የዘላለም ዋስትና

 (Eternal Security)

Original English By Norman Manzon
Translation By Zemen Endale Lashetew

 

ማይና ምድር ያልፋሉ፥ ቃሌ ግን አያልፍም። ማቴዎስ 2435 

 1) አማኞች  በእግዚአብሔር ሐይል የዘላለም ዋስትና እንዳላቸዉ እናምናለን ይህም በዉስጣችን በሚያድረዉ በመንፈስ ቅዱስ  አማካይት  ዳግም ልደት በማግኘትና በመታተም የሚሆን ነዉ፤

) በመጀመሪያ ማሰብ ያለብን

ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንደሚሉት ሰዉ አንድ ጊዜ ደህንነትን ካገኘ በኋላ ድነቱ እንደማይጠፋ ነዉ፤ በአንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም ሰዉ አንድ ጊዜ ድነቱን ካገኘ በኋላ እንደሚያጣዉ የሚናገሩ ክፍሎችም አሉ፤

ሁለት ሀሳቦች የተጣበቁ ናቸዉ

 1. መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጣረሳል ወይም አይጣረስም ማለት ነዉ፤ ካልተጣረሰ የተጻፈዉን ሁሉ ማመንና መቀበል ይኖርብናል፤
 2. አማኝ ድነቱን ሊያጣ ወይም ላያጣ ይችላል፤ የሚያጣ ከሆነ ግን ላለማጣት ራሱን አሳልፎ መስጠት  ይኖርበታል፤ ማንኛዉም በሕይወቱ ላይ አደጋ ሊያመጣ ከሚችል ሐጢአት ሁሉ ማስወገድ አለበት፤ ድነቱን ለማስጠበቅ የጸድቅ ሕይወትን በመለማመድ መትጋት ይኖርበታል፤ ይህ አይነት ሕይወት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በፍርሃት እንዲሞላ ያደርገዋል፤ ወደ ሲኦል እገባ ይሆንን በሚል ስጋት ማለት ነዉ፤ አማኝ ድነቱን የማያጣ ከሆነ ግን ያለ ፍርሃትና ስጋት በእግዚአብሔር ዋስትና ላይ በማረፍ የተባረከዉን የዘላለም ዋስትና በእግዚአብሔር መገኘት ዉስጥ ሆኖ ያጣጥማል፤እርሱን የምናገለግለዉ ከሲኦል ለመዳን ሳይሆን በእርሱ ፊት ለመደሰት ነዉ፤( ዕብ 122) ወይም ደግሞ ሀጢአት በሰራህ ቁጥር ወደ ዘላለም ጥፋት ትሄዳለህ ማለትም አይደለም፤

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ወደሚለዉ ሀሳብ እንግባ፤ በመጀመሪያ ስለ ዘላለም ዋስትና የሚነግሩን የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ከፍሎችን እንመልከት ከዚያም ጥቂት

በሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ዋስትና  የሚለዉን እናያለን፤

) የዘላለም ዋስትና የሚለዉን ሐሳብ የሚደግፉ ክፍሎች

የኤ ኤም አዋጅ ግምት ዉስጥ አስገብተን እንጀምራለን

ሁሉም አማኞች የዘላለም ዋስትናቸዉ የተጠበቀ ነዉ

ይህ ማለት ሁሉም አማኞች የዘላለም ዋስትና አላቸዉ ማንም አማኝ ምንም ይሁን ምን ድነቱን አያጣም የዘላለምን ሕይወት ይወርሳል፤

አማኞች የተጠበቁ ናቸዉ

ይሁዳ 11 የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ የያዕቆብም ወንድም የሆነ ይሁዳ፥ በእግዚአብሔር አብ ተወደው ለኢየሱስ ክርስቶስም ተጠብቀው ለተጠሩ፤

1ጴጥ 15 ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።

መጠበቅ የሚለዉ ቃል  ጥበቃ  ማድረግ ሲሆን እግዚአብሔር ይጠብቃል፣ዋስትና ይሰጣል፣ በክርስቶስ ያመኑትን አማኞች ይጠብቃል-ይህም ጊዜያዊ አይደለም- በመጨረሻዉ ዘመን ሊገለጥ ላለዉ ድነት ሲሆን ከዚያም ከጌታ ጋር ወደ  ዘላለማዊ ቤታቸዉ መንግስተ ሰማይ ይገባሉ፤

በእግዚአብሔር ሐይል

አጠቃላይ የቃሉ ትርጉም የራስ ማረጋገጫ ሲሆን ሁለት ነገሮች መታወቅ አለባቸዉ፤

 1. የሰዉን ስራ የሚቃወም ክፍል መሆኑን ነዉ- እግዚአብሔር ብቻ ነዉ አማኞችንን ዋስትና የሚያስጠብቅ እንጂ አማኙ ራሱ አይደለም
 2. በአማኞች ዉስጥ ያለዉ የእግዚአብሔር ሐይል ሐይለኛ እና ታላቅ ነዉ፤ ጳዉሎስ ስለ እግዚአብሔር ሐይል ሲናገር በተለይ ስለወደፊቱ ተስፋ ነዉ፤

 ኤፌሶን 118-19

ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤

                                                                                                                        ኤፌሶን 118-19

ታላቁና ሐይለኛዉ የእግዚአብሔር ሐይል ድነታችንን ይጠብቃል፤የሰዉ ሐይልና ጥረት ምንም ሊያደርግ አይችልም፤ በእግዚአብሔር ተጠብቆ ዋስትና የማይሰማዉ ማን ነዉ?

በዳግም ልደት

በክርስቶስ ዳግም ልደት ሲሆን የሚያፈራዉ ፍሬ አዲስ ፍጥረት መሆን ነዉ (2ቆሮ 517)፤በተፈጥሮ ልጆች ሲወለዱ በሐጢአት ከተበላሸ ዘር ነዉ የሚሞቱትም ከሚዛመተዉ ሐጢአት የተነሳ ነዉ፤ በክርስቶስ ዳግም የተወለደ ግን አዲስ ፍጥረት እንጂ ከተበላሸ ዘር አይደለም፤ የእግዚአብሔር ቃል የተበላሸ አይደለም ለዘላለም የሚኖር ያልተበላሸ ነዉ( (1ጴጥ 123) በመንፈስ ሊሞት አይችልም ምክንያቱም ዳግም የተወለደዉ ከሚጠፋ ዘር ሳይሆን ከማይጠፋዉ ዘር ነዉ፤

መኖር

እንደ ገላ 46 መንፈስ ቅዱስ በማንኛዉም አማኝ ዉስጥ ካመነበት ጊዜና ሰአት ጀምሮ ያድራል፤ ‹‹ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ››

እንደ ዮሐ 1416 መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ዉስጥ ለዘላለም ይኖራል ‹‹እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል››

መንፈስ ቅዱስ አንድ ሰዉ በዳነ ጊዜ በዉስጡ የሚያድር ከሆነ የሚያድረዉ እስከ ፍጻሜዉ ድረስ ነዉ፤መንፈስ ቅዱስ ለጊዜዉ ወይም ለአጭር ጊዜ አይደለም ለማደር የሚመጣዉ፤ ለጊዜዉ የሚመጣ ከሆነ ግን በዉስጡ አላደረም ማለት ነዉ፤መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ሕይወት የሚያድር ከሆነና አማኙም በመንፈስ ቅዱስ ዉስጥ የሚያድር ከሆነ ወደ ሲኦል ይጣላልን? እግዚአብሔር ወደ ሲኦል ይጥለዋል?

በመንፈስ ቅዱስ መታተም

2ቆሮንቶስ 122 ደግሞም ያተመን (እግዚአብሔር)  የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።

ኤፌሶን 430 “ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።

እና ኤፌሶን 113-14

13. እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።

የመዋጀት ቀን እስኪደርስ ድረስ መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ያትማል፤ ይህ ማለት የትንሳኤ ቀንና በንጥቀት ወቅት ስለሚለወጠዉ አካል ማለት ነዉ፤ መንፈስ ቅዱስ የሚመለከተዉ አማኞች አሁን ባሉበት እንዲህ ሆነዉ ሳይሆን በክርስቶስ እንደሚነጠቁ ነዉ፤ መንፈስ ቅዱስ አሁን በልባችን የተሰጠን እንደ መያዣ ነዉ ዘላለማዊ ቤታችን እስኪያገባን ድረስ አይተወንም፤ ነፍሳችንና ስጋችን በዚያን ቀን ከእርሱ ጋር አብረዉ ይሆናሉ::

) ስለ ዘላለማዊ ዋስትና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ

 1. አማኝ ለሕግ የሞተ ነዉ ከዚህ በኋላ በሕግ ሊፈረድበት አይችልም ሮሜ 64-10

እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።

ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን፤

ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን፤ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቋልና።

- ነገር ግን ከክርስቶስ ጋር ከሞትን ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንድንኖር እናምናለን፤

ክርስቶስ ከሙታን ተነሥቶ ወደ ፊት እንዳይሞት ሞትም ወደ ፊት እንዳይገዛው እናውቃለንና።

¹ መሞትን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለኃጢአት ሞቶአልና፤ በሕይወት መኖርን ግን ለእግዚአብሔር ይኖራል።

 ገላ219-20 እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርናከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም…”

እነዚህ ክፍሎች የሚከተሉትን ነገሮች ያመጣሉ

1.    የአማኝ ስጋ ከክርስቶስ ጋር ተሰቅሎአል ሞቷል ከእርሱም ጋር ተቀብሮአል፤

2.    የአማኝ ስጋ ተወግዷል የሐጢአት ስጋ አይደለም እንደገና ሊፈረድበት አይችልም

3.    የሞተዉ ከሐጢአቱ ጸድቋል፤አማኝ ከክርስቶስ ጋር ሞቷል ከሐጢአቱም ጸድቋል፤ የሐጢአት ስጋ የለዉም ላይጸድቅም አይችልም፤ድነቱም በክርስቶስ ተጠብቋል፤

4.    በክርስቶስ የሆኑ ሁሉ ድነታቸዉ በክርስቶስ ተጠብቋል፤

2.መንፈሳዊ እድገትና ቅድስና አብረዉ የሚያድጉ ናቸዉ

ጳዉሎስ ሲያረጋግጥ ‹‹በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፤ (ፊሊ16) መፈጸም ማለት ወደፊት ይዞ በመሄድ መጨረስ ማለት ነዉ፤

1ቆሮ 18 እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል፤

ይህ ማለት ግልጽና ቀጥተኛ የሆነ ሲሆን ጀማሪዉ እግዚአብሔር እስከመጨረሻዉ ማለትም ዘላለማዊ ቤታቸዉ እስኪደርሱ  ድረስ ያጸናቸዋል ማለት ነዉ፤

3.              የኢየሱስ ግልጽ የሆነ ቃል በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ ሶስት ነገሮችን እናያለን

ዮሐ 3:14-16

¹ ሙሴም በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ይሰቀል ይገባዋል።
¹
በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። 

ዮሐ 524 እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም

ዮሐ 10:27-29

² በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
²
እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
²
የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። 

ከላይ ያለዉ ንግግር የሚያስማማ ሲሆን፤ ሊቃረነዉ የማይችለዉ፤

የዘላለም ሕይወት አላቸዉ እንጂ አይጠፉም

ወደ ፍርድ አይመጡም በፍጹም አይጠፉም

ከእጄ ማንም አይነጥቃቸዉም

ከአባቴም እጅ ማንም አይነጥቃቸዉም

ኢየሱስን የምናምን ከሆነ እርሱ የተናገራቸዉን ሁሉ ማመን አለብን ይህም አማኞች አይጠፉም የሚለዉን ማለት ነዉ፤

4.ኢየሱስ አማላጃችን እና በአብ ፊት ጠበቃችን ነዉ፤

1ዮሐ21ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

ዕብ 725 ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል

የኢየሱስ ማማለድ ዋና አላማዉ እስከመጨረሻዉ እንድንድን ነዉ፤

መጽሐፍ ቅዱስ እስከመጨረሻዉ የሚለዉ ዘላለማዊ የሆነ ሙሉነትን ነዉ፤ ለሁሉም ሰዉ እስከመጨረሻዉ መዳን በቂ ነዉ፤

ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሰራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደ ምትሆን ቅድስት አልገባምና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ። (ዕብ924)

5.   የሮሜ 8 ዋስትና

የሮሜ 1-7 ድረስ ያለዉ የሐጢአትን በደለኝነት የሚናገር ሲሆን ዘላለማዊ የሆነ ይቅርታ በክርስቶስ እንደተደረገ ነዉ (323 623) ጳዉሎስ ሮሜ 7 ሲያጠቃልል .24 ላይ እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል? .25 በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እንግዲያስ እኔ በአእምሮዬ ለእግዚአብሔር ሕግ፥ በሥጋዬ ግን ለኃጢአት ሕግ እገዛለሁ።

ሮሜ 8 ላይ ሲቀጥል በዚሁ አምልኮ በመቀጠል የድነት ዋስትና ኢየሱስ መሆኑን ይነግረናል፤ ጥቂት ነገሮችን እንመልከት

 1. በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ አሁን ኩነኔ የለባቸዉም በክርስቶስ ያለዉ የሕይወት መንፈስ ሕግ ከሐጢአት እና ከሞት ሕግ ነጻ አዉጥቶኛልና

አማኞች ሐጢአት ቢሰሩ እንኳ አይፈረድባቸዉም ምክንያቱም የዘላለም ሞት፣ሲኦል ይፈረድብሃል ከሚለዉ የእግዚአበሔር ሕግ ነጻ ወጥተዋልና፤ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን (ኢየሱስን) ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” 2ቆሮ 521

አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። (ሮሜ815)

ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤ (ሮሜ 829)

(ሮሜ 838-39)

³ ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥
³
ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።

የእግዚአብሔር ቅደመዉሳኔ የማይከናወነዉ በተመረጡ በራሳቸዉ ሰዎች ነዉን? በዘላለማዊ እድል አይደለም! ለዚህ ጳዉሎስ ሲናገር አንድም ሰዉ ዘላለማዊ  አይደለም አማኝም ቢሆን ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለየዉ ነገር የለም፤

2.   ሁኔታዊ ዋስትናን የሚደግፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል

ሁኔታዊ ዋስትና ማለት አማኞች ዘላለማዊ ሕይወትን የሚያገኙት ከእነርሱ የሚጠበቀዉን ነገር ሲያሟሉና ሌሎችን ሲያስወግዱ ማለት ነዉ፤ የዚህ አይነቱ አመለካከት በአንድ ሰዉ ድነት ዉስጥ ምንም የእግዚአበሔር ሐይል ጣልቃ አለመግባቱን የሚያሳይ ነዉ፤አማኞች እነዚያን ሁኔታዎች ካላሟሉ የእግዚአብሔር ሐይል እንደማያገኛቸዉ ነዉ፤ ከላይ አንደተመለከትነዉ (ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል። (1ጴጥ 15) ይህ  በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ዋስትና ማለት አብሮ የሚኖሩ ነገር ግን የማይስማሙ ቃላት ናቸዉ፤ ሁኔታዊ ከሆነ እንዴት የአንድ ሰዉ ድነት በሰማይ ዋስትናን ያገኛል? መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሐሳብ ለማረጋገጥ ወይም ላለማረጋገጥ የሚለዉ ነገር የለም፤

ሎይስ ስፔሪ ቻፈር ሲናገር ‹‹ ብዙዎች እንደሚሉት ሰማንያ አምስት ከፍሎችን ዘርዝሮ የአርሜንያን አመለካከት የተመሰረተዉ በሁኔታዊ ዋስትና ላይ ነዉ፤(ሜጀር ባይብል ቲምስ ገጽ 220 ከበታች ያሉትን ነጥቦች ይመልከቱ) ሰማንያ አምስቱን ክፍሎች አንመረምርም፤ ነገር ግን ብዙ ጊዜ ተደጋግመዉ የተጠቀሱትን እንመለከታለን ነገር ግን በመጀመሪያ የሰዉን እይታና ፍርድ እንመልከት፤ 

በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ድነትን እንድናምን የሚያደርግ አንዳንድ ግልጽ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፤ ነገር ግን የምንመለከተዉና የምንለማመደዉ ነዉ፤ ብዙዎቻችን ብዙ ሰዎች ለጌታ ቅንአት እንዳላቸዉ እና እርሱን እንደሚፈልጉት እናያለን፤ወደ ሐጢአት ዉስጥ ደግሞ ገብተዉ ይዋኛሉ በዙዎች ይህን ሲመለከቱ እንደዚህ አይነት ሰዎች ድነታቸዉን ያጣሉ ወደሚል ድምዳሜ ይደርሳሉ፤ የሰዎች አመለካከትና ልምምድ የመጽሐፍ ቅዱስን እዉነት ሊገድበዉ አይችልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ የተሰጠን አመለካከታችንን እና ልምምዳችንን ለማስተካከል ነዉ፤ የእኛ ትርጉም፣አመለካከትና ልምምድ ስህተት ይኖርበታል፣ፍጹም አይደለም፣ትክክለኛ አይደለም ስህተት አለበት፤ የእግዚአብሔር ቃል ግን ፍጹም ነዉ እርሱ ብቻዉን ልክ እና ብርሃን ስለሆነ የእኛ አመለካከትና ልምምድ በእርሱ ይፈተሻል፤

ዘላለማዊ ዋስትና የሚለዉን ትምህርት መርምረን አይተናል አሁን ደግሞ በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ዋስትና የሚለዉን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እንመልከት

. አማኞች ለመዳን እስከመጨረሻዉ መጽናት አለባቸዉ

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲናገር ‹‹እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል።( ማቴ 2413)

ክፍሉ አማኞች እስከመጨረሻዉ ድረስ የማይጸኑ ከሆነ የዘላለምን ሕይወት የሚያጡ ይመስላል፤ ክፍሉ ግን የሚናገረዉ ለአማኞች ወይም ስለዘላለም ሕይወት የሚናገር አይደለም፤ቁ.1314እና 15 አዉዱ የሚናገረዉ ስለ ታላቁ መከራ ነዉ በተለይ .15 አና 16 ኢየሱስ እየተናገረ ያለዉ ለአይሁዳዉያን ነዉ፤ ዘካ138-9 እና ሕዝ 2038 በዚያ አስቸጋሪ ጊዜ ‹‹የያዕቆብ ችግር›› (ኤር 307) ታላቁ መከራ፣እግዚአብሔር የሚገድለዉ የእስራኤል አመጸኞችን ነዉ፤ 2/3ኛዉን በሐሳዊ መሲህ ሰራዊት አለምን የሚያሳምጹትን ሲሆን 1/3 ኛዉ ግን መንፈሳዊ እዉነትን የያዙ ሰዎች ናቸዉ፤ እነዚህ ጥቂት ሰዎች በእግዚአብሔር ጥበቃ በመከራዉ መካከል እስከ መጨረሻዉ የሚጸኑ ናቸዉ፤ በእግዚአብሔር ልዑላዊነት መንፈስ ቅዱስን ስለሚያፈስላቸዉ በመንፈስ ይድናሉ፤( ዘካ 1210131)

ጥቅሶቹ ሁኔታዊ ዋስትናን የሚደግፉ አይደሉም አላማኞች በአካል ስለመጽናታቸዉ እንጂ ስለአማኞች በእምነት በአካሄዳቸዉ ስለመጽናታቸዉ መናገሩ አይደለም፤

. አማኞች በወይኑ ግንድ ባይኖሩ ተቆርጠዉ ወደ እሳት ይጣላሉ::

በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።( ዮሐ 156) እስኪ ጥቅሱን እንመርምር::

ዮሐ 154-6

በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።
እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።
በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል። 

ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ሲያስተምር ድብቅ ትርጉም እንዲፈልጉ አድርጎ ነዉ፤ ዓላማዉ ዋናዉን ነጥብ ለማስጠንቀቅና ዝርዝር ሀሳቡን እንዲተረጉሙትና እንዲለማመዱት ለማድረግ ነዉ፤ ዋናዉ ነጥብ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱ በእርሱ እንዲኖሩና ፍሬያማ ሕይወት እንዲኖሩ ለማድረግ ነዉ፤ ስህተቱን በደንብ ማየት ያስፈልጋል ፍሬያማ ያልሆኑ ቅርንጫፎች ተቆርጠዉ ወደ እሳት ይጣላሉ ማለት ፍሬያማ ያልሆኑ አማኞች ወደ ሲኦል ይጣላሉ ማለት ነዉን? የእርሱ ምክር አማኞች በዳኑበት መዳን እስከ መጨረሻዉ እንዲጸኑና እንዲቀጥሉ ማድረግ ነዉ፤

አንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ የአተረጓጎም መርህ  ግልጽ ያልሆኑ ሐሳቦችን ግልጽ በሆነዉ ሐሳብ መመልከት  ነዉ፤ ፍሬ የማያፈራዉን ቅርንጫፍ ተቆርጦ ወደ እሳት ይጣላል ማለት ከሌሎቹ ስለፍሬ ከሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር በማስተያየት ማጥናት ያስፈልጋል፤  ለምሳሌ እንደ (1ቆሮ 311-15)

1ቆሮ 311-15

¹¹ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
¹²
ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ 

¹³ በእሳት ስለሚገለጥ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
¹
ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤
¹
የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።

ክፍሉ ግልጽ አድርጎ እንደሚነግረን አማኞች ፍሬያማ ሕይወት ካልኖሩ ሽልማት አያገኙም ማለት ነዉ ነገር ግን ይድናል፤ ስለዚህ ፍሬያማ ያልሆኑ ቅርንጫፎች ተቆርጠዉ ወደ እሳት ይጣላሉ ማለት ፈሬያማ ያልሆኑ አማኞች ወደ ሲኦል ይወርዳሉ ማለት አይደለም፤ ክፍሉ የሚናገረዉ ፍሬቢስ ስለሆነዉ አገልግሎት ነዉ፤ በክርስቶስ መኖር ማለት አማኞች ሁሉ ለመዳን ፈቃዱን ማድረግና መለማመድ ማለት አይደለም፤ አማኞች ሁሉ ግን ጌታ ያዘጋጀለትን ነገር ፍሬያማ ለመሆን ማገልገል ማለት ነዉ፤ እንደ ጸሎት (ሐዋ 439) ቃሉን ማሰላሰል (2ጢሞ316) መታመን (ምሳ 35 ማቴ 2818) እና ተግባር (ማቴ 2819-20)

. አማኞች ሊጣሉ ይችላሉ::

1ቆሮ 927 ጳዉሎሰ ሲናገር ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ፤ መጣል የሚለዉ በሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ላይ ከዉድድር መዉጣት፣ወይም መጣል ወይም ያልተረጋገጠ ማለት ነዉ፤

አንዳንዶች እንደሚናገሩት አማኞች ድነታቸዉን ሊያጡ ይችላሉ ነገር ግን ጳዉሎስ ይህን በርግጥ ተናግሮአልን? አሁንም ጥቅሱን በአዉዱ መሰረት ማየት ያስፈልጋል::

1ቆሮ 916,24-27

¹ ወንጌልን ብሰብክ እንኳ የምመካበት የለኝም፤ ግድ ደርሶብኝ ነውና፤ ወንጌልንም ባልሰብክ ወዮልኝ።

²
በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²
የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።
²
ስለዚህ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፥ ነፋስን እንደሚጎስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤
²
ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ ራሴ የተጣልሁ እንዳልሆን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ።

ጳዉሎስ ወንጌል መስበክን ከሩጫ ዉድድር ጋር አያይዞ የተናገረ ሲሆን በቦክስ ዉድድር የሚሸለመዉ አሸናፊዉ ብቻ ነዉ እርሱ አየተናገረ ለዉ ሽልማትን ከማግኘት ጋር ነዉ፤ በበ1ቆሮ312 ላይ በግልጽ እንደሚናገረዉ የማይጠፋዉ ሽልማት የወርቅ፣የብር እና የከበረ ድንጋይ ነዉ፤ ስለ ድነት የሚናገር ክፍል አይደለም፤ ሽልማቱን እንደሚያጣዉ አትሌት ሳይሆን ራሴን አስገዝቼ ባሪያ በመሆን ሽልማቴን ለማግኘት እሮጣለሁ ነዉ የሚለዉ፤

መጣል ማለት በአንድ አማኝ ሕይወት ዉስጥ ድነትን ማጣት ማለት ሳይሆን ሽልማትን ማጣት ማለት ነዉ፤

. አማኝ ከጸጋዉ ሊወድቅ ይችላል

ከጸጋዉ መዉደቅ ሚለዉ ሐሳብ ያለዉ (በገላ51-4) ዉስጥ ነዉ፤

ገላ 51-4

¹ በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።
²
እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ፦ ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም።
³
ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ።
በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። 

አንዳንዶች እንደሚሉት ከጸጋዉ መዉደቅ ማለት ድነትን ማጣት ይመስላቸዋል የሚቀጥለዉን ቁጥር ስንመለከት ትርጉሙ ትክክለኛ እንዳልሆነ እናያለን፤ .5 እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና ከጸጋዉ የወደቁ ሰዎች የጽድቅን ተስፋ ከሚጠባበቁ መካከል ያሉ ናቸዉ፤ ያልዳነ ሰዉ በመንፈስ ቅዱስ ምንም ማድረግ አይችልም ምክንያቱም መንፈስ የለዉምና ስለዚህ ከጸጋዉ የወደቁ ሰዎች የዳኑ ናቸዉ፤ ከጸጋዉ መዉደቅ ማለት ድነትን ማጣት ሳይሆን ሌላ ነገር ማለት ነዉ፤

ምን ማለት ነዉ? .1 እና 2 በክርስቶስ ነጻነት እና የሕግ ባሪያ መሆን ማለት .2 ላይ አማኞች ጸደቅን ለማግኘት ሲሉ ሕግን እንጠብቃለን ሲሉ ከጸጋዉ ይወድቃሉ በእግዚአብሔር በሚገኘዉ ጽደቅ ላይ የሚታመኑ አይደሉም ሕግን መጠበቅ ጨምሮ ማለት ነዉ፤ ራሳቸዉን ከሕግ በታች አኑረዋል ራሳቸዉንም ድነት በስራ እንደሚገኝ አድርገዉ ቆጥረዋል፤ ይህ ማለት ደግሞ ከእግዚአብሔር ጸጋ መዉደቅ ማለት ነዉ፤ በዚህ ሐሳብ ብቻ ነዉ ከጸጋዉ ወድቀዋል የሚባለዉ፤

ክፍሉ ድነትን ስለማጣት የሚናገር አይደለም፤ ነገር ግን ራሳቸዉን በሕግ ስር ስላስቀመጡ ነዉ እነዚህም ሰዎች የዳኑ ናቸዉ፤

) አማኝ ሐጢአቱን ሳይናዘዝ ከሞተ በእግዚአበሔር ይቅርታን አያገኝም

ይህ ግራ መጋባት የመጣዉ 1ዮሐ 19 ሲሆን በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።

አንዳንድ ሰዎች በዚህ ጥቅስ ግራ የሚጋቡ ሲሆን ላላመኑ ሰዎች የወንጌል ጥሪ የሚመስላቸዉ ይመስላል ነገር ግን 21 ላይ ዮሐንስ ለማን እንደሚናገር ግልጽ አድርጎታል ይህም ለዳኑ አማኞች ኢየሱስ በሰማይ ጠበቃ እንዳለን ነዉ፤ ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዮሐንስ የጻፈዉ ለአማኞች ሲሆን እርሱም በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን  ይላል፤ የኢየሱስ ጥብቅና በሐጢአተኞች አማኞች ፈንታ ሆኖ በአብ ፊት ይቆማል ይህም ለድነታቸዉ ዋስትና ነዉ፤ አማኝ ሀጢአት ቢሰራና ሳይናዘዘዉ ቢሞት ሀጢአቶቹን ቢያዉቅና ቢያስታዉሳቸዉም ድነቱ የተጠበቀ ነዉ፤

ዮሐንስ እያለ ያለዉ መናዘዝ ለድነት መናዘዝን አይደለም ለድነት መናዘዝ ማለት ኢየሱስ ጌታ ስለመሆኑ መናገር ማለት እንጂ ስለሐጢአት መናዘዝ አይደለም ( ሮሜ 109) ዮሐንስ እያለ ያለዉ መናዘዝ ከአብ ጋር ጤናማ የሆነ ግንኙነት እንዲኖረን እና በቅድስናችን እንድንቀጥል የሚያደርግ ነዉ፤

. አማኝ ለሌላዉ ሰዉ ይቅርታ ሳያደርግ ቢሞት በእግዚአብሔር ይቅር አይባልም::

ይህ አስተሳሰብ የመጣዉ የማቴዎስ 615 በደንብ ካለመረዳት ነዉ ለሰዎች ግን ኃጢአታቸውን ይቅር ባትሉ፥ አባታችሁም ኃጢአታችሁን ይቅር አይላችሁም፤

ይቅር የማይባለዉ ሐጢአት ነዉ፤ ኢየሱስ ደግሞ ላለፈዉ፣ለአሁኑና ለወደፊቱ ሐጢአት ሁሉ ሞቷል፤( ሐዋ 319 ኤፌ17 ዕብ 928) እዚህ ቦታ ጌታ እየተናገረ ያለዉ የአንድን ሰዉ ከአባቱ ጋር ስላለዉ ግንኙነት ነዉ፤ አንድ ሰዉ ከባልንጀራዉ ጋር ባለዉ ግንኙነት ይቅር ባይል ከጌታ ጋር ያለዉን የተባረከ ግንኙነቱን ይይዝበታል ማለት ነዉ እንጂ የዘላለምን ሕይወት ማለት አይደለም፤

. አንድ አማኝ ሐጢአትን የሕይወቱ ክፍል አድርጎ ቢሰራ ድነቱን ያጣል

ይህ ሐሳብ በዚህ ክፍል መግቢያ ላይ አይተናል ይህን ሰዉ በሁለት መንገድ እናያለን

 1. ሲጀመር እዉነተኛ አማኝ አይደለም እንክርዳድ ነዉ( ማቴዎስ 1324-30)
 2. እዉነተኛ አማኝ ሆኖ ነገር ግን በሐጢአት ዉስጥ የተዘፈቀ ነዉ፤ ይህን ሁኔታ ማየት ያስፈልጋል፤

ይህ ሁለተኛዉ ሐሳብ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን የነበረዉን ሰዉ ያስታዉሰናል ከአባቱ ሚስት ጋር በዝሙት የተዘፈቀ ማለት ነዉ( 1ቆሮንቶስ 5) እንደሚታወቀዉ አማኝ ነዉ ባይሆን ኖሮ ጳዉሎስ ለሰይጣን አሳልፎ ስጋዉን አይሰጠዉም ነበር፤ ለሰይጣን አሳልፎ የሰጠዉም ይህን በማድረግ የጌታን ትዕዛዝ ለማስታወስ ነዉ፤(ዕብ 214) ኢየሱስ ብቻ ነዉ አማኝን መግደል የሚችለዉ፤(ራዕ118) 1ተሰሎንቄ 414 በክርስቶስ ሆነዉ ስላንቀላፉ አማኞች የሚናገር ነዉ፤ ሰዉየዉ የዳነ ነዉ በጌታ ኢየሱስ እጅ ነዉ የሞቱ ጊዜ ሲደርስ ከሰይጣን ነጻ ይወጣል ማለት ነዉ፤

ሰዉየዉ ድነቱን አላገኘምን? አይደለም ጳዉሎስ  ስለ ሰዉየዉ ተግሳጽ ነዉ የተናገረዉ ‹‹መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው››( 55) ጌታ ብቻ ባለስልጣን ነዉ ሰዉየዉ ድነትን እንዲያገኝ ሀጢአቱን ባይናዘዝም በጌታ ተገስጾ ድነቱን ያገኛል፤ የፈለገዉን ነገር እያደረገ ምንም ባይሆን ተከታዮቹም በሐጢአት ይመላለሳሉ፤

. ሐጢአትን የምትሰራ ነፍሰ ትሞታለች

ይህንን ሐሳብ የምናገኘዉ በሕዝቅኤል 18

4 ሐጢአትን የምትሰራ ነፍስ ትሞታለች

13 በውኑ እርሱ በሕይወት ይኖራልን? በሕይወት አይኖርም፤ ይህን ርኵሰት ሁሉ አድርጎአልና ፈጽሞ ይሞታል፤ ደሙ በላዩ ላይ ይሆናል።

18 እርሱ በበደሉ ይሞታል.

20: ኃጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች.

24: የሠራት ጽድቅ ሁሉ አትታሰብለትም፤ ባደረገው ዓመፅና በሠራት ኃጢአት በዚያች ይሞታል.

26: ኃጢአትንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያም ቢሞት፥ እርሱ ባደረገው በደል ይሞታል፤

ከላይ ያሉት ሐረጎች አማኞች ሐጢአትን በሰሩ ጊዜ ተፈርዶበት የዘላለም ሞት እንደሚያገኛቸዉ ይመስላል እስኪ ምዕራፎችን እንፈትሽ፤

በማንኛዉም ጉዳይ ነፍስ የሚለዉ ቃል ነፊሽ ከሚለዉ የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ነዉ፤ በእንግሊዝኛዉ ነፍስ ማለት -ቁስ የሆነዉ አካል ነዉ፤ ብዙ ምሳሌዎችን በብሉይ ኪዳን ማግኘት ይቻላል፤ የነፍስ ሞት ማለት በሕይወት ያለዉ ሰዉ ሲሞት ነዉ (የነፍስን ከስጋ መለየት) ኢያሱ 1111 በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ ፈጽመውም አጠፉአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም አላስቀሩም አሶርንም በእሳት አቃጠላት።  እንደሚታወቀዉ ሰይፍ ስጋን ነዉ የሚገድለዉ ስለዚህም በሕዝ 18 ላይ ያለዉ ነፍስ የስጋ ሞትን የሚያሳይ ነዉ፤ ይህ ምክንያት ነዉን?

እንደ ቻርለስ ራይሬ በሕዝቅኤል መጽሐፉ መግቢያ ላይ የሕዝቅኤል አገልግሎት ከምርኮ በፊት ሰዎች ሐጢአትን ስለሰሩ ወደ ምርኮ እንደወሰዳቸዉ ይናገራል (ራይሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት) የባቢሎን ምርኮ ብሔራዊ፣ ጊዜያዊና ምድራዊ ፍርድ ነዉ፤ በምዕራፍ 9 ላይ የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደሚታረዱ ይተነብያል ምዕ 2213-22 የሚተነብየዉ ደግሞ ስለ እስራኤል የመጨረሻዉ ዘመን እና በፍጥነት በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚሆነዉ ፍርድ ነዉ፤ ሁለቱም ጊዜያዊና ምድራዊ ፍርዶች ናቸዉ፤ ስለዚህ ምዕራፍ 18 መታየት ያለበት ጊዜያዊ፣ ምድራዊ ፍርድ እንጂ ዘላለማዊ ፍርድ አይደለም፤

ምዕራፉ የያዘዉ ይዘት ሰዎች መልካም ስራ ሲሰሩ በሕይወት ይኖራሉ ክፉን የሚሰሩ ሰዎች ደግሞ ይሞታሉ፤ምድራዊ ፍርዱና ሞቱ ጊዜያዊ እንጂ ዘላለማዊ ሞት አይደለም፤ሐጢአትን የሚሰሩ በስጋቸዉ ይሞታሉ፤ እንዲሀ አይነት ፍርድ የቆሬ ልጆች ሙሴን ተቃወሙ ስለዚህም በስጋቸዉ ተቀጡ ከቆሬ ጋራ ያበሩ ሁሉ ጌታ ገደላቸዉ ከሙሴ የወገኑ ግን ዳኑ፤( ዘኁልቁ 16)

 ማጠቃለያ

 1. የነፍስ ሞት ማለት የስጋን ሞት ያመለክታል
 2. የምዕራፉ አዉድ ግን ብሔራዊ እና የስጋን ፍርድ ያሳያል
 3. እስራኤል በጅምላ ሲገደሉም ይሁን ሲድኑ ከመልካም ወይም ከክፉ ስራቸዉ የተነሳ ነዉ

ምዕራፉ ስለሞት የሚናገረዉ የስጋ ሞትን ነዉ ዘላለማዊ አይደለም ነገር ግን እስኪ ጠቅላላ ምዕራፉን እንመልከት፤ 

ሕዝ 18:1-4

¹ የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
²
ስለ እስራኤል ምድር፦ አባቶች ጨርቋ የወይን ፍሬ በሉ፥ የልጆችም ጥርሶች ጠረሱ ብላችሁ የምትመስሉት ምሳሌ ምንድር ነው?
³
እኔ ሕያው ነኝና እንግዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእስራኤል ዘንድ አትመስሉትም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

እነሆ፥ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ደግሞ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።

ሕዝቡ ያጉረመረሙት በአባቶቻቸዉ ምክንያት መከራን ተቀበሉ እግዚአብሔር በነብያቱ በኩል ይመልስላቸዉ ነበርኃጢአትን የምትሰራ ነፍስ ትሞታለች( .4) ስለምን አይነት መከራ ነዉ የሚያጉረመርሙት? ይህ ዘላለማዊ የሆነ ቅጣት ወይም መከራ አይደለም፤ እስካሁንም በሕይወት አሉ፤በመቀጠልም በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ አንድ ሰዉ ሲፈረድበት ዘላለማዊ ቅጣት ነዉ አይልም በበፊቱም ትዉልድ ቢሆን አልታየም፤ የእነርሱ መከራና ማጉረምረም በምርኮ ዉስጥ ሰለመሆናቸዉ እና ወንድሞች ስለመታረዳቸዉ ነዉ፤ ምናልባትም እነርሱንም የሚያጠቃልል ነዉ፤

ሁሉም ስለሞት የሚያወሩ ጉዳዮች ዘላለማዊ አይደሉም፤ስለዚህም አንድም ጥቅስ በሁኔታ ላይ ስለተመሰረተ ድነት አይናገርም፤

1.   ሐጢአተኛዉ በእምነቱ የሚድን ከሆነ እምነቱነ ሲያጣ አይድንም ማለት ነዉ፤

1ጴጥ15 ሲናገር በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፤ ከዚህ ክፍል እንደምንረዳዉ እግዚአብሔር አማኞችን በሰማይ ቤታቸዉ እስኪገቡ ድረስ እንደሚጠብቃቸዉ ነዉ እግዚአብሔር ለአማኞች ዋስትናን እንደሚሰጥ ነዉ፤ እንዲሁም በልባቸዉ ያለዉን እምነት በመንከባከብ ነዉ፤ እግዚአብሔር በእምነት እንዳዳነን ሁሉ በእምነት ይጠብቀናል (ኤፌ28)፤በእምነት የዳነ ሰዉ እምነቱን ሊያጣዉ አይችልም ምክንያቱም እግዚአብሔር ስለሚንከባከበዉ ነዉ፤

የሚነሳዉ ጥያቄ እግዚአብሔር ሳይሆን አማኙ ራሱ ነዉ እምነቱን መለማመድ ያለበት የሚል ነዉ፤ እንዴት ነዉ ልኡላዊ የሆነ አምላክ በአማኙ ዉስጥ ያለዉን እምነት የሚንከባከበዉ? ከሆነ አማኙ የራሱን ነጻ ፈቃድ እንዴት ይለማመዳል? መልሱ ተመሳሳይ ሆኖ ሰዉየዉ የዳነዉ በእምነት ነዉ፤ በዮሐ 644 ላይ ‹‹የላከኝ አብ ከሳበው በቀር ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ›› እግዚአብሔር ሰዉየዉን ወደ ክርሰቶስ ይስባል እና በመጨረሻም አስነሳዋለሁ፤ እግዚአብሔር ሰዉየዉን ወደ ክርስቶስ ይስበዋል ያም ሰዉ እምነቱን ለድነት በነጻ ፈቃዱ ይለማመዳል፤ ሰዉየዉ አንዴ ከዳነ መንፈስ ቅዱስና ልጁ እምነቱን በመማለድ ይንከባከቡታል፤

በሮሜ 8 ላይ ጳዉሎስ በግልጽ ሲናገር አማኞች በፍጹም የዘላለም ፍርድ የለባቸዉም ከእግዚአብሔር ፍቅር የሚለያቸዉም ነገር የለም፤( .26-27)

ሮሜ 8: 26-27

² እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንጸልይ እንደሚገባን አናውቅምና፥ ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፤
²
ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ አሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና። 

የእኛ ድካም መከራን ጨምሮ እምነታችንን ልናጣዉ ወይም ልንጥለዉ እንችላለን፤ ቁጥሮቹ የሚነግረን መንፈስ ቅዱስ እንደሚማልድልን ነዉ ይህም ደግሞ እምነታችን እንዳይጠፋ ያደርጋል፤ አዳም ክላርክ የተባለ ሰዉ ሰለ ቁጥሮቹ ሲናገር ‹‹ጌታችን ይማልድልናል በመስማማትና በማስተዳደር እንደ ወዳጃችን እና ወኪላችን በመሆን ይህ ሁሉ የሚያደርገዉ ለድነታችን ነዉ፤›› (የአዳም ክላርክ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ)

የመንፈስ ቅዱስ የመማለድ ስራ እምነታችን እንዳይጠፋ ዋስትናን ይሰጣል እምነታችን ካልጠፋ ድነታችን ሊጠፋ አይችልም፤ የልጁም በአብ ፊት መማለድ ተመሳሳይ የሆነ ዋስትና ይሰጣል፤ ይህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆንልን የጴጥሮስ ነዉ፤

. ሀጢአታችንን ስንናዘዝ  ጌታ ያድናል  ስንክደዉ  ወይም ስንተወዉ ጥፋት ያመጣብናል::

ይህ ሀሳብ ካላይ ካየነዉ ጋር የሚያያዝ ሲሆን እግዚአብሔር ሰዉየዉን በእምነት በኩል የሚያድነዉ ከሆነ ድነቱን የሚጠብቀዉ በእምነት በኩል ከሆነ ከዚያ በኋላ ከአንደበቱ ለሚቀጥለዉ ነገር ብዙ አይደግፍም፤

ጴጥሮስ ኢየሱስን ሶስት ጊዜ ከመካዱ በፊት ምን አለዉ? ( ማቴ 2669-74)? .31 ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።( ሉቃ 2231-32) እምነት እንዳይጠፋ ጌታ ማለደ፤ ይህ አገልግሎቱ ደግሞ የሚቀጥል ሲሆን የድነት እምነት ይጠፋል የሚለዉ ዋና ጉዳይ አይደለም፤ የአገልግሎት እምነት በመጀመሪያ በድነት መሰረት ላይ ካልቆመ ሊኖር አይችልም፤ የጴጥሮስ ክህደት ድነቱን አላጠፋበትም የዳነ አልነበረም ማለት አንችልም፤

ኢየሱስ መቼ ነዉ የተለወጥከዉ ብሎ ይጠይቅሃልን? ጴጥሮስ እምነት ነበረዉ ለዚህ ነዉ እምነቱ እንዳይጠፋ የማለደለት፤ የጴጥሮስ ለዉጥ የመጣዉ ሶስት ጊዜ ክዶት ወጥቶ ከሮጠና ከመከራዉ በኋላ ነበር፤ ኢየሱስን ሶስት ጊዜ ሲክደዉ (ማቴዎስ 2669-74) በኋላም በከባድ መከራ መካከል ቆሞ ነበር ( ሐዋ 418-20 እና 527-29)

ክህደት ዉጫዊ ተግባር ነዉ ዉጫዊ ተግባር ደግሞ በዉስጥ እየሆነ ስላለዉ ጉዳይ በፍጹም አመላካች አይደለም፤ከላይ እንዳየነዉ ሰዉ ሆኖ ስህተትን የማያደርግና የማይፈርድ የለም፤ ልክ እንደ ተዋናይ መድረክ ላይ ወጥተዉ ኢየሱስን በአፋቸዉ የሚቀበሉ በልባቸዉ ግን የሚክዱ ሰዎች እነሱ ከሀዲ ሊባሉ ይችላሉ፤ አንዳንዶች ደግሞ በአፋቸዉ የሚክዱ በልባቸዉ ግን የእዉነት የማይክዱ ይኖራሉ፤ ጴጥሮስ ኢየሱስን የካደዉ ስጋዉን ለማዳን ነዉ ከልቡ ነዉ ኢየሱስን የካደዉ የሚያስብል ምክንያት የለም፤ ለዉጫዊ ክህደት የሚዳርጉ ምክንያቶች ይኖራሉ  እንደ ክፉ ልምምድ ካላቸዉ የክርስቲያን መሪዎች ወይም በእምነቱ የቤተሰብ መገለል ሲደርስበት፤ አንዳንዴ ከራሱ ጋር ሰዉ ሲጣላ፣ሲናደድ ጌታን ሊተዉ ይችላል፤ በስጋዉ ሲያረጅ በዉስጡ የሚያድን እምነት ካለዉ ከእግዚአብሔር ጋር ያለዉን ግንኙነት በልቡ እንደገና ይጀምራል (1ጴጥ 15)

. አማኙ ለሞት የሚያደርስ ሐጢአት ሲሰራ

ለሞት የሚያበቃዉ ሐጢአት የተጠቀሰዉ 1ዮሐ 516 ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም”  ይህን ጥቅስ አንዳንዶች ሲፈቱት አማኝ ድነቱን ሊያጣ ይችላል ብለዉ ነዉ፤

ለሞት የሚያበቃዉ ሐጢአት ምንድን ነዉ? 1ቆሮ5 ላይ እንዳየነዉ ከአባቱ ሚስት ጋር ዝሙት የሰራ ሰዉ በቤተክርስቲያን ተግሳጽ ስር ሆነ፤ በቁ 5 ላይ ጳዉሎስ እንዳዘዘዉ ‹‹መንፈሱ በጌታ በኢየሱስ ቀን ትድን ዘንድ እንደዚህ ያለው ለሥጋው ጥፋት ለሰይጣን እንዲሰጥ ፍርዴ ነው›› ለሞት የሚያበቃዉ ሐጢአት እንደ 1ቆሮ5 ላይ ያለ ሐጢአት አይደለም ሰይጣን ሰጋዉን እንዲያሰቃይ ተላልፎ ቢሰጥም ነፍሱ በጌታ ቀን ትድናለች፤

በዘዚህ ስፍራ ምን አየን? ሰዉየዉ ንስሀ ገብቷል ( 2ቆሮ25-8) ሰይጣን ሊገድለዉ ስጋዉን ሊያጠፋ ፈለገ ነገር ግን ነፍሱ በጌታ ቀን ትድናለች፤ድነቱ በጌታ የተጠበቀና ዋስትና ያለዉ ነዉ፤ ንስሀ ባይገባ እንኳ ይህ ሰዉ ድነቱ የተጠበቀ ነዉ፤ ለሞት የሚያበቃ ሐጢአት ማለት የስጋ ሞት እንጂ ዘላለማዊ ሞት አይደለም፤ አማኝ የዘላለም ሞት የሚያበቃ ሀጢአት ሊሰራ አይችልም፤

. አማኝ ይቅር የማይባል ሀጢአት ይሰራል ይህም መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ነዉ

ኢየሱስም አለ፤

ማቴ 1231-32

³¹ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
³²
በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም። 

ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ስም ማጉደፍ ማለት ነዉ አነዳንደ አማኞች ይህን ጥቅስ ካነበቡ በኋላ አማኞች መንፈስ ቅዱስን  ቢሳደቡ ደነታቸዉን ያጣሉ ብለዉ ይናገራሉ፤

በፈሪሳዉያን አስተምህሮ ኢየሱሰ ብቻ አጋንንትን እንደሚያወጣ፣ ለምጻሙ አይሁድን መፈወስ፣ ከመወለዱ ጀምሮ እዉር የሆነዉ ሰዉ መዳን፣ በአገልገሎቱ ዉስጥ እርሱ ብቻ ይህን እንደሚደርግ ያምናሉ፤ በማቴ 12 ላይ ኢየሱስ አጋንንትን አስወጣ ብዙዎች ሰዎች ግን እንዲህ ሲሉ ተማከሩ ይህ የዳዊት ልጅ አይደለምን?( ማለት መሲሁ) (. 22-23)? ፈሪሳዉያን ሲመልሱ ግን ‹‹ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ›› (.24) ይህን በማለታቸዉ የራሳቸዉን አስተምህሮ አጣርሶባቸዋል፤የእስራኤል የሐይማኖት መሪዎች የኢየሱስን መሲህነት ከመጀመሪያዉኑ አልተቀበሉትም፤ በአጋንንት እንደተያዘ ሰዉ ቆጠሩት፤ይህም ንግራቸዉ ወደ ሕዝብ ተሰራጨ፤ ሁሉም እስራኤል የኢየሱስን መሲህነት አልጣሉም ተከታዮች ነበሩት በብሔራዊ ደረጃ እሰራኤል የእስራኤልን መሲህነት አልተቀበለችም፤ እንዲሁም በእርሱ የሚሰራዉን መንፈስ ይህ አጋንንት ነዉ ብላ በየነች፤

ሐረጉ ምን ይላል ? . 32 በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም፤ በዕብራይስጥ የሱስ ማለት በሚመጣዉ አለም የሚመጣዉ ኦላምሃባ ይህም ማለት አስተማሪ/መምህር/ሲሆን ለመሲሁ ግን የሺህ አመቱ ንጉስ ማለት ነዉ፤ ጸሐፊዉ እንደሰማዉ በሕጻናት ከንፈር ላይ ሁሉ ያለዉ ቃል መምህር/ረቢ/ ነዉ፤ ይህ ቃል በትላልቅ የጥቅስ ማዉጫ መጽሐፍ ላይ ያለ ነዉ፤ የግሪኩ ቃል ዓለምን ‹‹አየን ይለዋል ይህም ዘመን በተለይም (የአይሁድን) የመሲሁ ዘመን( የአሁኑን ወይም መጪዉን ያመለክታል፤

ስለ ይቅር የማይባለዉ ሐጢአት ኢየሱስ የተናገረዉ ዘላለማዊ የሆነ ይቅርታ ስለሌለዉ ነገር አይደለም ሰለ መሲሁ መንግስት መናገሩ ነዉ፤ ምክንቱም አገሪቱ መንፈስ ቅዱስን ተሳድባለች አልተቀበለችም፤መንግስቱ በዚያ ሰአት (በዚህም ጊዜ) አልተመሰረተችም፤ ወይም በሚመጣዉም ዘመን አላለም ነገር ግን ኢየሱስ የተናገረዉቁ (በማቴ 2338-39) ‹‹እነሆ፥ ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀርላችኋል እላችኋለሁና፥ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው እስክትሉ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ አታዩኝም›› ቤታቸዉ (ቤተመቅደሳቸዉ) ይፈርሳል ( 70/) አገሪቱ እርሱን እንደገና መሲህ አድርጋ እስክትቀበለዉ ዳግም ተመልሶ መንግስቱን እስኪመሰርት ድረስ ዳግም አታየዉም፤

. የዕብራዉያን መጽሐፍ የማስጠንቀቂያ ክፍል

ብዙ የዕብራዉያን መጽሐፍ ዉስጥ አማኞች ድነታቸዉን እንደሚያጡ የሚመስል የሚናገር ክፍል አለ ከእነርሱ ዉስጥ ሁለቱ

ዕብ 64-6 እና

አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩትን
መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን
በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው፤ ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያዋርዱትማልና።

 ዕብ 1026-29

² የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥
²
የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ።
²
የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤
²
የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል?

እንደገና ታሪካዊና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራዉን እንመልት

መልዕክቱ የተጻፈዉ 70 / በፊት በኢየሩሳሌምና በሮማዉያን ግዛት ለሚኖሩ የአይሁድ አማኞች ነዉ፤ለዚያ ፍርድ ኢየሱስ ደቀመዛሙርን አስጠንቀቆ ነበር ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ።የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤ (ሉቃ 2120-21)

ተከታዮቹ በከተማዋ ዉስጥ እንዳይቆዩ እንዲሸሹ ነገራቸዉ በሁለቱም ግንባር ታላቅ ፈተና ደረሰባቸዉ፤ የመጀመሪያዉ በምድራቸዉ አማኝ አይሁዳዉያን ስደት ደረሰባቸዉ በስደቱ ብዙዎች ኢየሱስን እየከዱ ወደ አይሁዳዊ እምነት ሲመለሱ ሁለተኛዉ ደግሞ ኢየሩሳሌምን ቀናተኛ የሆኑ አይሁዶች ለመቆጣጠርና ሮማዉያንን ለመዉጋት ተዘጋጁ፤አማኞች ሮማዉያንን ለመዉጋት አልሄዱም ነገር ግን ወደ ተራራ ሽሹ ነዉ የተባሉት፤ የዕብራይስጡ መጽሐፍ እንደተጻፈዉ ጌታን መታዘዝ እንዳለባቸዉ እንጂ ወደ ወደ አይሁዳዊዉ አስተምህሮ መመለስ እንደሌለባቸዉ ነገር ግን ወደ ተራራ ሸሹ ይላል፤ማንኛዉም በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ የተጻፈዉ ማስጠንቀቂያና ፍርድ 70 . ጋር በተገናኘ የተነገረ ነዉ፤ ከዘላለም ፍርድ ጋር በተገናኘ ወደ አይሁዳዉን አስተምህሮ ተመልሰዉ ቢሆን ይታረዱ ነበር ሸሽተዉ ማምለጣቸዉ ሕይወታቸዉ ሊተርፍ ችሏል፤

መጽሐፍ ቅዱስ የራሱ አላማ ያለዉ ነዉ በጌታ ርዳታ እርሱ እንድንታዘዝ ነግሮናል፤በ66 . ሮማዉን ሰራዊታቸዉን አስጠጉ በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ክርስቲያኖች የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግረዉ ወደ ተራራዉ ሸሹ፤ ፔላ በሚባል ስፍራ መሸሸጊያ አገኙ፤ 68. ደግሞ ሮማዉያን እንደገና በመነሳት 70 . ወደ ኢየሩሳሌም በመግባት ከተማዋን ደመሰሱ ቤተመቅደሱም ፈርሶ ብዙዎች ታረዱ፤

በዕብራይስጡ መጽሐፍ ዉስጥ ምንም አይነት ስለ ዘላለማዊ ፍርድ እና ማስጠንቀቂያ የለም ነገር ግን ስለ ስጋዊ ፍርድ ነዉ፤ በዕብራዉያን 6 ዉስጥ ያለዉ ንስሀ ወደ ድነት ለመመለስ የሚደረግ ንስሀ አይደለም፤ ነገር ግን በንስሀ ለጌታ ትዕዛዝ ከመታዘዝ መሸሽ ማለት ለሐጢአት ዳግመኛ መስዋዕት ሊቀርብ አይችልም ይህም የብሉይ ኪዳንን የሙሴ ሕግ  እንደ ምንዝርና፣መግደል አይነት ሐጢአቶች መስዋዕት አይቀርብም ይህ ለሞት ቅጣት ይዳርጋል፤ ለሐጢአት ሌላ መስዋዕት አይቀርብም፤ ይህ ክፍል ሲናገር በክርስቶስ ስቅለት ካለመታዘዝ የመጣ ሥጋዊ ፍርድ ያድናል ማለት አይደለም ነገር ግን በስጋቸዉ መክፈል ያለባቸዉን መክፈል አለባቸዉ ይህ ግን ስለ መንፈሳዊ ሕይወት አይደለም የሚናገረዉ፤

የትኛዉም የዕብራይስጥ መጽሐፍ ቀዱሰ አማኝ ድነቱን ያጣል የሚል ሀሳብ የለዉም፤

3.ማጠቃለያ

ከላይ እንደፈተሸነዉ ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በሁኔታ ላይ የተወሰረተ ዋስትናን የሚደግፍ ይመስላል ነገር ግን አንዱም የመጽሐፍ ቅዱስን የአተረጓጎም መርህ የተከተለ አይደለም፤ዘላለማዊ ዋሰትና እንዳለን ተመልክተናል፤ በግልጽ እንደሚታየዉ ጌታ ለአማኞቹ ዋስትና ሰጥቷል፤

መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ሲጣረስ አንድም ቦታ አናገኝም፤ነገር ግን አረጋግጦ የሚነግረን ነገር በእርሱ እንድንታመን ነዉ፤

እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም( ዮሐ 1028)

አማኝ ጌታን ሲያገለግል ድነቴን አጣ ይሆን ወይ እያለ በፍርሃት መኖር የለበትም ነገር ግን በድነቱ በእግዚአብሔር ጸጋ ዘላለም በመጠበቁ መደሰት አለበት፤ኢየሱስም አለ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ ዕብ 122

እናገልግለዉ!

ለመዳን ምን ማድረግ አለብኝ?

ወደ ውጭም አውጥቶ፦ ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው (ሐዋ 1630)

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት::” ጳዉሎስና ሲላስ መለሱ፤

የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” ( ሮሜ 623)

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”  ዮሐ 316

ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን  ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ፦ መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ ( 1ቆሮንቶስ 15:1-4)

ኢየሱስ የሚሰሙትን በወንጌል እመኑ ስለዚህ በትህትና መልስ መስጠት አለብን::

ማመን ከጀመርህ ያሳዉቁን

እግዚአብሔር ይባርካችሁ!


 በዚህ ጥናት ከተባረኩ እባክዎን ከሌሎች ትስስሮች ጋር ማስተዋወቁን ወይም ማገናኘቱን ያስቡበት.  አመሰግናለሁ. * 

 ኖርማን ማንዞን 2016 

መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነዉ!

 


 

                           ~ DONATE ~            ~ HOME & LIBRARY ~          ~ TRANSLATE? ~

                              Scriptures used by the author are generally in the New King James or New American Standard translations.
                             Scriptures in quotations by Dr. Arnold G. Fruchtenbaum are in the American Standard Version.
                                 Scriptures quoted by others may be in other translations.

 

                            ~      ~      ~

Bible Study Project is currently seeking 501(c)3 status at which time
it will resume issuing tax deductible receipts for U.S. donors.
However, donations are still much needed, particularly for
the sponsorship of BSP literature in foreign languages,
and would be much appreciated! 
Please pray about this.
Thank you.

 

 
© Norman Manzon 2011 - 2023
All rights reserved.

 

Copying and Republication Guidelines