አካላትን እንደመኮት ያሳያል

4.    አንኢኪዩቮካሊ ፍጹም አንድነትን ለማሳየት በሼማ ውስጥ ሙሴ ያኬድን መጠቀም ይችል ነበር  ነገር ግን አልተጠቀመም፡፡ ኤካድን ነው የተጠቀመው፡፡

5.    አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ስም አላቸው፡፡ በእነዚህ ነገሮች አመለካከት፣ በሼማ ውስጥ ያህዌን ያኬድ ብሎ መጥራት አሳሳች ነው የሚሆነው፣ በታናክም ውስጥ ቢሆን በእግዚአብሄር አብ ውስጥ የአካላት ብዝሃት መኖራቸው ግልጽ ስለሆነ፡፡ አንድ ብቻ ትክክለኛ ማጠቃለያ ይቀራል፡ ኤካድ በሼማ ውስጥ ለያህዌ ውህድ ጥምረትን ይገልጻል፤ ያንን  ውህድ ጥምረት የሚፈጥሩ ሶስት መለኮታዊ አካላት ስላሉ፣ ትራይዩኒቲ /ሶስት አንዶች ብለን እንጠራቸዋለን

 

IV.           ትሪኒቲ ሳይሆን ለምን ሶስት አንዶች?

የእግዚአብሔርን ሶስት  አካላት ጥምረት ለመግለጽ ትሪኒቲ በጣም  ተቀባይነት ያለው የእንግሊዘኛ ቃል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ትራይ በሚለው ቃል  አንዳንዶች የቃሉ ድምጽ በግልጽ ሶስትነትን እንደሚገልጽ ተመልክተዋል ነገር ግን በግልጽ አንድነትን አያሳይም፡፡ እውነታው፣ የቃሉ አመጣጥ  የአንድነት ጽንሰ ሀሳብ ፍጹም አለመኖርን ያመለክታል! ዌብስተር የትሪኒቲን ቃል አመጣጥ እንዲህ ያቀርባል፡ ከሌት ላቲን ትሪኒታት፣ ትሪኒታስ ሶስት እጥፍ የመሆንን ሀኔታ፣ ከላቲን ትሪነስ - ሶስት እጥፍ

በሌላ በኩል ሁለቱም ድምጹም የትሪኒቲም ቃል አመጣጥ የእግዚአብሄርን ሶስትነት እና አንድነት ፍጹም ሚዛንንም  ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ኤኤምሲ ትራይ ዩኒቲ የሚለውን ቃል ይጠቀማል፡፡

V.           አንድ ማንነት፡ የተጣመረ ውህደት መሰረት

የሶስቱ መለኮታዊ አካላት ጥምር አንድነት በእነርሱነታቸው ውስጥ አንድ ኢሴንስ ይዟል፡፡ የኢሴንስን ትርጉም በተመለከተ ዶክትር ሪሪ እንዲህ ይላል፣ ሰብስታንስ የሚለው ቃል በጣም ቁሳዊ ሊሆን ይችላል፡፡ አንዳንዶች ኢሴንስ የሚለውን ቃል ለመጠቀም ይመርጣሉ፡፡ “ (ሪሪ፣ ዶክተር ቻርለስ ካልድዌል፡፡ ቤሲክ ቲዎሎጂ፡፡ ዊተን፡ ቪክተር ቡክስ፣ 1986፡፡ ገጽ 53)፡፡ ለተጨማሪ ማብራሪያ በዶክተር ቻፈር የተሰጠውን ንግግር እሰጣለሁ፡ እያንዳንዱን አካል የሚለይ የተለየ አስተሳሰብ/ኮንሸስነስ አለ ያለጥርጥር፡፡ ቢሆንም ግን መገለጫዎችን እና ማንነትን በጋራ መያዝ አለ፡፡ (አጽኖት የእኔ)፡፡ (ቻፈር ዶክተር ሉዊስ ስፔሪ፡፡ ስልታዊ ሥነመለኮት፣  ቅጽ 1 ገጽ 273)

. አብና ወልድ አንድ ኢሴንስ

በዮሐ 1030 ኢየሱስ እኔና አብ አንድ ነን አለ፡፡

ይህን በተመለከተ ዶክተር ፍሩችተንቦም እንዲህ ይላል፡ ይህ ጥቅስ አብና ወልድ በኢሴንስ አንድ እንደሆኑ ያስተምራል፣ የመለኮትነትን የራሱን ኢሴንስ” (ገጽ 19)፡፡

ኢየሱስም አለው፦ አንተ ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቶአል፤ እንዴትስ አንተ፦ አብን አሳየን ትላለህ?እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል። 

ዮሐ 149-10

እኔ በአብ አብም በእኔ በሚለው ላይ አንዳንድ ማብራሪያዎች፡

“ . . . የማንነት አንድነት አገላለጽ” ( ጆን ጊልስ የመጽሐፍ ቅዱስ ኤክስፖዚሽን)

“  . . . በጣም ቅርብ የሆነ አንድነትን ያመለክታል” (የአልበርት ባርነስ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስታወሻ)

በጣም በቅርበት አንድ ነን፡ . . . ” (የአዳም ክላርክ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ)

አብና ወልድ አንድ ኢሴንስ ናቸው፡፡ ለዚህ ነው ኢየሱስ አብን ያንጸባርቅ የነበረው ደግሞም እኔን ያየ አብን አይቷል ማለትም የቻለው (ዮሐ 149)፡፡

. ወልድና መንፈስ ቅዱስ፡ አንድ ኢሴንስ

ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ፡፡ ብሉይ ኪዳን ሲነበብ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና። ነገር ግን እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ጊዜ ሁሉ መጋረጃ በልባቸው ይኖራል፤ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል። ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።

2 ቆሮ 314-17

እስራኤል ወደ ጌታ ሲመለስ መጋረጃው ይወሰዳል፡፡ ቁጥር 14 ጌታ የሚለውን እንደ ኢየሱስ ይመለከተዋል፡፡ ቁጥር 17 ጌታ መንፈስ እንደሆነ ይናገራል  . . .የጌታ መንፈስ . . .  በዚህ ምልከታ፣ ዶክተር ቻርለስ  ሪሪ . 17  “ክርስቶስ እና መንፈስ ቅዱስ በኢሴንስ አንድ እንደሆኑ ጠንካራ መግለጫ እንደሆነ ይናገራል (ሪሪ፣ ዶክተር ቻርለስ ካልድዌል፡፡ የሪሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ፡፡ ቺካጎ፡ ሙዲ፣ 1978፡፡)

. መንፈስ ቅዱስ እና አብ፤ አንድ ኢሴንስ

ሮሜ 827 ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና።  

አብና መንፈስ ቅዱስ  በጣም አንድ ናቸው  ሁልጊዜ መንፈስ ቅዱስ እንደ እግዚአብሄር ፈቃድ ይጸልያል፣ በፍጹም ትንሽም እንኳን ሳያመነታ፡፡  ሁለቱ በአንድ ሃሳብ ካልሆኑ በቀር መንፈስ ቅዱስም ይህን ማድረግ አይችልም፡፡ አንድ ኤሴንስ ነው ያላቸው፡፡

. ወልድ፡ አንድ ኢሴንስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር

ቆላ 29 ስለ ኢየሱስ እንዲህ ይላል፡ በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፡፡

የአብ ሙላት በአብና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ይኖራል ሁለቱም አንድ ኢሴንስ ናቸው፡፡

 

የአብ ሙላት በኢየሱስም ውስጥ ያኖራል፡፡ ሙላት ማለት አጠቃላይ እንደሆነ ሁሉ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ግድ አንድ ኢሴንስ መሆን አለበት፡፡

. አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስ፡ አንድ ኢሴንስ

አብና ወልድ አንድ ኢሴንስ ናቸው፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ አንድ ኢሴንስ ናቸው፤ ወልድና መንስ ቅዱስ አንድ ኢሴንስ ናቸው ኢየሱስም ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ኢሴንስ ነው፡፡ በግልጽ፣ አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ በኢሴንስ አንድ ናቸው፡፡

VI.          ሶስቱም አካላት በኢሴንስ አንድ ስለሆኑ አንድ አካል አለ ማለት እንችላለንን?

ዶክተር ጌስለር እና ሮናልድ ብሩክስ፡ የስላሴ ዶክትሪን፣ እግዚአብሄር ሶስት  አካላት አሉት ግን አንድ አካል ነው ብለን ከተረዳነው እርስ በርስ የሚቃረን ነው ይላሉ (ጌስለር፣ ዶክተር ኖርማን ኤል. እና ብሩክስ፣ ሮናልድ፣ ግራንድ ራፒድስ፡ ቤከር ቡክ ሀውስ፡፡ ገጽ 19-20)፡፡

አንድ አካል አይደሉም ምንም እንኳን በኢሴንስ አንድ ቢሆኑም፡፡ ቢሴንስ ንድ የሆኑ ሶስት የተለያዩ አካለት ናቸው ፡፡

VII.        ሶስቱም መለኮታዊ አካላት ሶስት የተለያዪ ወይም የተለዩ አምላኮች ናቸው?

እግዚአብሔር ሶስት የተለዩ አካላትን እንደያዘ ተመልክተናል ነገር ግን በኢሴንስ አንድ እንደሆኑም አይተናል፡፡ ስለዚህ መልሱ አይደለም ነው፡፡ አንድ ኢሴንስ ስለሆኑ ሶስቱ መለኮታዊ አካላት የተለዩ ወይም የተለያዩ አምላኮች ሣይሆኑ አንድ አምላክ ናቸው፡፡ በመሰረታዊ ኢሴንሳቸውም የማይለያዩ ናቸው፡፡

ዶክተር ቻፈር እንዲህ ይላል፡

ያለጥርጥር እያንዳንዱን አካል የሚለይ  የተለያየ ኮንሸስነስ  አለ ቢሆንም መገለጫዎችን  እና ማንነትን በጥምረት መያዝ ግን አለ  . . . (ስላሴ) አንድ ማንነት በአንድ በኩል ነጠላ በሌላ ደግሞ ብዙ ሊሆን እንደሚችል እንጂ ከዚያ በላይ ምንም አያረጋግጥም፡፡  በተፈጥሮ የእንዲህ ያሉ እውነታዎች የተለያዩ ምሳሌዎች ተዋውቀው ሊሆን ይችላል፡፡

በሰው ህገ መንግስት ውስጥ የጥምረት እና የብዝሃነት መጋጠሚያ አለ፡፡ ቁሳዊ ያልሆኑና ቁሳዊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች አንድ ግለሰብን  ለመፍጠር ይዋሃዳሉ  . . . የሰው ዘርን በተመለከተ አንድ አስተሳሰብ አለ ሁለት መልክ ሰብሲስተንስ ያለው፤ አምላክነትን በተመለከተ ሶስት ኮንሸስነስ ግን አንድ ማንነት አለ . . . ስላሴ የተለያየ ህልውና የሌላቸው ሶስት የተወሃዱ ሰዎችን የያዘ ነው  ፡፡ ስለዚህ  አንዱን አምላክ ለመፍጠር ሙሉ በሙሉ የተዋሃዱ ናቸው ፡፡ (ቼፈር፣ 273-276)፡፡

የተለያዩ ሶት አካላት ናቸው ነገር ግን በመለኮት ኢሴንስ አንድ እስከሆኑ ድረስ ሶስት አምላክ ናቸው ብለን መናገር አንችልም፣ በኣካል ሶስት ናቸው ነገር ግን በኢሴንስ አንድ ስለሆኑ አንድ አምላክ ናቸው፡፡

VIII.       ስላሴን አንድ የማድረግ ኢሴንስ ተፈጥሮ ምንድን ነው?

ይህንን የስላሴን አካላት እያንዳንዱን ኢሴንስ ለማወቅ በመፈለግ እንጀምር፡፡

. የእግዚአብሄር አብ ኢሴንስ

ኢየሱስ እግዚአብሄር መንፈስ ነው አለ (ዮሐ 424)፡፡ የእግዚአብሄር አብ ኢሴንስ መለኮታዊ መንፈስ ነው፡፡

. የእግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ኢሴንስ

እንደ እንግሊዘኛው፣ በእብራይስጡ መንፈስ ስም ነው ቅዱስ ደግሞ ገላጭ ቅጽል ነው፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኢሴንስ መለኮታዊ መንፈስ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

. የእግዚአብሔር ወልድ ኢሴንስ

በቀጥታ ወልድ መለኮታዊ መንፈስ እንደሆነ የሚናገር መጽሐፍ የለም ነገር ግን ሁለት አውዶች ጉዳዩን ግልጽ ያደርጋሉ፡

አንደኛው  ጌታ መንፈስ ነው የሚል አገላለጽ የያዘ 2 ቆሮ 314-17 ነው፡፡ ከላይ እንደ ተመለከተው ዶክተር ሪሪ ይህ ክርስቶስ  እና መንፈስ ቅዱስ በኢሴንስ አንድ እንደሆኑ ጠንካራ አገላለጽ ነው  ይላል (ሪሪ ስተዲ ባይብል)፡፡ የመንፈስ ቅዱስ ኢሴንስ ከሆነ፣ የወልድም ኢሴንስ መለኮታዊ መንፈስ ነው፡፡ ሌላኛው ቆላ 29 ነው፡

  በእርሱ የመለኮት ሙላት ሁሉ በሰውነት ተገልጦ ይኖራልና፤

አብ መንፈስ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ከሆነ እግዚአብሔር  ማለትም በወልድ የሚኖር ከሆነ ወልድም ደግሞ መንፈስ ነው፡፡ የወልድ ኢሴንስ መለኮታዊ መንፈስ ነው፡፡

. የትራይ-ዩኒቲ ኢሴንስ ማንነት፡ መለኮታዊ መንፈስ

የስላሴ ሶስት  አካላት አንድ ኢሴንስ እንደሆነ የእንዳንዱ የስላሴ አባል ኢሴንስም መለኮታዊ መንፈስ እንደሆነ አይተናል፡፡ ስለዚህ የትሪኒቲ ዩኒፋይንግ ኢሴንስ ተፈጥሮ መለኮታዊ መንፈስ ነው፡፡

አሁን ለአንዳንድ   . . .  ዝግጁ ነን

IX.          የስላሴ ትርጉም

ጌስለር እና ብሩክስ ይቀጥላሉ፡ ይሁን እንጂ፣ የኦርቶዶክስ ትምህርት ስለትሪኒቲ በአንድ ማንነት ውስጥ ሶስት  አካላት አሉ ይላል፡፡ “ (ጌስለር እና ብሩክስ፣ 19-20)፡፡

ዶክተር ቻፈር መለኮትን በተመለከተ፣ ሶስት ኮንሸስነስ ግን አንድ ማንነት . . .” አለ ይላል (ቻፈር፣ 275)፡፡ ስላሴ- አንድን አምላክ ለመፍጠር ሙሉ በሙሉ የተዋሃዱ ሶስት የተዋሃዱ የተለያየ ህልውና የሌላቸው ሰዎችን የያዘ ነው” (ቻፈር 276)፡፡

ዶክትር ሪሪ ትሪኒታቴ፡፡ የስላሴ ጽንሰ ሃሳብ በምእራብ ቤተ ክርስቲያን በዚህ  በኦገስቲን ስራ (354-430) የፍጻሜ ፎርሙሌሽን ላይ ደርሷል . . . በዚህ ትሪታይዝ እንዳንዱ የስላሴ ሶስት አካላት መላውን ኢሴንስ እነደያዘ እና ሁሉም በሌሎቹ ላይ ጥገኞች እንደሆኑ ይናገራል፡፡ “ (ቤሲክ ቲዎሎጂ፣ 385)፡፡

ከዚህ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ዶክተር ሪሪ (ቤዚክ ቲዎሎጂ፣ 53) ከሁሉም የተሻለው (ትርጓሜ) (የዋርፊልድ ) ነው፡ አንድ እውነተኛ አምላክ ብቻ አለ፣ በእግዚአብሔር አንድነት ውስጥ ግን ሶስት አብረው ዘላለማዊ እና አብረው አኩል የሆኑ በይዘት/ሰብስታንስ አንድ አይነት በሰብሲስተንስ ግን የተለያዩ አካላት አሉ፣ ፡፡ “ (. ዋርፊልድ ስላሴ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ ባይብል ኢንሳይክሎፒድያ፣ ጀምስ ኦር (ግራንድ ራፒድስ፡ አርድማንስ፣ 1930) 53012)፡፡

ዶክጸር ፍሩችተንቦም ነገር ግን የትሪኒቲ የላቀው እና ቀላሉ ትርጉም አንድ አምላክ ብቻ እናዳለ ነገር ግን በእግዚአብሔር አንድነት ውስጥ በሰብስታንስም / በኢሴንስ ተመሳሳይ በሰብሲሰተንስም / በህልውና ግን የተለያዩሶስት ዘላለማዊ እና አኩል አካላት አሉ፡፡

(ፍሩችተንቦም፣ ዶክትር አርኖልድ . ሬዲዮ ማስክሪፕት # 50 ስላሴ፡፡ ሳን አንቶንዮ፡ ኤርየል ሚኒስትሪስ ፣ፕሬስ፣ ገጽ 4)፡፡

·         ሶስት  ኮንሸስነስ ግን አንድ ማንነት . . . .

·         ሶስት አካላት በአንድ ማንነት ውስጥ

·         ሶስት የተዋሃዱ አካላት ያለተለያየ ህልውና

·         የስላሴ ሶስት አካላት መላውን ኢሴንስ ይዘዋል ደግሞም   . . .  ሁሉም እርስበርስ ጥገኞች ናቸው . . .

·         ሶስት  ዘላለማዊ እና እኩል አካላት ሰብስታንስ ወይም በኢሴንስ ግን የተለያዩ . . . .

·         በሰብስታንስ ወይም በኢሴንስ አንድ በሰብሲስተንስ ወይም በህልውና ግን የተለያዩ

X.           ስለ ትሪኒቲ የተጠቆመ  ትርጉም

የትሪኒቲ ኢሴንስ ምንነት መለኮታዊ መንፈስ እስከሆነ ድረስ፣ ይህንን ትርጉም እጠቁማለሁ

ስላሴ በጋራ

አንድ መለኮታዊ

መንፈስን የያዙ ሶስት

መለኮታዊ አካላትን

ያቀፈ ነው፡፡

XI.          አንድ መለኮታዊ አካል የሌላውን ቅርጽ ይይዛልን?

አብ በኢየሱስ መልክ  መጥቷል፡፡” “አብ በመንፈስ መልክ መጥቷል” “ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መልክ መጥቷል

እንዲህ ያሉ አባባልን ሰምተው ያውቃሉን?  ደህና፣ እውነት አይደሉም፡፡

ከመለኮት አካላት አንዱ በሌላው መልክ እንደመጣ የሚናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በፍጹም አታገኙም፡፡ በጋራ ንድ ኢሴንስን ይዘዋል ነገር ግን  ሁልጊዜ የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ መለያቸውን አያስወግዱም፣ አያስተላልፉም ወይም አይለውጡም፡፡ በፍጹም፡፡ ይሁን አንጂ ቀረብ የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ እንደዛ እንደሚያደርጉ የሚጠቁመው ሉቃስ 322 ነው፡ መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።

መንፈስ ቅዱስ የርግብ ቅርጽን ይሰጣል ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መሆንን አያቆምም፡፡

 

በርግጥ ሙሉው ክፍል የየራሳቸውን መለያ ይዘው እርስ በርስ በስምምነት እንደሚሰሩ ይናገራል፡፡

መንፈስ በኢየሱስ ላይ ወርዷል እግዚአብሄር አብም በልጁ ደስ እንደሚለው ተናገሯል፡፡ ኢየሱስ አዳባባይ አገልግቱን እንዲጀምር፡ ሶስቱ አካላት እንዳንዱ የራሱን መለያ ሳይለቅ በመልካም ሁኔታ አብረው ይሰራሉ፡፡

አንድ አካል የሌላውን መልክ በፍጹም አይዝም፡፡

XII.        ሥጋ የለበሰው ወልድ፡ ሃፖስታቲክ ዩኒየን  - ልዩ ትኩረት

ስጋ ሲለብስ ወልድ በመለኮታዊ ኢሴንሱ እና ስብዕናው ላይ ቡሉ በሙሉ የሰው መንፈስ እና ሙሉ በሙሉ የሰው አካልን ጨምሯል፤ ቢሆንም ግን ፍጹም መለኮት መሆንን ለቅጽበት እንኳን አልለቀቀም (ቆላ 29)፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ በስጋዊ ማንነቱ ሲመላለስም እንኳን ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በስላሴ ውስጥ ነበር፡፡ ዘላለማዊ፣ በሁሉም ስፍራ የሚገኝ፣ ሁሉን አዋቂ እና ሁሉን ቻይ መሆኑን ትቶ አያውቅም፡፡

ኢየሱስ አሁን በሰማያት አለ፣ ለዘላለም የስላሴ ክፍል ሆኖ፣ የሰውን መንፈስ አሁንም በመያዝ (ሉቃስ 2346) በከበረ አካል፡፡ ምንም እንኳን ስላሴ በሁሉ ስፍራ የሚኖር ቢሆንም የኢየሱስ አካል ግን እንደዛ አይደለም፡፡ ይህ ወደሰማይ ያረገው በአካባቢ/ሎካላይዝድ ማንነቱ በመሆኑ እውነታ መታየት ይችላል (ሐዋ ስራ 19)፡፡ በንጥቀት ጊዜ ቅዱሳንን  በስጋዊ ማንነቱ በአካባቢ ስፍራ (“ በአየር ላይ” 1 ተሰ 417) ወደ ምድርም በአካባቢ ፈረስ እንደሚመለስ በትንሳኤ/ በንጥቀት ጊዜ  መንፈሳቸው ሎካላይዝድ አካላቸውን በተቀበለ ቅዱሳን ታጅቦ (1 ቆሮ 15 51-54 ራእይ 1911 1521) የመመለሱ እውነታ መታየት ይችላል፡፡

በተጨማሪ ቅዱስ መጽሐፍ ከንጥቀት በኋላ የከበሩ የቅዱሳን አካላት  በሰማይ ለሰባት አመታት የሚኖሩ ሎካላይዝድ ከሆኑ በቀር ሌላ ነገር አይሆንም፡፡ ይህ የከበሩ አካላት በሰማይ ሎካላይዝድ በሆነ ፎርም እንደሚኖሩ ብርቱ ማስረጃ ነው፡፡ የኢየሱስን ሰባዊ መንፈስ በተመለከተ ቅዱስ መጽሐፍ ለሰው መንፈስ በሁሉ ስፍራ እንደሚገኝ አይገልጽም፡፡ ስለዚህ የእርሱ የሰው መንፈስ በኣካሉ ውስጥ ሎካላይዝድ እንደሆነ መደምደሙ የእኛ ድርሻ ነው፡፡ 

 

ልክ የእኛ መንፈስ በእኛ ውስጥ ሎካላይዝድ እንደሆነ እና በሰማይም እንደሚሆን የእኛ የሰው መንፈሶች ሁሉም ስፍራ እንደማይገኙ  የእርሱም አይገኙም፡፡

ምንም እንኳን የሰው መንፈሱና አካሉ ባይካፈሉም ኢየሱስ መለኮታዊ መንፈስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሁሉም ስፍራ መገኘትን እንደሚጋራ እንዴት ነው መረዳት የምንችለው?

ወዳጆች እዚህ ላይ የመገለጥን ገደብ እንዳለፍን አስባለሁ፤ ተጨማሪ ቬንቸር ማድረግ አለመሞክሩ የተሻለ ነው፡፡

ዘዳ 2929 ምሥጢሩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ነው፤ የተገለጠው ግን የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ እናደርግ ዘንድ ለእኛ ለዘላለምም ለልጆቻችን ነው።

XIII.       እንዴት ነው የስላሴ አንድነት በሶስቱ አካለት መካከል የሚገለጠው?

በዚህ ጥናት ውስጥ ያሉት ብዙዎቹ ቅዱሳት መጽሐፍት ቢያንስ የሚከተሉትን ለመናገር ከበቂ በላይ ናቸው

·         በፍጹም ቅድስና አንድ ናቸው

·         በፍጹም ፍቅር አንድ ናቸው

·         በሁሉም ነገር በአንድ ሃሳብ ናቸው

·         በሁሉም ድርጊቶቻቸው ፍጹም በሆነ ስምምነት አንድ ናቸው

 

XIV.      በድርጊቶቻቸው የግንኙነቶቻቸው ተፈጥሮ ምንድን ነው?

. ኢየሱስ የአብ አገልገይ ነው
ዮሐ 6 38 ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና።

. መንፈስ ቅዱስ የአብ አገልጋይ ነው

ዮሐ 1426 አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።

. መንፈስ ቅዱስ የኢየሱስ አገልጋይ ነው

ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።


ዮሐ
1613

. አብ ወልድን መባረክ ይሻል

ማቴ 317 እነሆም ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

መዝሙር 27 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔ ዛሬ ወለድሁህ።

XV.         በምን አይነት የልብ መንፈስ ነው አንዱ ሌላውን የሚያገለግለው እና የሚባርከው?

እንከን  በሌለው ፍጹም ሰማያዊ የፍቅር መንፈስ፡፡

1 ዮሐ 47-8 ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ የሚወደውም ሁሉ ከእግዚአብሔር ስለ ተወለደ እግዚአብሔርንም ስለሚያውቅ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ።

ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና።

 

አሜን፡፡ 

 

 በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. *  

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines